ኤች. አይ. ቪ. ኤድስ

   ኤች. አይ. ቪ. ኤድስኤች.አይ.ቪ. ማለት የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም የሚያዳክም ቫይረስ ነው። ይህ ቫይረስ ነጭ የደም ህዋሳትን በማጥቃት የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም ያዳክማል።

ኤች.አይ.ቪ. ኢንፌክሽን  ይህ ሁኔታ ሊፈጠር የሚችለዉ የኤች አይ ቪ ቫይረስ በሰዉነት ውስጥ ሲገባና ነጮችን የደም ህዋሳት ሲያጠቃ ነው።

ኤድስ  ማለት በቫይረሱ የተያዘ ሰው በሽታ የመከላከል አቅሙ በመዳከሙ ምክንያት በተደጋጋሚ በህመም የመያዝ ምልክቶች ሲታይበት ነው።

ኤች.አይ.ቪ. የሚተላለፍባቸው መንገዶች

 • በቫይረሱ ከተያዙ ሰወች ጋር ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈጸም። ይህ ዋነኛዉና በሃገራችን የተለመደው የቫይረሱ መተላለፍያ  መንገድ ነው።
 • ቫይረሱ ካለባት እናት ወደ ልጅ፣ ይህም ሊሆን የሚችለው በእርግዝና ወቅት በእንግዴ ልጅ አማካኝነት እና ልጅ በሚወለድበት ጊዜ ነው።
 • ቫይረሱ ካለበት ደም ወይም ሌላ ፈሳሽ ጋር መነካካት ሲኖር፣ ይህም ማለት በደም ልገሳ እና በቫይረሱ በተበከሉ ስለታማ እቃወች በጋራ መጠቀም።

  ኤች.አይ.ቪ. የማይተላለፍባቸው መንገዶች

ü  በመሳል፣ በማስነጠስ፣በላብ፣ በእንባ፣ በመተቃቀፍ፣ በመጨባበጥ

ü  የመጸዳጃ እና የመታጠብያ እቃወችን በጋራ በመጠቀም

ü  በወባ ትንኝ እና በሌሎች ነፍሳት ንክሻ

ü  በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር አብሮ  በመብላት፣ በመጠጣት

የኤች.አይ.ቪ. መከላከያ መንገዶች

ü  የወሲብ ግንኙነት ከመፈጸም ሙሉ በሙሉ መታቀብ

ü  ከአንድ በላይ የወሲብ ጓደኞች አለመያዝ

ü  በአጋጣሚ ከሚያገኟቸው ሰዎች ጋር ወሲብ ከመፈጸም መቆጠብ

ü  ኮንዶምን ወሲባዊ ግንኙነት በሚደረግበት ጊዜ ሁሉ በትክክል መጠቀም

ü  በቫይረሱ ከተበከሉ ማናቸውም ስለታም እቃዎች፣ የሰውነት ፈሳሾች ጋር መነካካት እንዳይኖር ጥንቃቄ ማድረግ

ü  ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ ያልተረጋገጠ ደም ልገሳ እንዳይኖር ጥንቃቄ ማድረግ

ü  የተበከለ ውዳቂ ነገር ሁሉ በተገቢመልኩ እንዲወገድ ማድረግ

ü  የተበከሉ እቃዎችን ለመያዝ ተገቢጥንቃቄ ማድረግ(በመከላከያ አልባሳትና በእጅ የሚጠለቅ ጓንት መጠቀም)

ü  ስለታማ እቃዎችን በጋራ የመጠቀም ጎጅ ልማዳዊ ድርጊትን ማስወገድ

ü  ንጽህናው ባልተጠበቀ እና በጋራ የውጊ መርፌ አለመጠቀም

ü  የአባለዘር በሽታ ሲያጋጥም መታከም

ü  ኤች አይ ቪን ጨምሮ የአባላዘር በሽታወችን ለመከላከል የሚያስችል የጤና  አጠባበቅ ትምህርት ማግኘት

ü  በእርግዝና ወቅት የ ኤች አይ ቪ የምክርና የምርመራ አገልግሎት ማግኘት

ü  ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ የሚረዳ የጸረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት መጠቀም

ለኤች.አይ.ቪ. የሚያጋልጡ ሁኔታወች

 • የግንዛቤ ማነስ
 • ከአንድ በላይ የወሲብ ጓደኞች መያዝ
 • ባጋጣሚ ከሚያገኙት ሰው ጋር ወሲብ መፈጸም
 • አልኮልና አደንዛዥ እጽ መጠቀም
 • ኮንዶምን በትክክልና ሁልጊዜ አለመጠቀም
 • የጤና አገልግሎት መጠቀም አለመፈለግ(ለምሳሌ የአባላዘር በሽታ ህክምና፣ የኤች አይ ቪ ምርመራ…..)
 • ድህነት
 •  ከቦታ ቦታ መዘዋወር
 •  ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች
 • የጾታ እኩልነት አለመኖር፣ጦርነት…. ናቸው።

ኤች አይ ቪ የ ሚያደርሰው ተጽእኖ

 • በግለሰብ ላይ

ü  ህመምና ሞት

ü  የማምረት/የመስራት አቅም መቀነስ

ü  የህክምና ወጭ መጠን መጨመር

ü  በህመም ምክንያት ከስራ/ ከትምህርት ገበታ መቅረት

ü  ስነ ልቦናዊ ችግሮች(ተስፋ መቁረጥ፣ስለወደፊቱ በማሰብ አለመረጋጋት ፣ ሃዘን ወዘተ)

 • መገለልና መድሎ በቤተሰብ ላይ

ü ኤች. አይ. ቪ . ኤድስ የቤተሰብ የጤና ችግር ነው። በሽታው ሚስት/ ባልንልጅን ሊመለከት ይችላል።

ü  የማምረት ችሎታ ማጣት

ü  የወጭ መጠን መጨመር (ለህክምና፣ለቀብርና ለሌሎች ጉዳዮች)

ü  ሃዘንና የሚወዱትን ሰው ማጣት

ü  ከሞቱት ሌላ የቀሩት የቤተሰብ አባላት ጤንነት መቀነስ(የልጆች ጤና)

ü  የቤተሰብ ሃላፊነት በልጆች ላይ መውደቅ

ü  መገለልና መድልዎ

 • በህብረተሰብ ላይ

ü  ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል የሰው ሃይል ማጣት

ü  ማህበራዊ ግንኙነት ላይ የሚያጠላ ተጽዕኖ፣ መገለልና መድልዎ

ü  ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ልጆችና ድጋፍና እርዳታ የሚፈልጉ ሰወች ቁጥር መጨመር

ü  የአምራች ሃይል መቀነስ

 • በሃገር ላይ

ü  የአምራች ሰራተኛ ሃይል መቀነስ

ü  በሃገሪቱ የጤና አጠባበቅ ስርዐት ላይ ጫና መፍጠር

ü  ሰራተኞች ከስራ ገበታቸው በህመምና  በሞት መለየት ምክንያት በሁሉም የኢኮኖሚ ክፍሎች ከፍተኛ ተጽዕኖ ይደርሳል።

የኤች አይ ቪ የደም ምርመራ እና የምክር አገልግሎት

 • አንድ ግለሰብ በደሙ ዉስጥ ኤች አይ ቪ መኖር አለመኖሩን የደም ምርመራ በማድረግ ማወቅ ይችላል። ይህም ግለሰቡ ቀጣይ ህይወቱን ጤናማ በሆነ መልኩ ለመምራት እንዲችል ግንዛቤና መልካም አጋጣሚ ይፈጥርለታል።
 • የምክር አገልግሎት ሳያገኙ በደም ምርመራ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንዳለ ያረጋገጡ ሰወች በስነ ልቦናቸው ላይ የሚደርስባቸውን ቀውስ(ድንጋጤ፣ ፍርሃት፣ አለመረጋጋት፣……)መቋቋም ያቅታቸዋል። ስለዚህ የምክር አገልግሎት ከኤች አይ ቪ የደም ምርመራ ጋር ማግኘት እጅግ ጠቃሚ ነው።
 • የኤች አይ ቪ የደም ምርመራና የምክር አገልግሎት የኤች አይ ቪ ኤድስን ስርጭት ለመግታት አይነተኛ ሚና ይጫወታል።
 • በደም ምርመራ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንዳለ ያረጋገጡ ሰወች በሚያገኙት ምክር ታግዘው ከቫይረሱ ጋር ለረዥም ጊዜ እንዴት መኖር እንደሚችሉና የወደፊት ህይወታቸውን እንዴት መምራት እንዳለባቸው እቅድ በማዉጣት ራሳቸውን ያዘጋጃሉ። የባህሪ ለውጥንም ለማምጣት ዉሳኔ ያደርጋሉ።
 •  በደም ምርመራ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንደሌለ ያረጋገጡ ሰወች ደግሞ ወደፊት እንዳይያዙ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የባህርይ ለውጥ እንዲያመጡ ያግዛቸዋል። ስለዚህ ተማሪዎች በየዩኒቨርሲቲው ክሊኒክ እና በየጤና ድርጅቱ የሚሰጠውን የኤች አይ ቪ የደም ምርመራና የምክር አገልግሎት በማግኘት ራሳችንን ማወቅ እና የወደፊት ህይወታችንን ጤናማ በሆነ መልኩ መምራት ይገባናል።
 • በተለይም ወጣቶች ከጋብቻ በፊት ከጓደኛችን(ፍቅረኛችን) ጋር የኤች አይ ቪ የደም ምርመራና የምክር አገልግሎት ማግኘት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል።
 • ነፍሰ ጡር የሆኑ ወጣት ሴቶችም ኤች አይ ቪ ወደ ህጻኑ እንዳይተላለፍ ለመከላከል ወደ ጤና ድርጅት በመሄድና የኤች አይ ቪ የደም ምርመራ በማድረግ ራሳቸውን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
 • አንድ ግለሰብ የደም ምርመራ አድርጎ በደሙ ውስጥ ኤች አይ ቪ እንዳለበት እስካልተረጋገጠ ድረስ ግለሰቡን በማየት ብቻ ሰውነቱ ስለከሳ ኤች አይ ቪ አለበት ማለት ስህተት ነው።

በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ የአባላዘር በሽታዎች

        የአባላዘር በሽታዎች የሚተላለፉት በሁለት ሰወች መካከል በሚፈጠር የፈሳሽ መነካካት አማካኝነት ነው። ማለትም በወንድ የዘር ፍሬ ፈሳሽ፣ በሴት የብልት ፈሳሽ እና በደም አማካኝነት ነው። በተጨማሪም በበሽታው ከተያዘች እናት ወደ

ልጅ በተላላጠ ቆዳ ንክኪ አማካኝነት ሊተላለፍ ይችላል። የአባላዘር በሽታ በዋናነት የሚተላለፈው በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ ሲፈጸም ነው።

ምንጭ – ethiopiawinote

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.