ሉብሪካንት በሁለት (ደረቅ) አካላት ንክኪ ወይም ፍጭት ምክንያት የሚፈጠር ሰበቃ (ፍሪክሽን)

ሉቦ

sexpየሀገራችን ሙስሊሞች ሲተርቱ፣ “ደረቅ በደረቅ፣ አላህም አይታረቅ!” ይላሉ። ይህ አባባል፣ ለዛሬ ከመረጥነው ርዕስ ጋር እጅጉን ይስማማል። የወሲብ መፈጸሚያ አካላቶቻችን ሳይረጥቡ፣ በደረቁ ወሲብ ከፈጸምን፣ ማመም ብቻ ሳይሆን፣ የወሲብ ፍላጎታችንም ይከሽፋል። ለግብረ ሥጋ ግንኙነት (ቫጂናል ሴክስ)፣ ለፊንጢጣ ወሲብ (አናል ሴክስ)፣ ራስን በራስ ለማርካት (ማስተርቤሽን) አለስላሽ ቅባቶች (ሉብሪካንቶች) በጣም አስፈላጊ ናቸው።

ሉብሪካንት በሁለት (ደረቅ) አካላት ንክኪ ወይም ፍጭት ምክንያት የሚፈጠረውን ሰበቃ (ፍሪክሽን) መጠን ይቀንሳል። የሰበቃው መቀነስ ደግሞ የአካላቱን ዝለትና ብቃት ያሻሽላል። ከወሲብ አንጻር፣ ሁለቱ አካላት እምስና ቁላ፣ ቁላና እጅ፣ እጅና እምስ፣ እምስና እምስ፣ ቁላና ፊንጢጣ (ቂጥ) ሊሆኑ ይችላሉ—እንደየ ወሲቡ ዓይነት።

እምስ በተፈጥሮዋ እርጥብ መሆን ትችላለች። በተፈጥሮ የራሷ የሆነ ሉብሪካንት ታመነጫለች። ይህ ሉብሪካንት፣ ቁላ ያለምንም ችግር እምስ ውስጥ ሰተት ብሎ እንዲገባና እንዲወጣ ያደርጋል። ሴቶች የወሲብ ፍላጎታቸው ሲነሳሳ፣ እምሳቸው ይህን የተፈጥሮ ቅባት ያመነጫል። የቅባቱም መዓዛ የወንድን የወሲብ ፍላጎት ያነሳሳል። ይህ የተፈጥሮ ቅባት፣ ሴቶች ስሜታቸው ገፍቶ ሲመጣ (ኦርጋዝም ላይ ሲደርሱ) ከሚለቁት ፈሳሽ (ኢጃኩሌሽን) የተለየ ነው—የዚህኛው ፈሳሽ ምንጩ ማህጸን አከባቢ ነው። ምንም እንኳ እምስ በተፈጥሮ የራሷን ቅባት ማመንጨት ብትችልም፣ አንዳንዴ የማታመነጭበት (የምትደርቅበት) ጊዜ አለ። በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ ሰው ሰራሽ የወሲብ ቅባቶች (ሉብሪካንቶች) አስፈላጊ የሚሆኑት። ያለ ሉብሪካንቶች ወሲብ ከተፈጸመ፣ በጣም የምትጎዳው ሴቷ ናት። ብዙ ጊዜ ሴቶች “አመመኝ” ከሚሉባቸው ተጠቃሽ ምክንያቶች መካከል አንዱ ይኼው ነው። አንዳንድ ወንዶች ምራቃቸውን በመጠቀም እምስን ለማለስለስ ወይም ለማርጠብ ይሞክራሉ። ሆኖም ግን ምራቅ ቶሎ፣ ቶሎ ስለሚደርቅ ውጤታማ አይደለም። ከዚያም በተጨማሪ ፣ የምትበዳትን ሴት ደጋግመህ እምሷን በምራቅህ የምትቀባባ ከሆነ ላይመቻት ይችላል (አይደለም ተደጋግሞ አንዴ የተጠቀምከው ራሱ ይደብራል)—ይህ እምስን ከመላስ ወይም ከመሳም የተለየ ነው። ስለዚህ የሷን ፍላጎት ጠብቀህ፣ ራስህንም ማርካት ከፈለግህ፣ ሌላ ዓይነት ሉብሪካንትን መጠቀም የግድ ነው።

አንዳንድ ሴቶች ደረቅ ወሲብን የሚወዱ አሉ። እነዚህ ከህመም ደስታን የሚያገኙ ሴቶች ግን በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ስለሆነም “እንትና ወዳው ነበር” ብለህ፣ እከሊትን ስቃይ ውስጥ ከመክተትህ በፊት አስብበት።

የእምስ ወሲብ ስትፈጽሙ ሰው ሰራሽ ሉብሪካንትን መጠቀም ካልፈለጋችሁ፣ የፎርፕሌይን ዘዴ ተጠቀሙና እምስ ራሷን በራሷ እንድታረጥብ አድርጓት።

ከእምስ ሌላ የፈረደበት ፊንጢጣም አለ። ፊንጢጣ ግን፣ እንደ እምስ፣ በተፈጥሮው ቅባት አያመነጭም። ስለዚህ የፊንጢጣን ወሲብ የሚፈጽም ሰው፣ ሉብሪካንትን ከመጠቀም ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም! ሌላው አማራጭ፣ ይህ ነው ተብሎ ሊገለጽ የማይችል ህመም ነው።

ሴጋ መምታትም ሉብሪካንት ያስፈልገዋል። ይሄ እንኳ ለብዙዎቻችን ግልጽ የሆነ ጉዳይ ነው። ቁላውን በደረቁ የሚፈትግ ወንድ ያለ አይመስለንም። ብዙዎቻችን “ዕድሜ ለገላ ሳሙና” እያልን፣ ሻወር ውስጥና ከሻወር ውጭ ብዙ ጀብዱ ፈጽመናል። አንዳንዶቻችንማ ከምራቃችን፣  ከአጃክስ ሳሙናና ከቫዝሊን ጋር አደገኛ ፍቅር የያዘን ሰሞን ነበር—አሁንም ፍቅሩ ያለቀቀው ብዙ ነው። በገጠር አከባቢ ያለነው ደግሞ ገራባ እየጨቀጨቅን፣ እጃችንን (መዳፋችንን) በመብዳት ስሜታችንን የምናረካ ብዙ ነበርን፤ ዝናብ ሲዘንብ መሬት ቆፍረን የምንበዳውሳ—ኑሮ በዘዴ?! በርግጥ እነዚህ “ባሕላዊ” ሉብሪካንቶች በሰዓቱ ጥሩ መስለው ቢታዩንም ጉዳታቸው ይልቃል፤ ቁላን ከማስቆጣታቸው ወይም ከማሳከካቸው (ኢሪቴሽን ከማስከተላቸው) በተጨማሪ፣ ያን ያህል ውጤታማ አይደሉም። ስለዚህ የመግዛት አቅሙ ያለው፣ ዘመናዊ ሉብሪካንቶችን ቢጠቀም፣ ራሱን በተሻለ መንገድ ማርካት ይችላል።

ሴቶችም አርቲፊሻል ቁላን (ዲልዶን) እና አንዛሪን (ቫይብሬተርን) ሲጠቀሙ ሉብሪካንት ያስፈልጋቸዋል (ሻማንም ለሚሞካክሩ ሴቶች ሉብሪካንት ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም)። ብዙ ሴቶች፣ ራሳቸውን በራሳቸው ለማርካት፣ ከጣታቸውና ከሌሎች ዘዴዎች በተጨማሪ፣ የተጠቀሱትን መሳሪያዎች በቁላ ምትክ ይጠቀማሉ (አንዳንድ ሴቶች በቁላ ከመበዳት ይልቅ ይህን ዘዴ ይመርጣሉ—በደንብ ስሜታቸው ስለሚወጣላቸውና ለእርግዝናም ሆነ ለአባላዘር በሽታዎች (STDs) ስለማይጋለጡ)። በተለይ፣ በባሕላችን ስማቸው የማይነሳው፣ ሌዝቢያኖች ሲባዱ፣ የወንድን አለመኖር የሚያካክሱበት አንደኛው ዘዴ አርቲፊሻል ቁላንና አንዛሪን በመጠቀም ነው። ባጠቃላይ ሴቶች በቂ አለስላሽ ቅባቶችን ካልተጠቀሙ፣ አርቲፊሻል ቁላው ወይም አንዛሪው እምሳቸውን ያሳምማል። በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ የሚፈጽሙ ሴቶች (የፊንጢጣን ወሲብ ጨምሮ)፣  ሉብሪካንት መጠቀም አለባቸው። አለበለዚያ ሲበዱ (ወይም ራሳቸውን ሲበዱ) የሚሰማቸውን ህመም መቋቋም ሊከብዳቸው ይችላል።

የሉብሪካንቶች ዓይነት

ሉብሪካንቶች በሦስት ይከፈላሉ፦

ውሃ–ነክ
ሲልከን–ነክ
ዘይት–ነክ

እያንዳንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ ጥቅምና ጉዳት አላቸው። ሰዎች በብዛት የሚጠቀሙት ግን ውሃ–ነክ ሉብሪካንቶችን ነው።

ውሃ–ነክ ሉብሪካንት

ውሃ–ነክ ሉብሪካንቶች ውሃማ ናቸው። እንደ ሲልከን–ነክ እና ዘይት–ነክ ሉብሪካንቶች የተጣባቂነትና ጭምልቅልቅ የማለት ባሕሪ የላቸውም። በውሃ ውስጥ የሚሟሙ ስለሆኑ፣ ለማጽዳት አስቸጋሪ አይደሉም። ለዚህም ነው በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ የሆኑት። ሆኖም  በወሲብ ላይ ስንሆን ደጋግመን መጠቀም ሊያስፈልገን ይችላል።

የውሃ–ነክ ሉቦች ትልቁ ጥቅማቸው ከኮንዶም ጋር ስምም መሆናቸው ነው። ለምሳሌ ዘይት–ነክ ሉቦችን ከኮንደም ጋር ተጠቀሙ ብለን አንመክርም ምክንያቱም ላቴክስ ኮንደምን ስለሚበሉ ወይም ስለሚበጣጥሱ (ኮሮዥን ስለሚፈጥሩ) ነው።

ነገር ግን በጣም ጥንቃቄ መደረግ ያለበት፦ ወሲብ ከተፈጸመ በኋላ፣ ሴቶች ይህንን ሉብሪካንት ወዲያው ማጽዳት አለባቸው። ውሃ-ነክ ሉቦች በውስጣቸው ግሊስሪንን (glycerin) ስለሚይዙ ሴቶችን በቀላሉ ለበሽታ (ኢንፌክሽን) ሊያጋልጡ ይችላሉ። ለነገሩ ሁሉንም ዓይነት ሉቦች፣ ከወሲብ በኋላ ወዲያው ታጥቦ፣ ከሰውነት ላይ ማስወገድ አስፈላጊነቱ ምክር አያሻውም።

ተጠቃሽ ውሃ–ነክ ሉቦች፦

አስትሮግላይድ (Astroglide)፦ በብዙ ሰዎች ዘንድ እውቅናን ያተረፈ ሉብሪካንት ነው። ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት ሉብሪካንት ተጠቅሞ የማያውቅ ሰው፣ በአስትሮግላይድ ቢጀምር ጥሩ ነው ብለን እናስባለን።

ማክሲመስ (Maximus)፦ ይኼኛው ከአስትሮግላይድ ከበድ ያለ ነው። አንዴ ከቀቡት ለብዙ ጊዜ የሚቆይና ወፍራምም ነው። ስትባዱ በደንብ እንዲያሙለጨልጫችሁ ከፈለጋችሁ ማክሲመስ በጣም ተመራጭ ነው።

ኬ ዋይ ጄሊ (KY Jelly)፦ ኬ ዋይ በጣም ታዋቂ ነው ግን እንደ ስሙ አይደለም። አስትሮግላይድ አስር እጅ ይሻላል። ሆኖም አንዳንድ ሰዎች ኬ ዋይን ይመርጣሉ።

ሲልከን–ነክ ሉብሪካንት

ሲልከን–ነክ ሉቦች ከውሃ–ነክ ሉቦች ጋር ይመሳሰላሉ። ነገር ግን በውፍረትና በቆዪነታቸው ይለያሉ—እነዚህን ሉቦች እንደ ውሃማ ሉቦች ደጋግመው መጠቀም አያስፈልጎትም። ሲልከን–ነክ ሉቦች ለመድረቅ ብዙ ጊዜ ይፈጅባቸዋል። በዚህም የተነሳ እንደ ውሃ-ነክ ሉቦች በቀላሉ አይጸዱም። ብዙ ጊዜ ሰዎች እነዚህን ሉቦች የሚጠቀሙት የፊንጢጣን ወሲብ ሲፈጽሙ ነው።

ታዋቂ ሲልከን–ነክ ሉቦች፦

ዌት ፕላቲነም (Wet Platinum)፦ ጥሩ ጥራት ያለውና ብዙ ጊዜ የሚቆይ ነው። ለፊንጢጣ ወሲብ (አናል ሴክስ) በጣም ይመቻል።

ኤሮስ ባዲግላይድ (Eros Bodyglide)፦ ከዌት ፕላቲነም ጋር ይመሳሰላል ግን በጣም ውድ ነው።

አይዲ ሚሌኒየም (ID Millennium)፦ ጥሩ ነው ግን እንደ ሁለቱ አይሆንም።

ዘይት–ነክ (ዘይታማ) ሉብሪካንት

ዘይታማ ሉቦችን ባይጠቀሙ ይመረጣል ምክንያቱም እላይ እንደተገለጸው ከኮንዶም ጋር ስለማይሄዱ። ለሴቶች ጤንነትም ጥሩ አይደሉም። በተጨማሪ፣ በጣም ጭምልቅልቅ ስለሚያደርጉ፣ የወሲባዊ ፍላጎትን ይቀንሳሉ። ቤቢ ኦይል፣ ቫዝሊን፣ ክሪስኮ፣ ወ.ዘ.ተ. በአለስላሽነታቸው ቢታወቁም ለወሲብ ግን ተመራጭ አይደሉም።

ከዘይታማ ሉብሪካንቶች መካከል ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ሜንስ ክሬም (Men’s Cream) የሚባለው ነው። ወንዶች ራሳቸውን በራሳቸው ሲያረኩ (ማስተርቤት ሲያደርጉ) እንዲጠቀሙት የተሰራ ሉብሪካንት ነው። በርግጥ ይሄ ቅባት በብዙ ወንዶች ዘንድ ተመራጭነት አለው። ከቫዝሊን፣ ከምራቅና ከሳሙና ያስንቃል።

እንግዲህ የሚመቻችሁን የሉብሪካንት ዓይነት መርጣችሁ፣ አሪፍ የወሲብ ጊዜ ታሳልፉ ዘንድ ምኞታችን ነው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.