በእርግዝና ወቅት የሚወሰድ መጠነኛ የሆነ የአልኮን በተፀነሰው ህጻን ላይ ተጽዕኖ እንደሚፈጥር ተገለጸ

381671-29222-53በእርግዝና   ላይ  ያሉ  ሴቶች   በሳምንት  አንድ   ወይም  ሁለት   ብርጭቆ   ወይን  በሚወስዱበት  ጊዜ   በሚወለድው   ህጻን   የአዕምዕሮ  ዕድገት  ላይ ተፅዕኖ  መፍጠር  እንደሚችል   አንድ  ጥናት  ጠቆመ ፡፡ 
ከኦክስፎርድና ከብሪስቶል  ዩኒቨርስቲዎች   የተውጣጡ    ተመራማሪዎች  ባደረጉት  ጥናት   የ4ሺ ህፃናት  የአዕምሮ  ልቀትን   በመለካትና   እናቶቻቸው   በእርግዝና ወቅት ምንያህል  የአልኮን  መጠን  እንደወሰዱ  በመመዝገብ  የምርምር  ውጤቱ  እንደተገኘ  ተገልጿል ፡፡   
በጥናቱ    ግኝት  መሠረት በሳምንት   ከ1 እስከ  6   ብርጭቆ  አልኮን  መውስድ   በመጠናኛ   ደረጃ   የአልኮን  አወሳሰድ  ሲሆን  በእርግዝና   ወቅት  ያሉትን  ህጻናት የአዕምዕሮ  ልቀትና  እድገት ላይ  ተፅዕኖ  እንደሚያመጣ  በጥናቱ   ተረጋግጧል ፡፡  
ኤክስፐርቶቹ እንደሚናገሩት አልኮንን መውሰድ የሚያስድረው ተፅዕኖው ትንሽ ቢመስልም የጥናቱ  ውጤት በእርግዝና ወቅት የትኛውዋም ሴት አልኮንን እንዳትወሰድ የሚያስገድድ ነው  ብለዋል ፡፡ 
ከዚህ ቀደም የተሰሩት ጥናቶች ከአነስተኛ  አስከ  መካከለኛ  ደረጃ   አልኮንን   መውሰድ   ምን  ያህል  በእርግዝና  ላይ  ያሉ ሴቶችን እንደሚጎዳ  ተለዋዋጭና  አሻሚ  የጥናት  ውጤቶች   ሲሠራጩ  የቆዩ  ሲሆን   በእርግዝና  ላይ  ያሉት  ሴቶች     በምን  እድሜና የትምህርት  ደረጃ ላይ  እንደሆኑ  የሚጠቁሙ  ነገሮች  በጥናቶቹ  ባለመካተታቸው   ምክንያት   ሌሎች    ሁኔታዎችን በጥናቶች ውስጥ  ከግምት  ወስጥ  አልገቡም ፡፡

ፕሎስ  በተባለ  አንድ  ጆርናል ላይ  የታተመ ጥናት  እንዳመለከተው   በሰዎች  መካከል   ባለው  የዘረ መል  ልዩነት  ምክንያት  በማህበራዊና የአኗኗር  ዘይቤ  የሚመጡት   ተፅዕኖዎችም  ልዩነት  እንደሌላቸው   ገልጿል ፡፡  
በጥናቱ መሠረት አራት አይነት   የሰው  የዘር  መል አይነቶችን  በመውሰድ    አልኮን  ምን  ያህል  በእናቶችና  በህጻናት  ላይ   ተፅዕኖ   እንደሚያሳድር   በማጥናት በህጻኑ  ወይም ህጻኗ 8 አመት ላይ የአዕምሮ   ልቀት ተፅዕኖ  እንደሚፈጥር  ለማየት  ተችሏል ፡፡  
በአጠቃላይ በውጤቱም  በእርግዝና ወቅት  ከአንድ እስከ  ስድስት  ብርጭቆ  አልኮን  የሚወስዱ  እናቶች  የልጆቻቸው    የአዕምሮ  የልቅት  መጠን  ከማይውስዱት  አንጻር  ሲታይ   ቀንሶ  ተገኝቷል ፡፡
የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና የጥናቱ መሪ  ዶክተር ሮን ግሬይ እንደሚገልጹት  በጥናቱ  እንደሚታየው   በህጻናት  መካከል የሚታየው የአምዕሮ ልቀት ልዩነት  ትንሽ  መስሎ  ቢታይም   የአዕምሮ ልቀት ባነሰ  ቁጥር  የማህበራዊ ህይወት መዛባት ፤   የጤና ሁኔታ  መስተጓጎልና  ያለዕድሜ  ከመሞት ጋር ይየያዛል፡፡       
በእርግዝና ወቅት አልኮን የመውሰድ ጉዳይ የሴቶቹ ውሳኔ  እንደሆነ  የገለጹት  ዶክተር  ሮን ግሬይ የህክምና ባለሙያዎች መረጃውን  ከማቅረብም   በላይ  ሴቶች  በእርግዝና   ወቅት   አልኮን   እንዳይወስዱ  ይመክራሉ ፡፡    
በማንቸስተር  ከተማ  የሴንት  ሜሪ  ሆስፒታል  የእናቶች  ወሊድና የህጻናት ሞት   አማካሪ የሆኑት ዶክተር ካርሌ ታወር  በበኩላቸው   እንደሚገልጹት  በእርግዝና ወቅት  አልፎ  አልፎ  አልኮን  የሚወስዱትን  እናቶች  በዚህ  የጥናት   ወጤት    መደንገጥ  የለባቸውም  ይላሉ ፡፡ 
እንደ  ዶክተር  ካርሌ  ታወር  አባባል  በአሁኑ ወቅት   በእንግሊዝ  የሚሰጠው  ምክር   በእርግዝና  ላይ  ያሉ  እናቶች  አልኮን   ከመውሰድ   እንዲታቀቡ   ሲሆን   የጥናቱም  ውጤትም  ያለምንም  ቅድመ  ሁኔታ  የሚደግፈው   መሆኑን   በመግለጽ   ሆኖም    አንድ በቅርብ የወጣ  ጥናት በአምስት  አመት  ጊዜ ወሰጥ የሚወሰድ  አልኮን  በተረገዘው ልጅ ላይ ምንም  አይነት  የአይምሮ  ልቀት  ተፅዕኖ   አያመጣም የሚል ቢሆንም  ጉዳቱ  አነሰም  በዛም  በሁሉም  ሴቶች እኩል ተፅዕኖ  ባያመጣም  እንኳን  መጠንቀቅ  ያሻል  ብለዋል ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.