(ሜዲካል ጋዜጣ)

በኢትዮጵያ 800,000 የሚሆኑ ሰዎች ለዓይነ-ስውርነት ተጋላጭ ሆነዋል!!

safe_image  ትራኮማ በኢትዮጵያ ለዓይነ-ስውርነት መንስኤበመሆን በሁለተኛነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የዓለም ጤና ድርጅት ጠቆመ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት አጋር ድርጅቶች ጋር በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ በኢትዮጵያ ከ138ሺህ በላይ ሰዎች በትራኮማ ሳቢያ ለዓይነ-ስውርነት እንደተዳረጉ ገልጧል፡፡ እ.ኤ.አ በ2020 ትራኮማን ከዓለማችን ለማጥፋት ያቀደው የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመላክተው ከሆነ፤ ኢትዮጵያ በትራኮማ በሽታ ስርጭት ከአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገሮች ካለው የትራኮማ በሽታ 30በመቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል፡፡ እንዲሁም ከ800,000 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውን በትራኮማ የተነሳ ለዓይነ-ስውርነት አደጋ የተጋለጡ እንደሆኑ መረጃው አስታውቋል፡፡

ትራኮማ በዓለማችን ዙርያ 1.3 ሚልየን ለሚደርሱ ዓይነ-ስውርነት መንስዔ እንደሆነ ያመለከተው የድርጅቱ መረጃ፤ በአብዛኛው ሴቶችና ህፃናት የበሽታው ተጠቂ መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 እና በ2006 በኢትዮጵያ በትራኮማ ላይ የተደረጉ ጥናቶች የእይታ መቀነስና በትራኮማ ሳቢያ የሚከሰት ዓይነ-ስውርነት የህብረተሰቡ ዋነኛ የጤና ችግር እንደሆኑ ያመላከቱ ነበሩ፡፡ 1.28 ሚሊየን ያህል ዜጎች ዓይነ-ስውር እንደሆኑና 2.5 ሚልየን የሚሆኑት ደግሞ አነስተኛ የማየት አቅም ያላቸው እንደሆኑም መረጃው ይፋ አድርጓል፡፡ እንዲሁም ከ9ሚልየን በላይ የሚሆኑት እድሜቸው ከ1-9 ዓመት የሚደርሱ ህፃናት በትራኮማ በሽታ ተጠቂ ናቸው፡፡

ትራኮማ (የአይን ማዝ) Chlamydia trakomatis እየተባለ በሚጠራ በሽታ አምጪ ባክቴሬያ ሳቢያ ሚከሰትና ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ ሊተላለፍ የሚችል በሽታ ነው፡፡ ባክቴርያው ከሰው ወደሰው ሊተላለፍባቸው ከሚችልባቸው መንገዶች መካከል ቀላል ንክኪ፣ በዝንቦች፣ በአይን ዳር ንክኪ ያላቸውን ነገሮች በመዋዋስ መጠቀምና እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በሽታው በአብዛኛው በድህነት ጋር የሚያይዝ በቂ ውሀ በሌለባቸው አካባቢወች በስፋት የሚታይ እንደሆነም ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.