አንጎልዎ ጤናማ እንዳይሆን የሚያደርጉት 9ኙ ልማዶች 

Concept of six ability in human brain1. ቁርስ አለመብላት ፤

ቁርስ የማይበሉ ሰዎች በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ያሽቆለቁላል፡፡ ይህም በአንጎል ውስጥ የሚኖረውን የአስፈላጊ ንጥረነገሮች አቅርቦት እንዲቀንስና አንጎል እንዲጎዳ ያደርጋል፡፡

2. ከመጠን በላይ መብላት

ከመጠን በላይ መመገብ የአንጎል የደም ቅዳ ቱቦዎች እንዲደድሩ በማድረግ የአንጎል የማሰብ ብቃት እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

3. ሲጋራ ማጨስ ፤

የአንጎል መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል፤ ለመርሳት በሽታ ሊዳርግም ይችላል፡፡

4. ከፍተኛ የስኳር ተጠቃሚነት ፤

ከፍተኛ መጠን ያለው ስኳር መጠቀም ፕሮቲንና ንጥረነገሮች በደም አማካኝነት ወደ አንጎል አንዳይሄዱ እክል በመፍጠር የአንጎል እድገት እንዲስተጓጎል ያደርጋል፡፡

5. የአየር ብክለት ፤

አንጎላችን ከሰውነታችን ክፍሎች ውስጥ ከፍተኛው የኦክስጅን ተጠቃሚ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የተበከለ አየር መተንፈስ ወደ አንጎል የሚሄደው የኦክስጅን መጠን እንዲቀንስ በማድረግ የአንጎል ብቃት እንዲያሽቆለቁል ያደርጋል፡፡

6. እንቅልፍ ማጣት ፤

እንቅልፍ አንጎላችን እንዲያርፍ ያደርጋል፡፡ ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ ማጣት የአንጎል ህዋሳት ሞትን ያፋጥናል፡፡

7. ሲተኙ ጭንቅላትን መሸፈን ፤

ሲተኙ ጭንቅላትን መሸፈን የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን እንዲጨምርና የኦክስጅን መጠን እንዲቀንስ ስለሚያደርግ አንጎልን ክፉኛ ይጎዳል፡፡

8. አነቃቂ ሀሳቦች ማጣት ፤

አነቃቂ ሀሳቦች ማጣት የአንጎል መጠን እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል፡፡

9. ምሁራዊ አተካራዎች ማብዛት

የአንጎልን ብቃትና የሰላ የፈጠራ ብቃት ያዶለዱማል፡፡ (Source TenaAdam)

www.fb.com/HahuDaily for more updates

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.