በዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ (አዲስ ጉዳይ እንዳተመው)

soybean-መገኛው በሰሜን አሜሪካ እንደሆነ ቢነገርም ፈረንሳውያን በስፋት ጥቅም ላይ እንዳዋሉት ይታያሉ፡፡ በዋነኛነት የሾርባ ማጣፈጫ ነው ብለው ከፍተኛ የንጥረ ነገሮች ይዘት Great northem beans የሚባል የኮራ የደራ ስም አለው-ቦሎቄ፡፡ በተለይ በክረምት ወራት ተመራጭ ከሆኑ ምግቦች ዋነኛው የሆነው ሾርባ ያለ ቦሎቄ አይደምቅም ይባላል- ጣእሙንና ጥቅሙን በሚያውቁት ዘንድ፡፡ በስራና በህመም እንዲሁም በእረፍት ማጣት በድካም የተዋጡና ፈጣን ማገገምን የሚሹ ሰዎች ቦሎቄ የታለከለባቸውን ምግቦች እንዲመገቡ ይመከራል፡፡ ቦሎቄ ከሾርባ በተጨማሪ በዱቄት መልክ ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡

ቦሎቄ ዝቅተኛ ስብ፣ ዝቅተኛ ካሎሪና ምንም አይነት ኮሌስትሮል ካለመያዙም በላይ የአይረን፣ የፋይበር፣ የፖታሲየምና የፕሮቲን መገኛ ነው፡፡ እንደ ሃርቫርድ የጤና ትምህርት ቤት ከሆነ ቦሎቄን በስጋ ምትክ አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች በርካታ ህመም አይነቶችን ለመከላከል ይችላሉ፡፡

 አይረን 

አንድ ኩባያ የበሰለ ቦሎቄ 3.77 ሚሊ ግራም አይረን ይይዛል፡፡ ይህ አሃዝ ሴቶች ለእለታዊ ፍጆታ ከሚያስፈልጋቸው መጠን 21 ከመቶውን የሚሸፍን ሲሆን የወንዶቹን 17 ከመቶ ይሰጣል፡፡

ዝቅተኛ የአይረን ይዘት ያላቸውን ምግቦች መመገብ በደም ማነስ የመጠቃት እድልን ከመጨመሩም በላይ እንደ attention-deficit hyperactivity ላሉ የኒውሎጂካል ችግሮች ያጋልጣል፡፡

ፋይበር

በግማሽ ኩባያ የበሰለ ቦሎቄ ውስጥ በቀን ከሚያስፈልገን ፋይበር ውስጥ 24 ከመቶውን እናገኛለን፡፡ አሜሪካ የሚገኘው የአይዳሆ የባቄላ ነክ ምግቦች ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት ላይ በቦለቄ ውስጥ ከሚገኘው ፋይበር 3/4ኛ የሚሆነው በቀላሉ የማይሟሟው insoluble  የተሰኘው ነው ያለ ሲሆን ይህ አይነቱ ፋይበር የሆድን ጤንነት ይጠብቃል፣ በደንዳኔ ካንሰር የመጠቃት እድልንም ይቀንሳል ብሏል፡፡ የተቀረው 1/3ኛ ፋይበር soluble (በቀላሉ የሚዋሃድ) ሲሆን የስኳር በሽታንና ኮሌስትሮልን ይከላከላል፡፡ እንደ ቦሎቄ ያሉ በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር በልብ በሽታ፣ በቅጥ ያጣ ክብደት፣ በደም ግፊትና በልብ ድካም የመጠቃት እድልን ይቀንሳል፡፡

ፖታሲየም

አንድ ኩባያ የበሰለ ቦሎቄ 715 ሚሊ ግራም ፖታሲየም ይዟል፡፡ ይህም ከእለታዊ ፍጆታችን 20 ከመቶውን ይሸፍናል፡፡ ፖታሲየም እንደ ኤሌክትሮ ላይትና እንደሚኒራል የሚያገለግል በመሆኑ ተፈላጊዎቹን ኢንዛይሞች በማነቃቃት ጡንቻዎች እንዲንቀሳቀሱና ኃይል እንዲያመነጩ የማድረግ ብቃት አለው፡፡ የፖታሲየም እጥረት ካለብዎ ለአጥንት መሳሳት፣ ለኩላሊት ጠጠር፣ ለልብ ድካምና ለከፍተኛ የደም ግፊት የመጋለጥ እድልዎ ከፍ ያለ ነው፡፡ ከሰውነታችን ስራዎች አንዱ የፖታሲየምና የሶድየም መጠንን ማመጣጠን ዋነኛ ነው፡፡ ምግብዎ ጨው የሚበዛበት ከሆነ ለፖታሲየም እጥረት ሊያጋልጥዎ ይችላል፡፡

ፕሮቲን

ከቦሎቄ ክብደት ሩብ ያህሉ ፕሮቲን ነው፡፡ ከአንድ ኩባያ የበሰለ ቦሎቄ 15.2 ግራም ፕሮቲን ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ በ2006 ‹‹the new England of medicine›› በተሰኘ የህክምና ጆርናል ላይ ለንባብ የበቃ አንድ ጥናት ሰውነታቸው የሚያስፈልገውን ፕሮቲን ከተክሎች የሚያገኙ ሴቶች በልብ በሽታ የመጠቃት እድላቸው ዝቅተኛ እንደሆነ ፅፏል፡፡

በ2008 ‹‹the American journal of clinical nutrition›› ላይ የወጣ ሌላ ጥናት ደግሞ በርከት ያለ የተክል ፕሮቲን የሚወስዱ ሴቶች በስኳር በሽታ የመጠቃት እድላቸው ዝቅተኛ ነው ብሏል፡፡ እንደ ቦሎቄ ያሉ የባቄላ ዝርያዎች ምንም አይነት አሚኖ አሲድ የማይዙ በመሆናቸው ማእድዎ ላይ ጥራጥሬ ማካተት ተገቢ ይሆናል፡፡

የቦሎቄ ሌሎች ጠቀሜታዎች  

የአሜሪካ የባቄላ ካውንስል ቦሎቄ በርካታ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይዟል ይላል፡፡ ከተክሎች የሚገኝ ፕሮቲን፣ አይረን፣ ምግኒዝየም፣ ዚንክ፣ ፎሊክ አሲድና ካልሲየም ሰብሰብ ብለው ቦሎቄ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በተለይ ነብሰጡር እናቶች ፎሊክ አሲድ የበዛበት ማእድ ማዘውተር እንዳለባቸው የሚመክረው ፎሊክ አሲድ ህፃኑ ጤናማ ሆኖ እንዲወለድ ስለሚደርግ ነው፡፡ ወተት የማይስማማቸው ሰዎችም ቦሎቄን አዘውትረው በመመገብ ለአጥንትና ጥርስ ጥንካሬ አለኝታ ሆነውን ካልሲየም በበቂ መጠን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የስነ-ምግብ ይዘቱ    

በአሜሪካ የስነ ምግብ ምደደባ መሰረት ቦሎቄ ሁለት ምድቦች ውስጥ ይገባል፡፡ በተፈጥሮ ከተክሎች ጋር ሲመደብ፣ አይረንና ዚንክን በመያዙ የተነሳ ደግሞ ከስጋ ምድብ እንዲገባ ተደርጓል፡፡

ማሳሰቢያ  

ቦሎቄ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የሆድ ህመምና የምግብ አለመስማማትና በሆድ አካባቢ ምቾት የማጣት ሁኔታን ሊፈጥር ስለሚችል ወደ ማእዳችን ስናካትተው በጥድፊያ ሳይሆን ቀስ በቀስ መሆን እንዳለበት የምግብ አበሳሰል መፅሃፎች ደራሲ የሆኑት ማርክ ቢትማን ያስረዳሉ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.