Demographic and Health Surveys Ethiopia 2005   የፆታና የተዋልዶ ጤና የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት መሆን ያለበት  ለምንድን ነው?1 የሰው ልጅ የተዋልዶ/ የመራቦ አካላት3 እርግዝናና ወሊድ6 የቤተሰብ ዕቅድ10 የእናቶች ጤና15 ኤች አይ ቪ/ ኤድስና ሌሎች የአባላዘር በሽታዎች20 የጽንስ ማቋረጥ26 የሴት ልጅ የወሲብ አካላትን መተልተል/ መቁረጥ31 አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች34 የፆታና ተዋልዶ ጤና ቃላት መፍቻ/ ትርጉም37

የፆታና የተዋልዶ ጤና የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት መሆን ያለበት  ለምንድን ነው?

የፆታና(Sexuality) ተዋልዶ ጤና ጤናማና ደህንነቱ የተጠበቀ ፆታዊ ግንኙነት፣እርግዝናን እንዲሁም ወሊድን አጠቃልሎ የሚይዝ ነው፡፡ የፆታና ተዋልዶ ጤና በሰዎች ኑሮ ውስጥ በጣም ድብቅ እና የግል ተብለው የሚታሰቡ፣ለመፃፍና በግልፅ ለማውራት የሚከብዱ ጉዳዮችን ያካትታል፡፡በዚህም ምክንያት አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ፆታንና ተዋልዶ ጤናን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖረው አድርጎታል፡፡በተጨማሪም ፆታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ባህላዊ ተፅዕኖናና ድብቅነት ህብረተሰቡን ስለጉዳዩ መረጃና አገልግሎት ከመፈለግ በመገደብ መንግስታትም አስቸኳይ መፍትሄ እንዳይሰጡ አድርጓቸዋል፡፡ ነገር ግን የፆታና ተዋልዶ ጉዳይ  ከአገሮች ማህበራዊና ኢኮኖሚ ዕድገት ጋር በእጅጉ የተያያዘ ነው፡፡ እናቶች በወሊድ ወቅት ሲሞቱ፤ልጆች ወላጅ አልባ ይሆናሉ፡፡ ሴቶችም ታናናሽ እህትና ወንድሞቻቸውን መንከባከብ ስለሚኖርባቸው ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ፡፡ ትምህርታቸውንም የማይከታተሉ ሴት ልጆች ያለዕድሜ ትዳር እንዲመሰርቱ ይገደዳሉ፡፡ይህም ጤናቸውን አደጋ ላይ ከመጣልም አልፎ በህብረተሰባቸውና በአገራቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ የሚኖራቸውን ተሳትፎ ይገድበዋል፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ፆታዊና የተዋልዶ ጤና ጉዳዮችን ትኩረት እንዲሰጣቸው ለማድረግ በሕብረተሰቡ ተሰሚነትና ተፅዕኖ ማሳደር የሚችሉ ግለሰቦችን ግንዛቤ በማዳበር የህብረተሰብ ጤና ፖሊሲው ላይ ግፊት እንዲያደርጉ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ እነዚህ ተደማጭነት ያላቸው ግለሰቦች መካከል  የመንግስት ባለስልጣናት እና ሰራተኞች፣መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መሪዎች፣የሴቶችና የሀይማኖት ማህበራት፣የትምህርትና የጤና ኤክስፐርቶች እንዲሁም ሌሎች  ተሰሚነት ያላቸው መሪዎችን ያካትታል፡፡ እነዚህ ተደማጭነት ያላቸው ግለሰቦች በየዕለቱ ጋዜጦችን፣ሬድዮንና ቴሌቪዥን ይከታተላሉ፤አመለካከታቸውም ከዚያ በሚያገኙት መረጃ ይቀረፃል፡፡  አልፎ አልፎ አንድ የዜና ዘገባ አንድን ውሳኔ ሰጪ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን ቀጣይነት ያለው ዘገባና የመረጃ ፍሰት  ለተለያዩ ተደራስያንን በፆታና ተዋልዶ ጉዳች ትምህርትና መረጃ ለመስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ መመሪያ የተካተቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ኢትዮጲያ፣ኬንያ፣ሩዋንዳ፣ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ ናቸው፡፡ ይህ መመሪያና በውስጡ የተካተቱት ለመረጃ ምንጭነት ያገለገሉ ሪፖርቶች በመረጃ መረብ ላይ ከሰኔ 12 2009 ጀምሮ ይገኛሉ፡፡ ስለፆታና ተዋልዶ ጤና ትክክለኛና ወቅታዊ ሪፖርቶችን የሚያቀርቡ ጋዜጠኞች፤

 • ድብቅ/ነውር ተብለው የሚታሰቡ ጉዳዮችን በግልፅ ለውይይት እንዲቀርቡ ያደርጋሉ፡፡
 • የመንግስታቸውን የጤና ዕቅድ አፈፃፀም ይከታተላሉ፤ የመንግስት ኃላፊዎች ያለባቸውን ተጠያቂነት ለሕዝብ ያሳውቃሉ፡፡

ይህ መመሪያ በኢትዮጲያ፣ኬንያ፣ሩዋንዳ፣ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ ላይ ያተኮሩ የቅርብ ጊዜ መረጃዎችን በማሰባሰብ ለጋዜጠኞች ህብረተሰቡንና ውሳኔ ሰጪዎችን በፆታና ተዋልዶ ጤና  ጉዳይ  ትምህርት እንዲሰጡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡   ራዕይ፡ የፆታና ተዋልዶ ጤና ለሁሉም በአለምአቀፍ ደረጃ የፆታና ተዋልዶ ጤና መብት  መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት መሆኑ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ ይህም በ1994 እ.ኤ.አ በተካሄደው አለማቀፉ የስነ-ህዝብና ልማት ኮንፈረንስ የፕሮግም እቅድ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡ ¾}ªMÊ Ö?“ TKƒ ከበሽታ ወይም ከህመም ነፃ መሆን ብቻ ሳይሆን የተዋልዶ ሥርዓት ተግባራትና ዕድገታዊ ሂደቶች ጋር የተዛመዱ ማንኛቸውም ጉዳዮችን በተመለከተ የተሟላ ›”L© ›°Ua›©“ TIu^© ÅI”’ƒ”“ Ö?“T’ƒ” ¾T>ÁSL¡ƒ ’¨<:: u²=IU SW[ƒ ¾}ªMÊ Ö?“ c­‹ ÅI”’~ ¾}Öuk“ Ö?“T ¨c=v© Ièƒ ”Ç=G<U ¾መዋለድ ’í’ƒ“ U`Ý ”Ç=•^†¨< ¾T>ÁÅ`Ó ’¨<::ልጅ የመውለድ   እና መቼ የሚለውን ለመወሰን እንደሚችሉም ያሳያል፡፡ በአለማቀፉ የስነ-ህዝብና ልማት ኮንፈረንስ ግለሰቦችም ሆነ ጥንዶች የልጆቻቸውን ቁጥርና መቼ መውለድ እንደሚፈልጉ እንዲወስኑ ህዝብ-ተኮር አቀራረብን አስተዋውቋል፡፡ሴቶችን ማብቃት ዋንኛ የዚህ አቀራረብ አካል ነው፡፡ በአለማቀፉ የስነ-ህዝብና ልማት ኮንፈረንስ ስምምነት ተዋልዶ ጤና ከሌሎች የሰዎች የኑሮ ሁኔታዎች ጋር ለምሳሌ ከኢኮኖሚ ፣የትምህርት ደረጃቸው፣የስራቸው አይነት፣የቤተሰባቸው መዋቅር እንዲሁም የሚኖሩበት የፖለቲካ፣የሃይማኖትና የህግ ስርአት ጋር  ቁርኝት እንዳለው አሳይቷል፡፡ ምንም እንኳ የተዋልዶ ጤና  የሰዎች የኑሮ ሁኔታዎች ጋር ይህን አይነት ቁርኝት ቢኖረውም እ.ኤ.አ በ 2000 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት በተካሄደው ስብስባ ከፀደቁት የመጀመሪያዎቹ ስምንቱ የምዕተ ዓመቱ ግቦች ውስጥ ግን አልተካተተም ነበር፡፡ከአምስት አመት በኋላ ግን የአለም መሪዎች ተዋልዶ ጤና የእናቶች ጤናን ለማሻሻል የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ያለውን ሚና በማመን የተዋልዶ ጤናን ለሁሉም በ2015 ለማዳረስ ቃል ገብተዋል፡፡

የሰው ልጅ የተዋልዶ/የመራቦ አካላት

የሴት የተዋልዶ/የመራቦ አካላት ውስጣዊ የተዋልዶ/የመራቦ አካላት

 • የእንቁላል እጢዎች የሚባሉት ጥንድ ትናንሽ የሆኑና የሴት እንቁላሎች የሚመረትባቸው አካላት ናቸው፤በየወሩም አንድ እንቁላል ይለቃሉ፡፡ይህም ሂደት ማኮረት ይባላል፣በአብዛኛው አንዲት ሴት የወር አበባ ማየት በጀመረች በ14 ቀናት ውስጥ ይከሰታል፡፡
 • የሴት ዘር እንቁላል ከወንድ ነባዘር/ስፐርም ጋር ወደሚገናኙበትና   ፅንስ ወደሚፈጠርበት የማህፀን ቧንቧዎች ይሄዳሉ እነዚህም የማህፀን ቧንቧዎች   የእንቁላል እጢዎችን ከማህጸን ጋር ያገናኛሉ፡፡
 • ከወንድ ነባዘር ጋር የተገናኘው እንቁላል  በማህጸን ውስጥ ሲተከል እርግዝና ይከሰታል፡፡ማህጸን ሾጣጣ ቅርፅ ያለው ከረጢት መሰል ከጡንቻ የተገነባና በእርግዝና ወቅት የሚያድገውን ፅንስ ለመያዝ የመለጠጥ ባህሪይ ያለው አካል ነው፡፡ ፅንሱ እድገቱን ሲጨርስ በወሊድ ጊዜ በማህፀን በር አድርጎ በሴት ብልት በኩል ይወጣል፡፡
 • የሴት ዘር እንቁላል ከወንድ ነባዘር ጋር ካልተዋሃደና ፅንስ ካልተፈጠረ፤በወር አበባ ወቅት እርግዝናን ለመቀበል የተዘጋጀው የማህጸን ግድግዳ ንጣፍና እንቁላሏ ከስመው በሴቷ ብልት በኩል በወር አበባ መልክ ወደ ውጪ ይፈሳል፡፡

ውጫዊ የተዋልዶ/የመራቦ አካላት

 • የላይኛው እና የታችኛው የሴት ብልት ከንፈሮች  የሴት ብልት መግቢያ በርንና የሽንት ቧንቧን የሚሸፍኑ ናቸው፡፡
 • ሁለቱ የታችኛው የብልት ከንፈሮች ቂንጥር ጋር ሲደርሱ ይገናኛሉ፡፡ ቂንጥር ከሚባለው ለወሲብ ስሜት ፈጣን ምላሽ የሚሰጥና በወሲብ ወቅት የሚቆም የሴት የተዋልዶ/መራቦ አካል  ነው፡፡
 • ድንግልና /ስስ  ሽፋን- የሴቶችን የብልት በር በከፊል የሚሸፍን ስስና ጠንካራ  ሽፋን ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ሲፈፅሙ ብዙ ግዜ የመቀደድና የመድማት ባህሪ አለው፡፡ይህም በብዙሃኑ ዘንድ የድንግልና ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ነገር ግን የደም ምልክት አለመኖር ሴቷ ከዚህ በፊት ወሲብ ለመፈፀሟ ማረጋገጫ አይሆንም፡፡ይህ ስስ  ሽፋን በአካላዊ እንቅስቃሴ ወቅት ሊቀደድ ይችላል፤አንዳንድ ሴቶች በተፈጥሮ ጭርሱኑ ይሄ ስስ  ሽፋን ላይኖራቸውም ይችላል፡፡

የወንድ የተዋልዶ/የመራቦ አካላት

 • የወንድ ብልት ስፖንጅ መሰል ጡንቻ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የሚቆም አካል ነው፡፡ የወንድ ብልት ጫፍ ለስላሳ በሆነና ብዙውን ጊዜ በግርዛት በሚወገድ ወሸላ በሚባል ቆዳ የተሸፈነ ነው፡፡
 • ለወሲብ ሲቀሰቀስ የወንድ ብልት ይቆማል፤የወሲብ እርካታ ላይ ሲደርስ ደግሞ የወንዱን የዘር ፍሬ/ነባ-ዘር የያዘ ፈሳሽ ይረጫል፡፡
 •  የቆለጥ ሽፋን ከወንዱ ብልት በስተጀርባ የተንጠለጠሉ የቆለጥ ፍሬዎችን የሚሸፍን የቆዳ ከረጢት ነው፡፡ ከረጢቱ የቆለጥ ፍሬዎችን፣ለወንዱ የዘር ፍሬ እድገት የሚያስፈልገውን ሙቀት የሚሰጡ የነርቭና የደም ቧንቧዎችን በውስጡ ይይዛል፡፡
 •  ቆለጥ (የነባዘር አመንጪ እጢ) ለወንድነት ባህሪ መከሰት አስተዋፅኦ የሚያደርግ ቴስቴስትሮን የተባለ አካላዊ ንጥረ-ቅመምና ነባዘር  የሚያመነጩ እጢዎች ናቸው፡፡ ብዙውን ግዜ ጤናማ ወንድ ሁለት የቆለጥ ፍሬዎች አሉት፡፡

ምንጭ

 • WebMD, in collaboration with the Cleveland Clinic. www.webmd.com
 • MedicineNet.com, www.medicinenet.com; and its online dictionary,
 • www.medterms.com

እርግዝናና ወሊድ

የወሊድ ምጣኔ ሁኔታ ከአንድ ሀገር ሌላ ሀገር ወይም ከአንድ ቦታ ሌላ ቦታ ይለያያል፡፡ጥናቶች እንደሚያሳዩት የቤተሰብ መጠን በሴቷ ትምህርት፣ ባላት የኑሮ ደረጃ፣ህብረተሰቡ ስለ ልጅ ያለው አመለካከት እንዲሁም በዘመናዊ የእርግዝና መከላከያ አገልግሎት/አቅርቦት  ይወሰናል፡፡ የወሊድ ምጣኔ ሁኔታና እድገት ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት ያሉ ሴቶች ከሌሎች አለማት ከሚገኙት ሴቶች ይልቅ በአማካኝ ብዙ ልጆች ይወልዳሉ፡፡ በክልሉ አጠቃላይ የወሊድ ምጣኔ ወይም ሴቷ በህይወት ዘመኗ የሚኖራት የልጆች ቁጥር በአማካኝ 5.4 ነው፡፡ ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው አማካኝ (2.6) ከእጥፍ በላይ ነው፡፡ በምስራቅ አፍሪካ ያለው ሁኔታም ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራት ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ዩጋንዳ ከፍተኛውን የወሊድ ምጣኔ በማስመዝገብ በምስራቅ አፍሪካ  ቀዳሚ ናት፡፡

ኢትዮጵያ(2005) 5.4
ኬንያ(2008) 4.6
ሩዋንዳ(2007) 5.5
ታንዛኒያ(2004) 5.7
ዩጋንዳ(2006) 6.7

አንዲት ሴት በሕይወት ዘመኗ የሚኖሯት የልጆች ብዛት በኢትጵያ፣ርዋንዳ፣ዩጋንዳ፣ኬንያና ታንዛንያ 1975-2008 ምንጭ:

UN Population Division, World Population Prospects: The 2008 Revision; and Demographic and Health Surveys (Ethiopia 2005, Kenya 2008- 2009, Rwanda 2007-2008, Tanzania 2004-2005, and Uganda 2006).

 • በሩዋንዳ፣በኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በቅርብ ባለፉት አሰርት አመታት ወዲህ አማካኝ የወሊድ ምጣኔ ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ ነው፡፡ በተለይም በሩዋንዳ ምጣኔው በጉልህ  መቀነሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
 • በኬንያ የወሊድ ምጣኔ ከ1970ዎቹ መጨረሻ እስከ 1990ዎቹ መጀመሪያ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም ከ1995-2005 ግን ለውጥ ሳያሳይ በነበረበት ደረጃ ቆይቶ በ2008 ግን ወደ 4.6 ወርዷል፡፡
 • በዩጋንዳ የወሊድ ምጣኔ ከ1970ዎቹ ጀምሮ እምብዛም የመቀነስ ሁኔታ ሳያሳይ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
 • በምስራቅ አፍሪካ የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ሊቀንስ የሚችለው ሀገራቱ  ያላቸውን የሕዝብ ቁጥር ሳይጨምር ባለበት መጠን ለመተካት የሚያስችል የወሊድ ምጣኔ ( በአማካኝ 2.1 ልጆች) ላይ ሲደርሱ ብቻ ነው ፡፡ እስከዚያ ግን ለሚቀጥሉት ብዙ አሰርት አመታት የአሁኑ ሕፃናትና ወጣቶች ወደ መውለጃ የእድሜ ክልል ስለሚገቡ ያለው የሕዝብ ቁጥር እድገት በለበት መልኩ በፍጥነት ማደጉን ይቀጥላል፡፡
 • ዛሬ በምስራቅ አፍሪካ ሃገራት 44% የሚሆነው ህዝብ ከ15 ዓመት ዕድሜ በታች ነው፡፡
 • የሕዝብ ቁጥር ትንበያዎች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ በ2008 809 ሚሊዮን የነበረው በአፍሪካ ከሰሃራ በታች የሚኖር ህዝብ እ.ኤ.አ በ2050 1.7 ቢሊዮን ይደርሳል፡፡ እዚህ ቁጥር ላይ ለመድረስ የወሊድ ምጣኔው በአማካኝ ወደ 2.5 ልጅ ዝቅ ሊል ይገባዋል፡፡ ነገር ግን  የወሊድ ምጣኔው በአማካኝ  ወደ 3 ልጅ ከቀነሰ የትንበያው ቁጥር ከ 2 ቢሊዮን ያልፋል፡፡
 • በአፍሪካና በአጠቃላይ በአለም ዙሪያ እንደሚታየው፣ የተማሩና ጥሩ ደረጃ ያሉ ሴቶች ዘግይተው ያገባሉ፣ዘግይተውም ልጅ ይወልዳሉ፤በተጨማሪም የትምህርት እድል ካላገኙ ደሃ ሴቶች ይልቅ በተሻለ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ይጠቀማሉ፡፡

ያልታቀደ/ያልተፈለገ እርግዝና

 • በምስራቅ አፍሪካ ከሚያጋጥሙት እርግዝናዎች ብዙ እጅ የሚሆኑት ያልተፈለጉ (ያልታቀዱ ወይንም ጭርሱኑ ያልተፈለጉ)ናቸው ፡፡

 

ኢትዮጵያ 35%
ኬንያ 45%
ሩዋንዳ 40%
ታንዛኒያ 24%
ዩጋንዳ 46%
 • በብዛት እንደሚታየው ያልተፈለጉ እርግዝናዎች የሚከሰቱት ዘመናዊ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን ባለመጠቀም ነው፡፡ አንዳንዴም ደግሞ የሚጠቀሙትን ዘዴ በአግባቡ ባለመጠቀም ወይም የእርግዝና መከላከያ ዘዴው እርግዝናን መከላከል ሲሳነው ነው፡፡
 • ያልታቀዱ እርግዝናዎች ከታቀዱት ይልቅ ብዙ የጤና እክሎች ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ከ18 ዓመት በታች ወይንም ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ፣በላይ በላይ የወለዱ ወይንም ብዙ ልጆች ያላቸው ሴቶች ለራሳቸውም ሆነ ለልጆቻቸው የበለጠ ለጤና ችግር ተጋላጭ ናቸው፡፡
 • ያልተፈለገ እርግዝና ሴቷን  ፅንሱን ወደ ማቋረጥ እንድታመራ ሊያደርጋት ይችላል፤ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት ደግሞ በአብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት በሕግ የተከለከለ ስለሆነ  ጥንቃቄ በጎደለውና ደህንነቱ ባልተጠበቀ መልኩ  ለሚካሄድ የፅንስ ማቋረጥ ሰለባ ያደርጋቸዋል፡፡

መካንነት

 • በአለማችን 10% የሚሆኑት ጥንዶች ልጅ ያለመውለድ/የመካንነት ችግር አለባቸው፡፡

 

 • ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት የሴቶችም ሆነ የወንዶች መሃንነት የሚከሰተው  በወቅቱ ሕክምና ባልተደረገለት እንደ ጨብጥና ሌሎች በግብረ-ስጋ ግንኙነት  በሚተላለፉ በሽታዎች ምክንያት ነው፡፡
 • ለመካንነት ብዙ ጊዜ ተጠያቂ ተደርገው የሚወሰዱት ሴቶች ናቸው፤ሆኖም ግን ወንዶች ግማሽ ያህል ለሚሆኑት በክልሉ  ለሚከሰተው መካንነት ምክንያቶች ናቸው፡፡

ምንጭ Demographic and Health Surveys: Ethiopia 2005, Kenya 2008-2009, Rwanda 2007-2008, Tanzania 2004-2005, and Uganda 2006 (Calverton, MD: ORC Macro, various years). www.measuredhs.com Carl Haub and Mary Mederios Kent, 2008 World Population Data Sheet (Washington, DC: Population Reference Bureau, 2008). www.prb.org/Publications/Datasheets/2008/2008wpds.aspx Rhonda Smith et al., Family Planning Saves Lives, 4th ed. (Washington, DC: Population Reference Bureau, 2009). www.prb.org/Reports/2009/fpsl.aspx Julie Solo, Family Planning in Rwanda: How a Taboo Topic Became Priority Number One (Washington, DC: Intra Health International, 2008). UN Population Division, World Population Prospects: The 2008 Revision (New York: UN Department of Social and Economic Affairs, Population Division, 2009). http://esa.un.org/unpp/ ለጋዜጠኞች ማስታወሻ

 • አንዲት ሴት በህይወት ዘመኗ የሚኖራት አማካኝ የልጆች ቁጥር በ “አጠቃላይ የወሊድ ምጣኔ ” ፋንታ “የወሊድ ምጣኔ” ብለን ልንገልፀው እንችላለን፡፡
 • የወሊድ ምጣኔ ስንገልፅ ቁጥሩን እንዳለ ከማስቀመጥ አጠጋግተን ሙሉ ቁጥሩን ብናስቀምጥ የተሻለ ነው፡፡ ለምሳሌ 5.4 የሆነን የወሊድ ምጣኔ ከአምስት ልጆች በላይ ወይንም 4.9 የሆነን የወሊድ ምጣኔ ወደ አምስት የሚጠጉ ልጆች በማለት መግለፅ እንችላለን፡፡
 • የወሊድ ምጣኔ በመቶኛ አይገለጽም፡፡
 • የአገሮችን የህዝብ ቁጥር ትንበያ ማወቅ ከፈለጋችሁ የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ክፍል ድህረ-ገጽን  http://esa.un.org.unpp ተመልከቱ
 • በተዋልዶ ጤናና በቤተሰብ ዕቅድ ዙሪያ ላላችሁ ጥያቄዎች የህክምና ባለሙያዎችንና በተለይም  የጽንስና የማህጸን ሃኪሞችን አማክሩ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.