በዶ/ር አብርሃም ክብረት (ሜዲካል)

SEXUUAL INTበአሁኑ ወቅት ዕድሜየ 24 ሲሆን አንድ የወንድ ጓደና አለኝ፡፡ ታዲያ ከዚሁ ጓደኛየ ጋር በጣም የሚያሳቅቀኝ ነገር ቢኖር ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት የሌለኝ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ እሱን ግራ ሳያጋባው የቀረ አይመስለኝም፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን ቦይ ፍሬንዴን በጣም ስለምወደውና እንዲለየኝ ስለማልፈልግ ይህንን የወሲብ ችግሬን እንዴት ነው መፍታት የምችለው? ችግሩ ከየት መጣ? መፍትሄውስ?

ዜድ.ቢ ነኝ

መልስ

የወሲብ ፈላጎት ማነስ ወይም መብዛት ይከሰታል፡፡ በተለይም በሴቶች ዘንድ ችግሩ በጣም ብዙ ወይም ከፍተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ በጣም አነስተኛ ሲሆን አንድ ሰው ስለ ወሲብ ፍላጎት ሳያስብ  ሊቀር ይችላል፡፡ ሌሎች የወሲብ ፍላጎት ባይኖራቸውም በሴክስ ግን ይደሰቱበታል፡፡ ችግሩ በጣም ከባድ ሲሆን ደግሞ የወሲብ ፍላጎት አይኖርም፡፡ ሊከሰት ይችላል ብለው ሲያስቡም ይጨነቃሉ፡፡ አንዳንዴ በማስተርቤሽን፣ የወሲባዊ ፋንታሲና በማንኛውም ግንኙነት የወሲብ ገፅታ ላይ ምንም አይነት ፍላጎት አያሳድርም፡፡ አንድ ሰው ያለው አነስተኛ የወሲብ ፍላጎት የቱንም ያህል አነስተኛ ቢሆን እና በየትኛውም ጊዜ ቢከሰትም አንኳን ይህ ሁኔታ ችግር ሊሆን የሚችለው ግለሰቡ ወይም ተጓዳኞቹ እንደ ችገር ሆኖ ሲያገኙት ብቻ ነው፡፡

ምልክቶቹ

  • በየትትኛውም የወሲባዊ እንቅስቃሴ ላይ ፍላጎት አለመኖር፤
  • የወሲባዊ እንቅስቃሴዎች ማነስ
  • የወሲባዊ እንቅስቃሴ አለመኖር እና ስነልቦናዊ ችግር ሲፈጠር፤
  • ስለ ወሲብ የደበዘዘ ስሜት መኖር፤
  • ግለሰቡ በአካል ወሲባዊ እንቅስቃሴ ቢኖረውም ስነልቦናዊ ፍላጎት ግን አይኖረውም፤
  • የሴት ብልት መድረቅ ሲከሰት፤፤
  • የብልት አካባቢ ስሜት ሲቀንስ፤
  • የወሲባዊ እርካታ ላይ ለመድረስ አለመቻል፤

   መንስኤዎቹ

እድሜ፡- ወንዶችም ሆነ ሴቶች ሲያረጁ በሰውነታቸው ውስጥ በርካታ ለውጦች ይከሰታሉ፡፡ አንዳንዶቹ ለውጦችም የወሲባዊ ፍላጎትን ሊያውኩ ይችላሉ፡፡

ጾታ፡- ምንም እንኳን ወንዶችም ሆነ ሴቶች የወሲብ ፍላጎት መቀነስ ቢደርስባቸውም በብዛት የሚከሰተው ግን በሴቶች ላይ ነው፡፡

ማረጥ፡- በሴቶች ዘንድ የማረጥ ምልክቶች የፈሳሽ መቀነስ፣ የኤስትሮጂን መጠን መቀነስ ሲሆኑ ይህም ሴቶችን ለወሲብ ሊያነሳሳ የሚችል ነው፡፡

የሆርሞን መጠን፡- የቴስቴስትሮን መጠን ማነስ በወንዶችም ሆነ በሴቶች ላይ የወሲብ ፍላጎት መቀነስን ያስከትላል፡፡

የማህፀን አካባቢ ችግሮች፡- በርካታ ሁኔታዎች ሴቶች ወሲብ ሲፈፅሙ እንዳይመቻቸው ሊያደርጋቸው ይችላል፣ እነዚህም የማህፀን አካባቢ ችግሮች፣ የብልት መድረቅ፣ አንደሜትርዮሲ፣ የማህፀን እጢ፣ ኦቫርያን ሲስት፣ በኦፕራሲዮን የተነሳ የተከሰተ ጠባሳ ወዘተ ናቸው፡፡

ከመድኃኒት ጋር መለማመድ፡- የድብርት ስሜትን ለማከም የሚያገለግሉ መድኃኒቶች የወሲብ ፍላጎትን ሊያዳክሙ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ የነዚህ መድኃኒቶች በብዛት የጎን ጠንቃቸው የወሲብ ፍላጎት መቀነስ ነው፡፡ ሌሎች ተመሳሳይ ችግር የሚያስከትሉት ደግሞ አንዳንድ የኬሞቴራፒ መድኃኒቶች፣ ለደም ግፊት ህመም የሚሰጡ መድኃኒቶችና ለአእምሮ ህመም የሚሰጡ መድኃኒቶች ናቸው፡፡

ድብርት፡- በአጠቃላይ ድብርት ሲከሰት በአብዛኛው የደስተኛነት ስሜት መቀነስ የሚከሰት ሲሆን የወሲብ መነቃቃትንና እንቅስቃሴን የመቀነስ አዝማሚያ አለው፡፡

ጭንቀትና ውጥረት፡- በእነዚህ የደስተኛነት ስሜት ቀናሽ ሁኔታዎች የተነሳ የምትሰቃይ ከሆነ የወሲብ ፍላጎትን በጊዜያዊነት ወይም በዘላቂነት ሊቀንሰው የሚችል ሲሆን ይህም ባለው ጭንቀትና የጥፋተኝነት ስሜት ሊወሰን ይችላል፡፡

ስለወሲብ መጥፎ ተሞክሮ ሲኖር፡- የወሲባዊ ፍላጎት መቀነስ የሚከሰተው ወሲብ ሲደረግ ህመም ከተከሰተ፣ በልጅነት ወቅት ጉዳት ያስከተሉ ሁኔታዎች ከነበሩ ወይም ከፍተኛ የወሲብ ፍራቻ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸው ወይም ወሲብን እንደሀጢያት የሚቆጥሩ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ የወሲብ ፍላጎታቸው አነስተኛ ነው፡፡

ከተጓዳኝ ጋር መለማመድ፡- አንድ ሰው ከወሲብ ተጓዳኝ ጋር በጣም ሲለማመድ የወሲብ ፍላጎቱ ሊቀንስ ይችላል፡፡

ፍላጎትን ለመጨመር በራስ የሚደረጉ ህክምናዎች፡- ለሁሉም የወሲብ ችግሮች መድኃኒት የግድ ላያስፈልግ ይችላል፡፡ አንዳንዶቹ መንስኤዎች በአንቺና በተጓዳኝሽ አማካኝነት ሊፈቱ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት ደግሞ ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ ይከስማሉ፡፡ ስለዚህም ትግስትና መግባባት ብቻ ናቸው የሚያስፈልጉት፡፡

. አንዳንድ ጊዜ ከተጓዳኝ ጋር ስለችግሩ ማውራት በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ለተጓዳኞቻቸው ስለወሲባዊ ፍላጎቶቻቸው የሚያወሩ ሴቶች የሚያረካ የወሲብ ህይወት የማግኘት እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡

. ወሲብ ከመፈፀምም በፊት ሪላክሴሽን ቴክኒኮችን መጠቀም፡፡

. በብልት መድረቅ የተነሳ የሚመጡ ለወሲብ የመነሳሳት ችግሮችን ለመፍታት ማለስለሻዎችን መጠቀም

. ወሲብ የሚደረግበቴን ፕሮግራም መቀየር፡፡ ይህም ቀስቃሽ ማሳጅ፣ አዳዲስ የወሲብ ፖዚሽኖች፣ የወሲብ አነቃቂ ቪድዮዎችን መጠቀም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ወይም ደግሞ መፃህፍትን መጠቀም ሊሆን ይችላል፡፡

 

የህክምና መፍትሄዎች

ህክምናው የሚወሰነው በመንስኤው ላይ ነው፡፡ ችግሩ የተከሰተው አካላዊ በሆነ ሁኔታ የተነሳ ከሆነ ተገቢው ህክምና እንዲደረግ ሀኪም መጠየቅ፡፡ ይህም መድሀኒቶችን፣ የኑሮ ዘይቤ ለውጥን፣ ኦፕራሲዎን ወይም የምክር አገልግሎት ሊሆን ይችላል፡፡

የሚከተሉት ከተከሰቱ በሀኪም ይታይ

  • ቀድሞ ባልነበረ ሁኔታ ወሲባዊ ግንኙነት ህመም ያለበት ይሆናል፡፡ ተገቢውን ትኩረት የሚፈልግ ኢንፌክሽን ወይም ሌላ ህመም ሆናል፡፡
  • የአባላዘር ህመም ሊደርስበት የሚችል እድል ካለው፡፡

በሴቶች ላይ ለሚከሰት አነስተኛ የወሲብ ፍላጎት መቀነስ ችግሮች የሚከተሉትን ህክምና መከተል ይቻላል፡፡

የብልት ማለስለሻ

ለብልት ድርቀት የሚሆኑና ያለ ሀኪም ማዘዣ የሚገዙ ጄሎች፣ ክሬሞች ናቸው፡፡ ኮንደም የምትጠቀሚ ከሆነ ወተር ቤዝድ ማለስለሻዎች ተመራጭ ናቸው፡፡ እንደ ፔትሮሊየም ጀል፣ ሜኔራል ዘይት ወይም ቤቢ ኦይል ኮላቴክስ ኮንደሞች ጋር መስተጋብር በመፍጠር እንዲቀደዱ ደርጋቸዋል፡፡

ቶፒካል ኤስትሮጅን

ለአረጡ ሴቶች የሚታዘዝ ሲሆን በተለይም የብልት መድረቅን የሚያክም ነው፡፡

መድሃኒቶች

ቪያግራን ሴቶች ፈፅሞ መውሰድ የለባቸውም

Leave a Reply to Anonymous Cancel reply

Please enter your comment!
Please enter your name here