ከሊሊ ሞገስ

በሚኒሶታ በምትታተመው መዲና ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ 

ይህ የመሳሳም አይነት የምላስ ለምላስ ንክኪን ያካተተ በመሆኑ፣ በተወሰኑ የዓለም ክፍሎች የነፍሶች አሳሳም (soul kissing) በመባል ይጠራል፡፡ ይህንን ስያሜ ሊያገን የቻለበትም ምክንያት፡-

በዚህ መልኩ በምንሳሳምበት ወቅት የምላስ በአፍ፣ በትንፋሻችንና በምላሳችን አማካኝነት ነፍሶቻችን ንክኪ ይፈጥራሉ ተብሎ ይገመት ስለነበር ነው፡፡

ይህ የመሳሳም አይነት በአብዛኛው የዓለም ክፍል የሚወደድና በወጣቶች በጣም የሚዘወተር የፍቅር ጥበብ ነው፡፡ በዚህ የመሳሳም ጥበብ በምንሳሳምበት ወቅት የምላስ ሚና ከፍተኛን ደረጃ ይይዛል፡፡ በፍሬንች የመሳሳም ቆይታ ወቅት ሁለት ነገሮች ከፍተኛ ሚና ይኖራቸዋል፡፡ እነሱም ከንፈርና ምላስ ብቻ ናቸው፡፡

ይህ የመሳሳም አይነት ‹‹ፍሬንች›› ሊባል የቻለው የዚህን አይነት የአሳሳም ጥበብ በመጀመሪያ በመጠቀም ፍቅርን ይለዋወጡ የነበሩት ህዝቦች ፈረንሳውያን ናቸው ተብሎ ስለሚገመት ነው፡፡ ፈረንሳውያን ለረጅም ዘመን ነፃ የአስተሳሰብን መርህን ሲያራምዱ የነበሩ ህዝቦች ከመሆናቸውም በተጨማሪ በፍቅር ዘርፍ ስማቸው በቅድሚያ የሚጠራ፤ የፍቅር ጠበብቶችና የመሳሳም ጥበብንም በተመለከተ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ህዝቦች ናቸው፡፡

scale

ተግባራዊ ልምምድ

ከንፈራችሁን በመጠኑ ከፈት አድርጉና የጓደኛችሁን ከንፈር ከሳሟችኋቸው በኋላ ምላሳችሁን በመጠቀም ከሚከተሉት ጥበቦች መካከል በአንዱ መተወን ትችላላችሁ፡፡

በምላሳችሁ የጓደኛችሁን ምላስ በመግፋት ጓደኛችሁም ልክ እንደ እናንተ እንዲያደርጉ አመላክቷቸው፡፡

ስለዚህ የመሳሳም ስልት በአንድ ወቅት አንዲት የፈረንሳይ ፀሐፍት ስትቀኝ፡-

‹‹በዚህ አይነት መልኩ መቶ ጊዜም ሳመኝ

ኧረ ሺህ አድርገው፣ መቶ ሺም ድገመኝ

ኧረ የምን መቶ፣ ሚሊየኑም አይረባኝ

የገንዘቦች ክምር ቢሊዮን ከምትሰጠኝ

 አፈር ስሆንልህ አንዴ ፍሬንች ሳመኝ›› ነበር ያለችው፡፡ ቀጠል አድርጋም ስለ መሳሳም ስትናገር ‹‹አንድ ከሰዎች ነጥቀህ ለመውሰድ የማይቻልህ ነገር አለ፡፡ እርሱም ፍቅር የመስራት ብቃታቸውን ነው፡፡ በዚህ አለም ላይ ምንም አይነት ዝብርቅርቅ ሁኔታና ጥድፊያ የበዛበት ህይወት ቢኖርም ሰዎች መዋደዳቸውን፣ መሳሳማቸውንና መጋባታቸውን አያቆሙም፡፡ ስለዚህ ፍቅር በራሱ ቀጣይነትን የተላበሰ ዘላለማዊ ጥበብ እንዲሆን ስለሚቻለው የልባችንን አውጥተን መጠበብና ስለ ፍቅር ስንል መኖር ይገባናል›› ብላ ነበር፡፡

በፍሬንች ኪሲንግ ወቅት መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

ምላሳችሁንና ከንፈሮቻችሁን በመጠቀም የጓደኛችሁን ጥርሶች አቀማመጥ ለመረዳት ሞክሩ፡፡ ይህ ሁኔታም በምትሳሳሙበት ወቅት ሊከሰት የሚችለውን አላስፈላጊ የጥርስ ግጭት ለመከላከል ያስችላችኋል፡፡

በምትሳሳሙበት ወቅት የምትስማሙበትን ፍጥነትና እንቅስቃሴ በየጊዜው በመቀያየር የተለየ ስሜትን ለመፍጠር ሞክሩ፡፡ የተለያዩ የመሳሳም ስልቶችን የተቀላቀላችሁም በመሳሳም አስደሳች ቆይታን ለመፍጠር ሞክሩ፡፡

ዘና ይበሉ፡- ሰውነታችሁን ፈታ ማድረግና ከንፈሮቻችሁንም ዘና ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡ ይህ ሁኔታም የተሻለ የደስታ ስሜትን ለመፍጠር ይረዳችኋል፡፡ ይህ ሳይሆን ከቀረና ከንፈሮቻችሁ እጅግ ጠንካራ ከሆኑ ግን ለጓደኛችሁ ባዶ ስሜትን የሚፈጥር ስለሚሆን በተቻለ መጠን ቆይታችሁን ግዳጅ እንዳታስመስሉት መጣር ይኖርባችኋል፡፡

ከንፈሮችዎን ይክፈቱ፡-

ከንፈሮችዎን በመጠኑ ማለያየትና ልክ አየር ለመሳብ በምትሞክሩበት ወቅት የሚኖራቸውን አይነት ክፍተት መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

ተአምረኛ የመሳሳም ጥበብ ንጉስ ለመባል የሚያስችል ሰባት መሰረታዊ ነጥቦች፡-

1. ወደ መሳሳም መሰረታዊ ነጥቦች ስንመጣ መልካም የአፍ ጤንነት ትልቁን ቦታ ይይዛል፡፡ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ የጥርስ ንፅህናን ብቻ መጠበቅ መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል ዋናው ነጥብ ነው ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ ሆኖም መረሳት የሌለበት ሌላው ጉዳይ የምላሳችን ንፅህና ነው፡፡ የጥርስ ቡርሻችንን (ለስለስ ያለውን የጥርስ ቡሩሽ) እንደ ምላስ ቡሩሽ በመጠቀም ለመሳሳም ከመዘጋጀታችሁ በፊት ምላሳችሁን ማፅዳት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

2. በጣም የምትወዱትን/ዷትን ግለሰብ ለመሳም ባሰባችሁ ወይም በጣም በቀረባችሁ መጠን ሊያጋጥማችሁ የሚችለውን ከመጠን በላይ የደስታ ስሜት ልትቆጣጠሩ ይገባል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጓደኛችሁ በሰውነታቸው እንቅስቃሴ ሊነግሩዋችሁ የሚጥሩትን ሀሳብ ለመረዳት መሞከርም ይኖርባችኋል፡፡ መሳሳም፣ ምላስንና ከንፈርን መጠቀም ብቻ ማለት ያለመሆኑን መገንዘብና ከዚህ ዘለል ያለ ትርጉም ሊኖረው እንደሚችልም መረዳቱ ጠቃሚ ነጥብ ነው፡፡

3. ልክ ልትሳሳሙ ስትሉ በተለይም የመጀመሪያችሁ ከሆነ፣ የደስታና የጭንቀት ስሜት ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ እዚህ ጋር ማድረግ የሚኖርባችሁ ነገር ቢኖር ሁኔታዎችን አለማሰብና የፍቅረኛችሁን አይኖች ብቻ መመልከት ነው፡፡ ይህ ሁኔታም በራስ የመተማመን ስሜትን ይፈጥርላችኋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከጓደኛችሁ በኩል የሚፈጠረው ፈገግታ አስደሳች ብቻ ሳይሆን ጓደኛችሁ ለእናንተ ያላቸውን ጥልቅ ስሜት ስለሚያሳይ የበለጠ ድፍረትን ይጨምርላችኋል፡፡ እናንተም በተራችሁ ፈገግ በሉ፡፡

4. አሁን ትንፋሻችሁን እንኳን መስማማት እስክምትችሉበት ድረስ መቀራረብ የሚኖርባችሁ ወቅት ነው፡፡ ይህም የመሳሳም ሂደቱ መንደርደሪያ ነጥብ ላይ መድረሳችሁን ያመለክታል፡፡

5. በመጠኑ ወደ ፊት ታዘነብሉና ጓደኛችሁን አንድ ሁለት ጊዜ መደበኛ የሆነ የከንፈር ንክኪ የታከለበትን የመሳሳም አይነት ከሳማችኋቸው በኋላ ቀጥሎ ሁኔታዎችን ጠበቅና ከረር እያደረጋችሁ በሚመቻችሁ የአሳሳም አይነት መጠበብ ትችላላችሁ፡፡ በመሳሳም ቆይታችሁ ወቅት አይኖቻችሁን መክደን በሂደቱ መመሰጥን የሚያሳይ ስለሆነ አይኖቻችሁን ለመክደን ብትሞክሩ የተሻለ ነው፡፡ ሆኖም ይህንን ሁኔታ እንደ አንድ ህግ እንድትከተሉት ግን አትገደዱ፡፡ ይልቁንም የተመቻችሁን መከተሉ የእናንተ ምርጫ ይሆናል፡፡

6. በፍሬንች ኪሲንግ የአሳሳም አይነት ጓደኛህን ለመሳም በምትቀርብበት ወቅት ምላስሀን በመጠቀም የላይኛውን ከንፈሯን ከታችኛው በመለየት መሳምህን ቀጥል፡፡ ምላስህን ረጋ ባለ መልኩ በማንቀሳቀስና ወደ ጓደኛህ አፍ ውስጥ በመክተት ላይ በተጠቀሰው መልኩ መሳምም ትችላለህ፡፡

7. አሁን የከንፈር ንክኪን ተከትሎ የሚከሰተውን መጠነኛ የደስታ ስሜትን ካለፋችሁ በኋላ ምላሳችሁን በመጠቀም ወደምትተውኑበት ሂደት ላይ ደርሳችኋል፡፡ ምላሳችሁን በመጠቀም ከጓደኛችሁ ምላስ ጋር የተወሰኑ ቸዋታዎችን መጫወት ትችላላችሁ፡፡ ምላሳችሁን በጓደኛችሁ ምላስ ላይ በማዟዟርና በማሽከርከር መሳምዎን ይቀጥሉ፡፡ ሆኖም ከመጠን በላይ ፈጣንና ከመጠን በላይ ረጋ ያለ መሳሳም ሊፈጠር የሚችለው አስደሳች ስሜት ሊያጠፋው ስለሚችል ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መተግበር ይገባል፡፡

አንዳንድ ግለሰቦች በመጀመሪያ የመሳሳም ቆይታቸው ወቅት በዛ ያለ የምላስና የአፍ ንክኪ የታከለበት የኪሲንግ አይነት የሚያስደስታቸው መሆኑን ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ ስለሆነም ጓደኛችሁ ለመሳሳም ሒደቱ ጀማሪ ከሆኑ ትንሽ የፍሬንች ኪሲንግ ቆይታና ረዘም ያለ የመደበኛ መሳሳም ስልትን በመጠቀም ጥበቡን ማለማመድ ይችላሉ፡፡

በምትሳሳሙበት ወቅት ልትገብሩዋቸው የሚገቡ፡-

– ለመተንፈስ አፍንጫችሁን ተጠቀሙ፡፡

– ምራቃችሁን በመዋጥ በአፋችሁ ውስጥ በዛ ያለ የፈሳሽ ክምችት እንዳይኖር አድርጉ፡፡

– ከንፈሮቻችሁ መጠነኛ እርጥበትና ወዝ እንዲኖራቸው አድርጉ

– የፍርሃትን ስሜትን ያስወግዱ

ፍሬንች ኪሲንግ ለጀማሪዎች

ፍሬንች ኪሲንግ፣ ጨዋታ የተሞላበትና በወጣት ፍቅረኛሞች ዘንድ በብዛት የሚወደድ ፍቅርን የተላበሰ የመሳሳም ስልት ነው፡፡ በዚህ የመሳሳም ስልት ከጓደኛችሁ ጋር ለመሳሳም ከመሞከራችሁ በፊት ጓደኛችሁ በዚህ የመሳሳም ስልት ለመሳሳም መፈለግና ያለመፈጋቸውን ማረጋገጥ ይኖርባችኋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ ምላስዎን እጓደኛዎ አፍ ውስጥ ለማስገባት ይሞክሩ፡፡ ወይም ምላስዎን በጓደኛዎ አፍ ላይ ቀስ ብለው ያንሸራቱት፡፡ በዚህ ወቅት፡- ጓደኛዎ ለዚህ የኪሲንግ አይነት ዝግጁ ከሆኑ አፋቸውን በመክፈት ምላስዎን ወደ ውስጥ እንዲያስገቡ በማድረግ ለሂደቱ ያላቸውን ዝግጁነት ይገልፃሉ፡፡ በተቃራኒው ጓደኛዎ ወደ ኋላ ቢያፈገፍጉ መከፋት ወይም ማፈር አይኖርብዎትም፡፡ ይልቁንም በዚህ ስልት የመሳሳም ፍላጎቱ ከጓደኛዎ እስኪመጣ ድረስ መደበኛ የፍሬንች ኪሲንግ ስልቶችን እየተገበሩ መቆየት ይኖርብዎታል፡፡

በአይነትና በቴክኒክ የተለያዩ የፍሬንች ኪሲንግ አሳሳም ስልቶች የሚገኙ ሲሆን ወደ ፊት ዘርዘር ተደርገው የተቀመጡትን ጥበቦች በመጠቀም እነዚህኑ ስልቶች በሚፈልጉት ደረጃ መካን ይችላሉ፡፡

የምትሳሳሙበት የአሳሳም ስልት በጓደኛችሁ በኩል መወደድና አለመወደዱን ከሚያሳዩዋችሁ የተለያዩ ምልክቶች ማወቅ ትችላላችሁ፡፡ ለመጥቀስ ያህልም የምትሳሳሙበትን ግፊት ጠበቅ ካደረጉት ወይም በምትሳሳሙበት ወቅት የማቃሰት ድምፅ ካሰሙና በቆይታችሁ ላይ እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ሁኔታዎች ከታከሉበት ያለጥርጥር ፍቅረኛችሁ የመሳሳም ስልታችሁን ወደውታል ማለት ነው፡፡

የጓደኛችሁን የታችኛውን ከንፈር በምትመጡበት ወቅት የተለየ ድምፅ የሚያሰሙ ከሆነ፣ የአፋቸውን የተወሰነ ክፍል ለምሳሌ፡- ላንቃቸውን ወዘተ… በምላሳችሁ በመዳሰስ ጓደኛችሁ የተለየ ስሜት እንዲፈጠርባቸውና እንዲደሰቱ ለማድረግ ትችላላችሁ፡፡

በመጨረሻም የመጀመሪያ የፍሬንች ኪሲንግ ቆይታችሁን ብዙ ሰዎች በተሰበሰቡበት ወይም ቆይታችሁን ሊረብሹ የሚችሉ ነገሮች ባሉበት ቦታ ባታደርጉት ይመረጣል፡፡

እዚህ ጋር ማስታወስ የሚኖርባችሁ ነገር ቢኖርም ምንም እንኳን ፍሬንች ኪሲንግ በምላስና ከንፈር ላይ ብቻ ያተኮረ የመሳሳም ስልት ቢሆንም ይህንን የመሳሳም ጥበብ ተጠቅማችሁ በምትሳሳሙበት ወቅት እጃችሁ የሚኖረው ሚስጢራዊ ሚና የሚናቅ አለመሆኑን ነው፡፡

Source- Zehabesha.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.