ከሜዲካል ጋዜጣ የተወሰደ   marriage 

ትዳር ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ከአንዱ የህይወት ምዕራፍ ወደ ሌላ የህይወት ምዕራፍ የሚወስድ የህይወት መዘውር ነው ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ ትዳር በአለማዊውም ሆነ መንፈሳዊው ህወይት ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ አንድ ሰው ሊኖረው ከሚገባ ወሳኝ የህይወት ገፆች ውስጥ በጉልህ ሊኖር የሚገባው ነው፡፡ ሆኖም ባሁኑ ወቅት ትንሽ ገንዘብ ላጠራቅም፤ እድሜየ ገና ነው፤ ቤትና መኪና ልግዛ በሚል አጉል ፈሊጥ ትዳርን ሲሸሹት ይታያል፡፡ ይሁንና እንደባለሙያወቹ ገለፃ ከሆነ ትዳር የያዙ ሰዎች  ትዳር ካልያዙ ሰዎች በተሻለ ሁኔታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ብሎም የህይወት ክህሎትን ማዳበር እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡ አኛም አንድ ሰው ከትዳር ሊያገኛችው የሚችላቸውን ጥቅሞች ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው ዘቅርበናል፡፡

  1. ኢኮኖሚያዊ ጥቅም

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ያገቡ ሰዎች ካላገቡ ሰዎች በተሻል ሁኔታ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ማስመዝገብ እንደሚችሉ አሳይተዋል፡፡ እንደ ጥናቱ ገለፃ ከሆነ ያገቡ ሰዎች ከራሳቸው አልፈው ለሚስታቸውና ለልጃቸው ስለሚያስቡ እና ስሚጨነቁ ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ በመስራት በቂ ገንዘብ እንደሚያገኙ የተገለፀ ሲሆን በሌላ በኩል በትዳር ውስጥ ሚገኙ ሰወች ካላገቡ ሰወች በተሻለ ሁኔታ ገንዘባቸውን በአግባቡ የሚጠቀሙበት ሲሆን ያላገቡ ሰዎች ግን ያገኙትን ገንዘብ አላግባብ ስለሚያወጡት ኢኮኖሚያዊ እድገታቸውን ውስን መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡

  1. ህይወትን መካፈል

አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ የተለያዩ የደስታና የሀዘን ወቅቶች እንደሚያጋጥሙት እሙን ነው፡፡ በመሆኑም እርስዎ ያገቡ ከሆኑ በህይወትዎ ውስጥ የሚያጋጥምዎትን የተለያዩ ውጣ ውረዶች ከቤተሰቦት ጋር በማያቋርጥ ሁኔታና ትክክኛ ስሜትን በተጎናፀፈ መልኩ መካፈል ይችላሉ፡፡ ዳሩ ግን ያላገቡ ሰዎች በህይወታቸው የሚገጥሟቸውን የህይወት ገጠመኞች በተሟላና በማያቋርጥ መልኩ ስሜታቸውን ለመጋራት ብሎም ለመግለጥ ያላቸው ዕድል አናሳ ነው፡፡

  1. ጤናማ የወሲብ ሕይወት

ያገቡ ሰዎች ጤናማና የተረጋጋ የወሲብ ሕይወት ሲኖራቸው በተቃራኒው ያላገቡ ሰዎች ጤናማ ላልሆነና ላልተረጋጋ የወሲብ ሕይወት በከፍኛ ሁኔታ ተጋላጭ ናቸው፡፡ ይህም ዘርፈ ብዙ የጤና ችግር ማስከተሉ አይቀሬ ነው፡፡

  1. ልጆች በአግባቡ ለማሳደግ

ሰዎች በትዳር ውስጥም ሆነ ከትዳር ውጭ ሆነው ልጅ ሊወልዱ ይችላሉ፡፡ ሆኖም በትዳር ውስጥ የሚወለዱ ልጆች የእናትና አባት ፍቅር በአግባቡ አግኝተው ያድጋሉ፡፡

  1. በማህበረሰብ ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ያገቡ ሰዎች ካላገቡ ሰዎች የተሻለ የህይወት መንገድ እንዳላቸው ነው፡፡ ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ ያገቡ ሰዎች በማህበረሰብ ህግ እና የአኗኗር ዘይቤ ካላገቡት በተሻለ ሁኔታ መገዛትና ህጉን የሚያከብሩ ስለሆነ ነው፡፡  

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.