(ከጤና ይስጥልኝ መፅሔት)

period የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ዘዴ አጠቃቀም መጨመሩ ይነገራል፡፡ ይህም ለኤች.አይ.ቪ መጨመር የራሱ አስተዋፅኦ እንዳለው ባለሞያዎች ያነሳሉ፡፡ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ እርግዝናን እንጅ ሌሎችን የአባላዘር በሽታዎችን ሊከላከል ስለማይችል እንደስያሜው ሁሉ አንዲት ሴት ድንገተኛ  የእርግዝና ስጋት ውስጥ ስትገባ ብቻ ልትጠቀመው የሚገባ ነው፡፡

ይህ አይነቱ የእርግዝና የመከላከያ ዘዴ ባለ ነጠላ አካላዊ ቅመም ሆኖ በአፍ የሚወሰድ ሲሆን ብዙ ጊዜ የሚወሰደው ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚያስከትለውን ድንገተኛ እርግዝና ለመከላከል ነው፡፡ ይህ ዘዴ ድንተኛ እርግዝናን ከመከላከል ባለፈ የሚዘወተር አይደለም፡፡

እርግዝናን የሚከላከለው እንዴት ነው?

 1. የሴቷ እንቁላል ከእንቁልጢ ተኮርታ እንዳትወጣ በማድረግ፤
 2. የማህፀን በር ፈሳሽን በማወፈር እና የአጣብቂኝ አይነት ባህሪ እንዲኖረው በማድረግ የወንድ የዘር ፍሬ ወደ ማህፀን ለመግባት የሚችልበትን መተላለፊያ በመዝጋት፤
 3. የማህፀን ግድግዳን በማሳሳት ከወንድ የዘር ፍሬ ጋር የተዋሃደችውን እንቁላል የምታርፍበትን የማህፀን ግድግዳ ለፅንሱ ቀጣይ እድገት እንዳይመች በማድረግ እርግዝና እንዳይከሰት ይከላከላል፡፡

የጎንዮሽ ችግሮች

 • የወር አበባ መዛባት (መጠነኛ የሆነ ወር አባባ መዛባት እንክብሉ በተወሰደ 1-2 ቀናት ድረስ ሊከሰት ይችላል)
 • የወር አበባ በሚጠበቅበት ጊዜ ፈጥኖ ወይም ዘግይቶ ሊመጣ ችላል፤
 • ማቅለሽለሽ፤
 • የሆድ ቁርጠት፤
 • የድካም ስሜት፤
 • የራስ ምታት፤
 • የጡት መደደር፤
 • መጠነኛ የመፍዘዝና መደንዘዝ፤
 • ትውከት ናቸው፡፡

ጤና ነክ ጥቅሞች

 • እርግዝና እንዳይከሰት ያደርጋሉ፤
 • የፅንስ መቋረጥ አያስከትሉም፤
 • እርግዝና ከተከሰተ በፅንሱ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አያመጣም፤
 • መካን አያደርግም፤

ይህ የእርግዝና ዘዴ አለ ተብሎ ግን ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ መፈፀም በፍፁም አይመከርም፡፡

መወሰድ ያለበት መቼ ነው?

 • ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች ትንቃቄ የጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት በተፈፀመ በ120 ሰዓታት ውስጥ ወይም 5 ቀን በአፍ መወሰድ አለባቸው ይላሉ ባለሞያዎች፡፡ መታወቅ ያለበት ቀኖች እየገፉ በሄዱ ቁጥር ግን እርግዝናን የመከላከል አቅሙ እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ ስለዚህ ወዲያውኑ መውሰድ ይመከራል፡፡
 • የመጀመሪያው እንክብል በተቻለ መጠን በፍጥነት መወሰድ ያለበት ሲሆን ሁለተኛው እንክብል ደግሞ የመጀመሪው እንክብል በተወሰደ በ12 ሰዓት በኋላ መወሰድ ይኖርበታል፡፡
 • የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን አንዲት ሴት የወር አበባ እያየች መውሰድ ትችላለች፡፡

መጠቀም ያለብን መቼ ነው?

 • ጥንቃቄ ከጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ መወሰድ ያለበት ሲሆን በፍጥነት ከተወሰዱ እርግዝናን የመከላከል አስተማማኝነታቸው ይጨምራል፡፡
 • ከማንኛውም ጥንቃቄ ከጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት በኋላ መጠቀም ይቻላል፡፡
 • ሌሎችን የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን በትክክል ሳንጠቀም ስንቀር፡፡
 • ወንዶች የዘር ፍሬያቸውን በትክክል ወደውጭ ማፍሰስ ሳይችሉ ሲቀሩ፡፡
 • በማህፀን ውስት ተቀምጦ የነበረው ሉፕ ሲወጣ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

በመሆኑም ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያዎች 85 ፐርሰንትብቻ ውጤታማ ናቸው፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.