secondary_syphilis_diagram1347745144492v  ጨብጥ

v  ኤች አይ ቪ

v  ቂጥኝ

v  ከርክር(ጥልቀት ያለእውና በጣም የሚያም የብልት ቁስል)

v  ባንቡሌ(እባጭ)

v  ክላሚድያ(እንደ ጨብጥ የብልት ፈሳሽ)

v  ትሪኮሞኒያሲስ(የብልት ፈሳሽ፣ ማሳከክ)

v  ዋርት(በብልት አካባቢ የሚወጣ ኪንታሮት)

v  ፓፒሎማ ቫይረስ

v ኸርፐስ(ዉሃ የቋጠረ የሚያሳክክ ብዛት ያለው የብልት ላይ ቁስል)

የአባላዘር በሽታዎች ዝርዝር ኔታዎችሁ

1 ጨብጥ

በሃገራችን በስፋት የተስፋፋና የሚታወቅ በወሲብ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ ነው። ዋና ዋና ምልክቶቹ የሚከተሉት ናቸው።

 • ሽንት በሚሸናበት ወቅት የማቃጠል ወይም የህመም ስሜት
 • ከብልት የሚወጣ መግል የቀላቀለ ወፍራም ፈሳሽ
 • የሽንት ቧንቧን በማጥበብ ወይም በመድፈን ሽንት እስከ መከልከል በወንዶች ላይ ሲታይ በሴቶች ላይ ደግሞ ከብልት የሚወጣ ተመሳሳይ ፈሳሽ ይኖራል።
 • በአብዛኛው በሴቶች ላይ በሽታው ምንም አይነት ምልክት አያሳይም። በዚህም ምክንያት በሽታው መኖሩ ሳይታወቅ ዉስብስብ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል። በተጨማሪም በሽታው የተዋልዶ  አካላትን ከውስጥ የሚያቆስል ስለሆነ በውጭ በኩል ምንም አይነት ቁስለት ላያሳይ ይችላል።

ህክምና ያልተደረገለት ጨብጥ በሴቶች ላይ የሚከተሉትን ጉዳቶች ያስከትላል።

F የማህጸን ቁስለትን፣ የወር አበባ መዛባትን

F ከእምብርት በታች ባለው የሆድ ክፍል የህመም ስሜት

F የማህጸን ቧንቧዎችን በማቁሰል መካንነትን፣ እንዲሁም ከማህጸን ውጭ የሆነ እርግዝናን ሊያስከትል ይችላል። በሽታው በወንዶች ላይም መካንነትን ሊያስከትል ይችላል።

F ከእናት ወደ ህጻን በወሊድ ጊዜ ስለሚተላለፍ የአይን በሽታና አይነ ስውርነትን በህጻኑ ላይ ሊያስከትል ይችላል።

በሽታው በተገቢው ጊዜ ህክምና ከተደረገለት ሙሉ በሙሉ ይድናል። ከበሽታው ለመዳን በጤና ባለሙያ  የሚታዘዘውን መድሃኒት በትክክል መውሰድ ያስፈልጋል። መድሃኒቱን ወስደው የበሽታው ምልክት ካልጠፋ ወደ ጤና ባለሙያው እንደገና በመሄድ ተጨማሪ ምርመራና ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል።

2 ቂጥኝ

ቂጥኝ እንደ ጨብጥ በወሲብ ግንኙነትየሚተላለፍ በሽታ ሲሆን በሽታው ካለበት ሰው ጋር በቀጥታ ንክኪ እንዲሁም ከእናት ወደ ጽንስም ይተላለፋል።

የበሽታው የመጀመሪያው ምልክት በብልትና በብልት አካባቢ አነስ ያለና የማያም ቁስል ሲሆን በአብዛኛው ይህ ምልክት የህመም ስሜት ስለሌለው በቸልታ ሊታለፍ ይችላል። ይህ ምልክት በራሱ ጊዜ ከጠፋ ከጥቂት ሳምንት በኋላ በተዋልዶ  አካላት ላይ የንፊፊት ማበጥ፣ የሚያሳክክ የሰውነት መንደብደብ በተለይ በእጅ፣ መዳፍ እና በውስጥ እግር ላይ፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የአጥንትና  የጡንቻ ህመም ያስከትላል። ከዚህ በኋላ በሽታው ለረዥም ጊዜ በሰውነት ውስጥ በመሰወር ዋና ዋና የሰውነት አካላትን ለምሳሌ እንደ ልብ፣ አንጎል፣…. ያሉትን በማጥቃት ለሞት ይዳርጋል። ስለዚህ የበሽታው ምልክት በመጀመሪያ  እንደታየ  ወዲያው ወደ ጤና  ድርጅት በመሄድ ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል። የቂጥኝ በሽታ ከእናት ወደ ልጅ በእርግዝና እና በወሊድ ጊዜ ይተላለፋል። ስለዚህም ነፍሰ ጡር ሴቶች በቅድመ ወሊድ ምርመራ ወቅት ለቂጥኝ  ምርመራ ሊያደርጉ ይገባል።

3 ክላሚድያ

የክላሚድያ በሽታ ምልክቶች ከጨብጥ በሽታ ምልክቶች ጋር ተመሳሳይነት አላቸው። ነገር ግን በአብዛኛው በሽታው የያዛቸው ሰወች ምልክቱን አያሳዩም። በሽታው ህክምና ከተደረገለት ይድናል። ነገር ግን ህክምና ያልተደረገለት የክላሚዲያ በሽታ በሴቶችም በወንዶችም ላይ መካንነትን ያስከትላል። የክላሚድያ በሽታ የማህጸንንና የሽንት ቧንቧን ያቆስላል። ለኤች አይ ቪም ያጋልጣል። ከእናት ወደ ጽንስም ይተላለፋል።

4 ከርክር

በብልት ላይ ጥልቀት ያለው በጣም የሚያም ቁስለት ያስከትላል። በሽታው ህክምና ከተደረገለት ይድናል። ህክምና ካልተደረገለት ቁስሉ እየሰፋ በመሄድ በብልት አካባቢ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።

5 ባምቡሌ

የባምቡሌ በሽታ በመጀመርያ በብልት ላይ ቁስለት በማስከተል ከዚያም ውሎ ሲያድር በግራና በቀኝ ንፊፊትን በማሳበጥ ከፍተኛ ህመም ያስከትላል።

6 የተዋልዶ አካላት ኪንታሮት(ዋርት) እና ፓፒሎማ ቫይረስ

በቫይረስ አማካኝነት በወሲብ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፉ በሽታዎች ሲሆኑ በተለይም ኪንታሮት በብልትና በሌሎች በተዋልዶ አካላት ላይ ህመም የሌለው ቁስል ያመጣል። ፓፒሎማ ቫይረስ የማህጸን በር ካንሰር ሊያስከትል ይችላል። ስለዚህም ወደ ጤና ድርጅት በመሄድ ምርመራና ተገቢውን የህክምና እርዳታ ማግኘት ያስፈልጋል።

በአጠቃላይ  የአባላዘር በሽታ የተለመዱ ምልክቶች

 • ሽንት በሚሸናበት ወቅት የማቃጠል ወይም የህመም ስሜት
 • ከብልት/ሽንት መሽኛ በኩል የሚወጣ መግል የቀላቀለ ፈሳሽ
 •  ሽንት ለመሽናት መከልከል
 • የብልት ላይ እብጠት፣ ቁስልና የማሳከክ ስሜት
 • በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የህመም ስሜት
 • ህመም ያለው የንፊፊት ማበጥ
 • የታችኛው የሆድ ክፍል የህመም ስሜት(ለሴቶች)
 • መጥፎ ሽታ ያለው ከሴት ብልት የሚወጣ ፈሳሽ
 • የወር አበባ መዛባት
 • የቆለጥ ማበጥና የህመም ስሜት
 • ደም የቀላቀለ ከወንድ ብልት የሚወጣ ፈሳሽ

ህክምና ያልተደረገላቸው የአባላዘር በሽታዎች የሚያስከትሏቸው የጤና ችግሮች

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.