የስኳር በሽታ

0

2.28_glucosetestየስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ኢንሱሊን የተባለውን ኬሚካል ሰውነታቸው በአግባቡ ማምረት ወይም መጠቀም አይችልም፡፡ ኢንሱሊን ማለት በሰውነታችን ውስጥ የሚገኝና ሰውነታችን የሚፈልገው የኬሚካል አይነት ነው:: ኢንሱሊን የሚጠቀመው ስኳርና ሌሎች ምግቦችን ወደ ግሉኮስ ለመቀየር ነው፡፡ ግሉኮስ ለሰውነታችን ሀይል በመስጠት ሰውነታችንን የሚያንቀሳቅስ ነው፡፡ በስኳር በሽታ ተጠቂ ከሆኑ ውስጥ 1/3ኛ የሚያህሉት በሽታው እንዳለበቻው አያውቁም፡፡ በደንብ ካልተከታተሉትና እንክብካቤ ካላደረጉለት የስኳር በሽታ አይነ ስውርነት፣ የልብ በሽታ፣ በቀላሉ የማይድኑ ቁስሎችንና የመሳሰሉት በሽታዎች ያስከትላል፡፡

ስኳር ያለባቸው ሰዎች የሚመገቡትን ምግብ በመቆጣጠር፣ የስኳር መጠናቸውን በየጊዜው በማወቅ፣ ክኒን/እንክብል በመውሰድና ኢንሱሊን በመውሰድ እራሳቸውን ይንከባከባሉ፡፡ ስኳር ካለቦት እራሶትን መጠበቅ አለቦት፡፡ ስኳሮትን በአግባቡ ከተቆጣጠሩ ጤናማ ሆነው ረጅም ሕይወት ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

ሁለት አይነት የስኳር በሽታዎች አሉ፡፡

ዓይነት 1: የዚህ በሽታ ተጠቂዎች በሽታው ከልጅነታቸው ጀምሮ የሚመጣባቸው ስለሆነ ማስወገድ አይችሉም፡፡ ሰውነታቸው በቂ ኢንሱሊን ስለማይሰራ ኢንሱሊን በየጊዜው መውሰድ አለባቸው፡፡

ዓይነት 2: የዚህ በሽታ ተጠቂዎች ደግሞ በአብዛኛው በዕድሜ የገፉ ሰዎች ናቸው፡፡ የሰውነታቸው ኢንሱሊን አጠቃቀም ያልተስተካከለ ስለሆነ እነዚህ ሰዎች አመጋገባቸውን መቆጣጠርና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ አለባቸው፡፡

ለስኳር በሽታ የተጋለጡ እነማን ናቸው?

ሐኪሞች “ዓይነት 1” ከምን እንደሚነሳና ወይም እንዴት እንደሚመጣ ስለማያውቁ ለዚህ ዓይነቱ የስኳር በሽታ የሚጋለጡት እነማን እንደሆኑ መገመት አይቻልም፡፡ ወላጆች የዚህ ዓይነቱን የስኳር በሽታ ምልክቶች በጥንቃቄ ማወቅ አለባቸው፤ ምክኒያቱም ልጆቻቸው ላይ ካዩ በፍጥነት ወደ ሃኪም መውሰድ እንዲችሉ፡፡

በ”ዓይነት 2″ የስኳር በሽታ በቀላሉ ሊያዙ የሚችሉት፡-

 • ዕድሚያቸው 55 ወይም ከዛ በላይ የሆኑ
 • ስኳር ያለበት የቅርብ ዘመድ (ወላጅ፣ ወንድም ወይም እህት) ያላችው
 • ወፍራም ሆነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማይሰሩ
 • ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ወይም ኮሌስትሮል ያለባቸው

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ሕፃናትና ወጣቶች “ዓይነት 2” የስኳር በሽታ ተጠቂ ሆነዋል። ይህም የሆነበት ምክኒያት ብዙ ስብ እና ስኳር ስለሚመገቡ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ/ስፖርት ስለማይሰሩ ነው። በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች ጤናማ የሆነ አኗኗር የስኳር በሽታን ለመከላከል ጠቃሚ ነው።

የስኳር በሽታ ምልክቶች፡-

“ዓይነት 1” የስኳር በሽታ ያለባቸው ሕፃናት የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ

 • በቀላሉ የማያልፍ የውሃ ጥም
 • ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት
 • ድካም
 • ከፍተኛ የሆነ ውፍፈት ወይም ክሳት
 • ማስመለስ

በአብዛኛው የ”ዓይነት 1″ ተጠቂዎች ስኳር እንዳለባቸው የሚታወቀው ከታመሙ በኋላ ስለሆነ ምልክቱን አይተው ወደ ሐኪም መውሰድ የወላጆች ሃላፊነት ነው፡፡

የ “ዓይነት 2” የስኳር በሽታ ምልክቶች

 • የማይጠፋ ከፍተኛ የሆነ የውሃ ጥም
 • ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት
 • ድካም
 • ማስመለስ
 • የዓይን መፍዘዝ/በጥራት አለማየት
 • የቀላል ቁስሎች ቶሎ አለመዳን

እነዚህ ምልክቶች በእርስዎ ወይም በሚወዱት ሰው ላይ ካዩ ሀኪም ያማክሩ፡፡ ስኳር በሽታ ሊታከም ይችላል፣ ነገር ግን ምልክቶቹን ከናቁ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ሊያስከትልብዎ ይችላል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.