ምትሀት የሚመስለው የ3ዲ መድሀኒት ማተሚያ በሁሉም ምዕራባውያን ቤት ውስጥ ሊገባ ጥቂት ወራት ብቻ ይቀረዋል፡፡

computer-generated-ኮምፒዩተሮች ድሮ ለፕሮግራም አዋቂዎችና ባለሞያዎች ብቻ ነበሩ፤ዛሬ ግን በየሁሉም ቤት ውስጥ መግባት ችለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም አጅብ የሚያሰኙ ግኝቶች ተፈጥረዋል፡፡ አዲሱ ግኝት የ3ዲ መድሀኒት ማተሚያ ተብሎ ይጠራል፡፡ በቤትዎ ሆነውም መድሀኒትዎን እሚያትሙበት እጅግ ዘመናዊ መሳሪያ ነው፡፡

 

ከእርስዎ የሚጠበቀው እቤትዎ የሚደርስ ኢንተርኔት እና አዲሱን ከፈረንጆቹ ግንቦት ወር በኋላ ለገበያ የሚቀርበውን የ3ዲ ማተሚያ ማሽን መግዛት ብቻ ነው፡፡ ከዛም የራስዎ ሀኪም ሆኑ ማለት ነው፡፡ እንዴት ይሆናል ብለውስ ጠየቁ? ነገሩ ወዲህ ነው፤ በእስኮትላንድ ግላስኮው ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ በ ሊ ክሮኒን የሚመራ የኬሚስትሪ ምሁራን የምርምር ቡድን ለመድሀኒት መቀመሚያ የሚሆኑ ኬሚካሎችን ቀመርና 2000 የአሜሪካን ዶላር የሚፈጅ የ3ዲ ማተሚያ ማሽን በመጠቀም አስገራሚ የሆነ ግኝት ፈጥረዋል፡፡

 

የ3ዲው ማተሚያ በቀላሉ የቤተሙከራ መድሀኒት መቀመሚያ እቃዎችን የሚተኩ ዘመናዊ እቃዎችን በውስጡ ይዞ ይገኛል፡፡ በሚታዘዝበትም ወቅት አስፈላጊውን የመድሀኒቶቹን ውህዶች ይቀምማል፤ በመጨረሻም የሚፈለገውን የኬሚካል ውህድ ፈጥሮ መድሀኒቱን ይሰራል ወይም በዘመነኛው የመሳሪያው አጠራርም መድሀኒቱን ያትማል ማለቱ ይቀላል፡፡      “ኬሚስትሪን ለሁሉም ሰው የማስተዋወቅ ያህል ይሆናል፤ኬሚስትሪ ያን ያህል ከባድ በማይሆንበት ሁኔታ ሰዎች የሳይንስ ፍሬዎችን እንዲጠቀሙ የማድረግ ያህል ነው፡፡” ይላል የግኝቱ ባለቤት ሊ ክሮኒን፡፡ በተለይ ሕክምና በቀላሉ የማይደርስበት አካባቢ ሰዎች የራሳቸውን የራስ ሕመም ክኒን ወይም ሌላ መድሀኒት በአፋጣኝ አዘጋጅተው ራሳቸውን ከድንገተኛ አደጋ እንዲታደጉ ሊረዳ እንደሚችልም ያምናል፡፡

 

መድሀኒትም መታተም ይችላል?

 

ቃሉን በቀጥታ ከፈረንጅኛው ወስደን “መታተም” ያልነው ምክንያት ስላለን ነው፡፡ ዋነኛው ምክንያት ማተሚያ መሳሪያው ያዘዝነውን የመድሀኒት አይነት ፎርሙላ ወይም ቀመር በሕትመት አይነት ዘዴ ያትማል ይህ ሕትመትም በብሉ ሬይ ቴክኖሎጂ አማካኝነት በማተሚያው በሚገኘው የኬሚካል መቀመሚያ ገንዳ መሰል እቃ ውስጥ መድሀኒቱን ያዘጋጃል፡፡ የሚዘጋጀውም ማሽኑ በተሰጠው ቀመር መመሪያ መሰረት ነው፡፡ ሕገወጥ የሆነ መድሀኒትምርትንም ለማስቀረት ተመራማሪቹ ዘዴ ፈይደንለታል ይላሉ መፍትሔውም ይህን ማሽን የገዛ ማንም ሰው የሚተመውን መድሀኒት ቀመር ዝርዝር መረጃ ሳይሆን ተሰርቶ ያለቀውን ቀመር ብቻ ከኢንተርኔት ዳውንሎድ በማድረግ ብቻ እንዲጠቀም ይደረጋል፡፡

 

ከኢንተርኔት ዳውንሎድ የሚደረጉ መድሀኒቶች?

 

የምንፈልገውን የመድሀኒት አይነት በ3ዲ መሳሪ በቤታችን ለማዘጋጀት ስንፈልግ የመድሀኒቶቹን አይነት በቀጥታ ከኢንተርኔት ዳውንሎድ ማድረግ ይጠበቅብናል ነገርግን ዳውንሎድ የምናረገው የመድሀኒቱን ቀመር እና ዝርዝር ሁኔታ የያዘ ሶፍትዌር ነው፡፡ ሶፍትዌሩ በ3ዲ ማተሚያ ውስጥ ሲጫን ማተሚያው በሶፍትዌሩ ትዕዛዝ ኬሚካሎችን በውስጡ በመቀመም ያዘጋጃል፡፡ ማሽኑ ኬሚካሎችን ለመቀመም የሚያስችለው የኬሚስትሪ የተሟሉ ዕቃዎችንም አካቷል፡፡ በእርግጥ አነስተኛ እ የአንድ ፎቶ ኮፒ ማሽንን የሚያክል ይዘትና ስፋት ቢኖረውም ልዩና ዘመናዊ የሆነ ስራዎቹን የሚቆጣጠሩበት ኮምፒዩተር ተገጥሞለታልም፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.