clean-ness_logo (1)የሰውነትና የልብስ ንጽህና አብረው የሚሄዱ ናቸው። አንዱን አጽድቶ ሌላው ከተተወ ለውጥ አያመጣም። በላብም ሆነ በምንበላው ምግብ አይነት ምክንያት ሰውነት ጠረን ይፈጥራል። ልብስም ቢሆን ለምሳሌ ላብ ከነካውና ለምግብ ቅመም ሽታ ከተጋለጠ የሚደብር ሽታ ይፈጥራል። እና አንድ ሰው አልቦት ገላውን ካልታጠበና ልብሱም ለላብም ሆነ ለምግብ ሽታ የተጋለጠ ከሆነ ሽታው አይጣል ነው። ይህ ሁኔታ የሁሉም ሃገር ዜጋ ላይ ቢታይም አብዣኛው ኢትዮጵያውያን ላይ ግን ይበዛል። በተለይ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች እንዳሉ ሆኖ ለምሳሌ ወደ ድግስ ቦታ የመጣ ሰው፤ ትንሽ ከተንቀሳቀሰ በኋላ አድስ ላብ ሲመጣበት የበለጠ ይቀረናል። ቤት ውስጥም ስለሚሆንና ትኩስ አየር ስለሚያንስ እንዳለ ቤቱን በቅርናት ይሞላዋል። በተለይ ሰው ከላይ ልብስ ብቻ በመልበስ የውስጥ ኮተቱን ቸፍኖ ከቆየ በኋላ በዳንስም ይሁን በሙቅት ምክንያት ድንገት የሚደብር ሽታ ላካባቢው ሲረጭ ጉድ ያሰኛል። ብዙውን ጊዜም ማን ደህና ማን ጥፋተኛ እንደሆነ መለየት ያስቸግራል። በተለይ ደግሞ የሌሎች ሃገር እንግዶች ካሉ እራስን ለውርደት ማጋለጥ ነው። በተለምዶ ደግሞ በህዝብ ማመላለሻ ለምሳሌ አውቶቡስ ውስጥ በአይን ሳያዩ በሽታ ብቻ አበሻ መኖሩን ማወቅ የሚቻልበት ወቅት ብዙ ነው። ይህ የሚፈጠረው የገላም ሆነ የልብስ ንጽህና በደንብ ሳይጠበቅ ሲቀር ነው።

ስለ አካል ንጽህና፤

ካላችን አልቦንም ሆነ ሳያልበን፣ ቅመም የበዛበት ምግብ በላንም አልበላን፤ ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ ገላችንን ካልታጠብን አካላችን የሆነ ሽታ ያፈልቃል። እኔ ሃኪም ስላልሆንኩ ይህ ሽታ እንዴትና ለምን እንደሚፈልቅ አላውቅም። ነገር ግን ሽታውን ለማጥፋት ወይም ለመቀነስ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት ባጭሩ አብራራለሁ። የተለየ የአካል ሽታ ችግር ያለበት ሰው ካለ ደግሞ ሌሎች መፍትሄወችን በራሱ መሻት አለበት። ባጠቃላይ ውኃና ሳሙና እስካለ ድረስ የገላ ንጽህናን መጠበቅ በጣም ቀላል ነው። የገላ ንጽህናን መጠበቅ ለጠረን ብቻ ሳይሆን ለጤንነትም ጭምር ይጠቅማል። ገላን ሲታጠቡ ሽቶ የሌለው ሳሙናና ከተቻለ ደግሞ ለምሳሌ የመታጠቢያ ጓንት መጠቀም ገላን በደንብ ያጸዳል። ብዙ ዝርዝር ውስጥ መግባት አያስፈልግም ግን አካላትን በሙሉና በተለይ ብብትና ብልትን በውኃና በሳሙና ደጋግሞ መታጠብ አስፈላጊ ነው። መታጠቢያ ውኃውም ከተቻለ በቀዝቃዛው ወይም ትንሽ ለብ ያለ ብቻ ቢሆን ይመረጣል። አንዳንድ ሰወች ግን መጎነፍ እንደሚወዱ ይኖራሉ።

ው ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ ገላውን መታጠብ አለበት። ሰው ቀኑን ባያልበው እንኳን በውኃ ብቻ መታጠብ ይችላል። ከዛም ገላን በፎጣ ካደረቁ በኃላ የመረጡትን የብብት ቅባት መቀባት። እዚህ ጋ ግን ውድም ይሁን ርካሽ፣ የብብቱ ቅባት ሽታው ከሩቅ ሰውን የማይጣራና ለራስ የሚስማማ ሆኖ የተመረጠ መሆን አለበት። ሰው የራሱ ምርጫ ቢሆንም የገላ ሽቶ ምናምን ኮተት ማብዛት ማጋነንና እራስን መደበቅ ስለሆነ በውኃና በሳሙና ብቻ ከታጠቡ በቂ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ሽቶ መጠቀም ይችላል። አንዳንድ ሰወች እንዲሁ ጥሎባቸው ሁልጊዜ ሽቶ ሽቶ ይሸታሉ። ብዙዎቹ ደግሞ ያደረጉት ሽቶ ሽታው ከመደበሩም አልፎ ሰላም ሲሉ አይን ውስጥ የሚገባ ወይም ጉንጭ ላይ የሚቀር ነው። አንድ ጊዜ እኔ አንዷን ያው በባህላችን መሰረት ሰላም ስል የጸጉሯ ሽቶ ግራ አይኔ ውስጥ ገባና አይኔን ጨፍኜ ኖሮ ሴትዮዋ የምጠብሳት መስሏት ስትደነግጥ አጋጥሞኛል። እኔም ይሉኝታ ይዞኝ “ይቅርታ ሽቶው ነው እንዲህ ያረገኝ” ሳልላት ቀረሁ። እሷም ይኸ ጉደኛ ድንገት ዛሬ ምነካው ብላ ይሆናል? እኔ እንጃ። ለማንኛውም ሴትዮዋን ሌላ ጊዜም አግኝቻት ስለነበር ሰላም ነው።

ስለ ልብስ ንጽህና፤

ላን በደንብ ከታጠቡ በኋላ ንጹህ ልብስ መልበስ ማለት ግሩምና የሚጥም ምግብ ሰርቶ ለምሳሌ በንጹህ ሳህንና በቅጡ የተዘጋጄ ጠርንጴዛ ላይ ማቅረብ እንደማለት ሆኖ ሊቆጠር ይችላል። ልብስ እንዴት እንደሚታጠብና እንደሚተኮስ ሰው በራሱ ያርገው እንጂ እኔ እዚህ አልጽፍም። ዋናው ነገር ግን ሰው ገላውን ከታጠበ በኋላ ሙሉ ለመሆን ንጹህ ልብስ መልበስ አለበት። እንደ ሱሪ-ግልገልና የውስጥ ካኒተራ ምናምን የመሳሰሉትን በየቀኑ ቢቀየሩ ይመረጣል። ሱሪና የላይ ልብሶች ግን በደንብ ተደጋግመው መለበስ ይችላሉ። አንዳንድ ሰዎች ልብስ ላይም ሽቶ የሚያደርጉ አሉ። በተለይ ልብስ ላይ ሽቶ ማድረግ በጣም የሚደብር ነው። የሰው ልጅ የዚህን ያክል አርቲፊሻል መሆን የለበትም። ልብስ በውኃና በልብስ ሳሙና እስከታጠበ ድረስ ሲለበስ ሽቶ ላዮ ላይ ማድረግ ሰወች የራሳቸው ምርጫ ቢሆንም ጥቅሙ አይታየኝም። ዋናው ነጥቤ ግን ሰወች ሽቶሽቶ መሽተት የለባቸውም ለማለት ነው። በተለምዶ ደግሞ ካጠገቡ ሽቶሽቶ የሚል ሰው እንዲቀርበው የማይፈልግ ሰው ብዙ ነው። ፍቅረኛሞችና ባልና ሚስት ከሆኑ ደግሞ ሌላ ታሪክ ነው። ለማንኛውም ሽቶ ገላን ለመታጠብም ሆነ ልብስን መቼ ማጠብ እንደሚቻል ስለሚሸውድ ጉዳት አለው።

ፍንጫ ብዙ ይነግራል። ሰው ገላው ምን ምን እንደሚል ለማወቅና ገላውን አሁን መታጠብ ካለበት የራሱን አፍንጫ ለምሳሌ ወደ ብብቱ ጎንበስ ብሎ እራሱን በማሽተት ማወቅ ይችላል። ልብስም ከመለበሱ በፊት ወደ አፍንጫ ጠጋ ካደረጉት የራሱ መልዕክት አለው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.