የአልኮ መጠጦችን ከመጠን በላይ አዘውትሮ መውሰድ  ለብዙ  ፈውስ ለሌላቸው  በሽታዎች አንደሚያጋልጥ በተመራማሪዎች ተረጋግጧል፡፡

alcoholየኦክስፎርድ ዩኒቨርሰቲ ከሰሞኑ ባወጣው ሪፖርት ወንዶች በቀን  ከሶስትና አራት ጠርሙስ  በላይ  መጠጥ መውሰድ  የለባቸውም። ሴቶችም  ቢሆኑ በቀን  ከሁለትና ሶስት ጠርሙስ በላይ እንዳይወስዱ ይመከራል ፡፡

ከአልኮ ጋር በተያያዘ ለሚፈጠር ችግር እንግሊዝ 3.3 ቢሊዮን ፓውንድ ያህል ገንዘብ በየአመቱ ወጪ እንደምታደርግ ይገመታል ፡፡

የኦክሰፎርድ አጥኚ ቡደን ከአጠቃላይ  የቤተሰብ ዳሰሳ ጥናት በመነሳት በእንግሊዝ  በ15ሺ  አዋቂዎች   በሳምንት  የሚወስዱትን  የመጠጥ መጠን  የሚያሳዩ  መረጃዎቸን  ሰብስቧል ፡፡ አጥኚዎቹ  አልኮን  ለረጅም ጊዜ  በመወሰድ  በሚከሰቱ  11 አይነት ህመሞች ምክንያት ለሞት  የተዳረጉትን  ሰዎች ለማጥናትም የሂሳብ ሞዴል  ተጠቅሟል።

የእንግሊዝ የህክምና ጆርናል  ሪፖርት እንደሚያሳየው አልኮል  ከመወሰድ ጋር ተያያዠነት ያላቸው በሽታዎች የልብ ህመም ፤ የልብ ውጋት ፤ የደም ግፊት ፤ የስኳር ፤ የጉበት ፤ የሚጥል በሽታና አምስት የተለያዩ የካንሰር  በሽታዎች  እንደሆኑ በጥናቱ አካቷል ፡፡

እንደ ጥናቱ ከሆነ በእንግሊዝ በየቀኑ ከሚወሰደውን የአልኮ መጠን ግማሹን ያህል በመቀነስ በአመት 4 ሺ 600 ያህል ሰዎችን   ከሞት መታደግ ይቻላል።

የጥናቱ ዋና አቅራቢ የሆኑት ዶክተር ሜላኒ ኒኮላስ  እንደተናገሩት  በእንግሊዝ  በካንሰር ፡ በልብ በሽታ ፤ በልብ ውጋት እንዲሁም  በጉበት በሽታ ከሚሞቱት ከ4ሺ በላይ ሰዎች በየቀኑ በአማካኝ  ይወስዱ የነበሩትን  የአልኮል መጠን  መቀነስ  ቢቻል  ህይወታቸውን  ማትረፍ ያስችላል፡፡ ግማሽ  ጠርሙስ አልኮ  ማለት አንድ  አራተኛ የወይን ጠርሙስ ማለት እንደሆነ በመጠቆም ህዝቡ  ምን ያህል  አልኮል መጠጣት እንዳለበት መረጃ  በመሥጠት  ሰዎች እራሳቸው ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ መርዳት እንጂ በመጠኑ ዙሪያ ገለጻ  ለማድረግ እንዳልተሞከረ አስታውቀዋል፡፡

የአልኮል  ኮንሰርን  ደርጅት  ዋና ሥራ አስኪያጅ ኤሪክ አፕል ባይ በበኩላቸው   የመንግሥት መመሪያዎች ህዝቡን ከአልኮል  መጠጥ ጋር  ተያያዠነት  ካላቸው  የጤና አደጋዎች በተጨባጭ መጠበቅ የሚያስችሉ መሆን አለባቸው ብለዋል ፡፡

ሌላው ችግር የአልኮል መጠጦች በአይነታቸው የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን  ሰዎች የሚወስዱትን  የአልኮል  መጠጥ  በጠርሙስ መለካት  በተግባር  ምን ማለት እንደሆነ  ህዝቡን  ለማስገንዘብ አስቸጋሪ  እንዲሆን ማድረጉ ነው ፡፡

ሆኖም የእንግሊዝ የመጠጥ አምራቾች ወኪል  የሆኑት ሄነሪ  አሽ ወርዝ 78 በመቶ የሚሆነው የእንግሊዝ ህዝብ  በህክምና ባለሙያዎች የሚፈቀደውን  አነስተኛ  የመጠጥ መመሪያ ተግባራዊ ያደርጋል ብለዋል፡፡ የመጠጥ አምራቾች ወኪል የሆኑት  ሄነሪ  አሽ ወርዝ   በዘፈቀደ  እያንዳንዱ  ሰው የሚወስደውን የአልኮል መጠን በግማሽ እንዲቀንስ ማድረግ አልኮልን  የአለአግባብ የሚወሰዱትን ሰዎችና ልዩ እንክብካቤ በሚያሻቸው ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ  የሚያስችል ዘዴ አይደለም በማለት አጣጥለውታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.