ከስትሮክ አደጋ ራስዎን የሚጠብቁባቸው 5 ምርጥ መላዎች!!!

ማኅደረ ጤና
አዲስ አበባ

images-periodontal-heart-disease-stroke-1ሳይንቲስቶች  በተለያዩ  ጊዜያት ምርምሮችን ሲደርጉ ቢቆዩም በርካታ ሰዎች በተሩቅ ለሚፈሩትና በጭንቅላት ውስጥ የደም መፍሰስ ወይም ኦክስጂን አቅርቦት መቋረጥን በማጣት የህመምና ሞት እንዲሁም አካል ጉዳተኝነት ለሚዳርገው ስትሮክ ህመም ግን መቶ በመቶ ውጤታማ ህክምና ማግኘት ቀላል ሆኖ አልተገኘም፡፡ አሁን ላይ ታድያ ባለሙያዎቹ መከላከሉ ላይ እንዲሁም ስትሮክ ቢከሰት ውጤታማ ሆነው የሚቋቋሙበትን መንገድ እየተመለከቱ ይገኛሉ፡፡ በቅርቡ በወጡት አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ካርዲዮሎጂ ጆርናል፣ በኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦፍ ሜድስን እና ስትሮክ ጆርናል እትሞች ላይ ከህይወት ዘዬ ልምዶች ላይ የሚደረጉ ለውጦች አዳዲሶቹ ከስትሮክ ጥቃት መጠበቂያ ስትራቴጂዎች ሆነው ቀርበዋል፡፡

 ተፈጥሯዊውን ደም ማቅጠኛ ውሃ ይውሰዱ!

        ውሃ ደምን በከፍተኛ ሁኔታ የማቅጠን ብቃት አለው፡፡ ደም በቀጠነ መጠን ደግሞ የመወፈርና የመርጋት ጠባዩ በእጅጉ ይወርዳል፡፡ ጭንቅላት ውስጥ በመርጋት የህዋሳትን ስራ የማደናቀፍ አቅሙ ይቀንሳል፡፡ የአሜሪካው ሎማሊንዳ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች በቅርቡ ባወጡት ጥናት በየእለቱ ስምንት ብርጭቆ ውሃን የጠጡ የጥናቱ ተሳታፊዎች ከሶስት ብርጭቆ ውሃ ከጠጡት በ53 በመቶ የስትሮክ ተጋላጭነታቸው ቀንሶ ተገኝቷል፡፡

የጨውን ነገር ያስቡበት!    

ጨው የደም ግፊት በመጨመሩ ይታወቃል፡፡ ከፍተኛ የደም ግፊት አለ ማለት ደግሞ በሆነ ጊዜ ስትሮክ የሚከሰትበት እድል ይጨምራል ማለት ነው፡፡ ጨውን ከምግብ ውስጥ መቀነስ በደም ግፊትና በስትሮክ የመጠቃት አጋጣሚን ይቀንሳል፡፡ ጥናቶቹ እንደሚያመለክቱት ቸውን መቆጣጠር የስትሮክ ጥቃትን የመቋቋም እድልመን እስከ 14በመቶ ይጨምራል፡፡

ከዓሣ ጋር ወዳጅነትን ይመስርቱ!

በኢትዮጵያ በአብዛኛው ዓሣ የሚበላው በፆም ወቅት በመሆኑ ከዓሳ የሩቅ ምስራቅ ሰዎች ያገኟቸውን ጥቅሞች እንዳንጋራ ምክንያት ሳይሆን አልቀረም፡፡ የስትሮክን ነገር ያጠኑ ባለሙያዎች የዓሣን ጉዳይም አብረው አጥንተዋል፡፡ በጥናታቸው መሰረት ለስትረሮክ መከላከል ዋነኛ ስልት የሆነውን የደምን መወፈርና መርጋት ለመቀነስ ተግባር ዓሣ አስተዋጽዎው ላቅ ያለ ነው፡፡ በዓሣ ውስጥ የሚገኙት ኦሜጋ3 ፋቲ አሲድ ንጥረ ነገሮች የኮሌስትሮልን መጠን ለመቀነስና ደም ጭንቅላትን ጨምሮ ወደተፈለጉት አካላት ያለእገዳ እንዲደርስ ያመቻቻሉ፡፡

እንቅስቃሴ መድኃኒት ሲሆን!

ኤሮቢክስ እንቅስቃሴ ፀረ-ስትሮክ መድኃኒት ነው፡፡ መሮጥና የሶምሶማ እርምጃ ካልሆነሎትም የክብደት እንቅስቃሴ ውስጥ ይግቡ፡፡ የትኛውም አይነት እንቅስቃሴ ቢሆን የደም ግፊትን ለመቀነስና የኮሌስትሮልን ምጣኔ በመቀነስ በስትሮክ የመጠቃትን አጋጣሚ በእጅጉ ስለሚቀንስ የሚችሉትን ያህል እንዲንቀሳቀሱ ከጥናቶቹ የተገኙት ውጤቶች ይመክራሉ፡፡

አጫሽ ዋዳጅዎ በስትሮክ ይገድልዎታል!

ሲጋራ ማጨስ ከስትሮክ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ቀድሞም ይታወቃልና ሲጋራ አያጭሱ፡፡ በአዲሱ ጥናት ግን የራስዎ ብቻ ሳይሆን በአካባቢዎ ሚጨስ ሲጋራ ጭስም ለስትረሮክ የማጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ በኦክላንድ ንቨርስቲ ተመራማሪዎች ተሰራው ጥናት እንደሚለው የሲጋራ ጭስ በቀጥታ የሚጋለጡ ሰዎች ካልተጋለጡት አንፃር ለስትሮክ ያላቸው ተጋላጭነት በ82በመቶ ከፍ ብሎ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም አለማጨስ ብቻ ሳይሆን ሲጋራ በብዛት ከሚጨስበት ቦታም ራስዎን ያርቁ ነው የባለሙዎቹ መልእክት፡፡

ከህክምና ይልቅ ቅድመ-ጥንቃቄ እና መከላከሉ አዲሱ ስትሮክ ህክምና ስትራቴጂ እንደሆነ ጥናቶቹ ዕያመለከቱ ነው፡፡ ከውቴቶቹ በመነሳት ተሰጡት ምክሮችም በልምምድ ውጤት የሚያመጡና ቀላል ስትራቴጂዎች መሆናቸውም እየተወሳ ነው፡፡ በጥቂቱ የጨለፍናቸው ስትራቴጂዎች በብዙ ቢተገበሩ ውጤታማነታቸው የበዛ ይሆናል!!

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.