ማረጥ

ማረጥ ሁሉንም ሴት በተለያየ መልኩ ይቀይራታል፡፡ ማረጥ የሚከሰተው አንድ ሴት እድሜዋ ገፍቶ ማሕፀኗ እንቁላል ማምረት ሲያቆምና የወር አበባዋን ማየት ስታቆም ነው፡፡ ለአብዛኛዎቹ ሴቶች ይህ ነገር የሚጀምረው ከ40 አመታቸው በኋላ ነው፡፡ ሲጀምርም የወር አበባው እንደተለመደው ቀኑን ጠብቆ መምጣት ያቆማል፡፡ ማረጥ ቀስ እያለም ሊመጣ ይችላል፤ በተመሳሳይ ጊዜም ድንገት በአንዴ ሊመጣ ይችላል፡፡

እንደ ማሕፀንን ማስወጣት (ሄስተሬክቶሚ) ያሉ አንዳንድ የቀዶ ጥገና ድርጊቶች የወር አበባን ስለሚያስቀሩ ማረጥን ያስከትላሉ፡፡ በማህፀን ላይ ያሉት የእንቁላል ከረጢቶችም በቀዶ ጥገና ከተወገዱ (ኡፎሬክቶሚ) የማረጥ ምልክቶች ወዲያው ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ በቀዶ ጥገና ምክንያት የሚመጣው ማረጥ የዕድሜ ገደብ የለውም፡፡

አንዳንድ የማረጥ ምልክቶች ምንድን ናቸው?ማረጥ ምንድን ነው

 • ግራ የተጋባ (ጊዜውን የማይጠብቅ) የወር አበባ
 • የሰውነት የመገጣጠሚያ አካላት ህመም
 • አንድ ነገር ላይ ሀሳብን የማሰባሰብ ወይም የማስታወስ ችግር
 • የወሲብ ፍላጎት መለወጥ
 • በጣም ማላብ
 • በድንገት መጥቶ የሚጠፋ ትኩሳት
 • ቶሎ ቶሎ ሽንት መምጣት
 • እንቅልፍ ሳይጨርሱ ቶሎ መነሳት
 • የብልት መድረቅ
 • የፀባይ መለወጥ
 • ቅዠት
 • ሌሊት በላብ መዋጥ
 • መነጫነጭ

የማረጥ ምልክቶችን እንዴት ይቆጣጠሯቸዋል?

 • በሐኪም በሚታዘዝ መድኃኒት (ክኒን፣ የብልት ቅባት፣ ሰውነት ውስጥ የሚቀበር መድሃኒት፣ ወይም ሌላ ተስማሚ ህክምና ሊሆን ይችላል፡፡)
 • እስትንፋስ፣ የጥንካሬ፣ የመወጣጠር ወይም ሌላ ዓይነት ስፖርትን ማዘውተር
 • አትክልትና ፍራፍሬ የበዛው ምግብ መመገብ፤ የአኩሪ አተር ውጤት የሆኑ ምግብና መጠጦችን ማዘውተርም ይመከራል፡፡
 • ከህክምና ባለሞያ ጋር መወያየትም በእራስዎ ላይ የሚደርሱ ለውጦችን እንዴት መቋቋም እንደሚችሉ ይረዳሉ

ethiopia.thebeehive

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.