የአልኮል ተጠቂነትን ለመቀነስ የሚረዱ ጥቂት ጠቃሚ ሃሳቦች

0

ሀሰን አሰፋ (የኛ ፕሬስ)

የአልኮል ተጠቂነትን ለመቀነስ የሚረዱ ጥቂት ጠቃሚ ሃሳቦችበፍቅረኝነት ጊዜና በትዳር ውስጥ ሴቶች ‹‹ባለቤቴን ከአልኮል ሱሰኝነት እንዴት ልታደገው እችል ይሆን?›› በማለት ይጨነቃሉ፡፡ ወንዶችም ፍቅረኛቸው የአልኮል ተጠቂ ከሆነች እንዲሁ ነው፡፡ የአልኮል ተጠቂዎችም እንዴት ከአልኮል ሱሰኝነት እንደሚወጡ በብርቱ ያስባሉ፡፡ ከአልኮል ሱሰኝነት መላቀቅ የቻለ አንድ ሰው አልኮል መጠጣት ካቆመ በኋላም የመጠጣት ስሜቱ ዳግም ሊያቆጠቁጥበት ይችላል፡፡ በመቀጠልም በድጋሚ ወደ ሱሰኝነት ሊመለስባቸው የሚችላቸውን ዕድሎች እርግፍ አድርጎ ለመተው የሚቸገርባቸውን ሁናቴዎች ለማንሳት እንሞክራለን፡፡

አልኮል ለመጠቀም የሚጋብዙ ሁኔታዎች

ዘለግ ላሉ ዓመታት አልኮልን ብቻ ተወዳጅ መጠጡ አድርጎ የኖረ አንድ ሰው በተለያዩ አጋጣሚዎች በጤናው ላይ በሚያጋጥመው እክል የተነሳ ወይም በሌላ ምክንያት አልኮል መጠጣቱን እርግፍ አድርጎ ሊተው ይችላል፡፡ ከተወሰነ እረፍት በኋላ ውሳኔውን ቀልብሶ ለመጠጣት የሚያበቁ ሁኔታዎች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ወደ ቀደመው የአልኮል ተጠቂነት ሁኔታዎች መመለስ የሚለካው በግለሰቡ በአመለካከት ነው፡፡ የአመለካት ውጤቱ በድርጊት የሚለካው ደግሞ በሂደት ነው፡፡ እነዚህን ሁኔታዎች በመቀጠል እንመለከታለን፡፡

ሁኔታ አንድ

አንድ የአልኮል ተጠቃሚ ከረጅም ጊዜ ልምዱ መላቀቅ የሚሳነው አልኮል የሚጠጣበትን ጊዜ በሌላ መልካም ልምድ መተካት ባለመቻሉ ነው፡፡ ከለመደው የመጠጥ ሙድ ለመውጣ ሲወስን ያንን ጊዜ በምን እንደሚያሳልፍ አስቀድሞ ማቀድ ይኖርበታል፡፡ ጊዜውን በለስላሳ መጠጦች ወይም በመዝናናት ለማሳለፍ መወሰን ይኖርበታል፡፡

ሁኔታ ሁለት

አንድ የአልኮል ተጠቃሚ ከአልኮል ሡሰኝነት ለመላቀቅ የራሱን ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ ውሳኔውን ተከትሎ የሚገጥሙትን መሰናክሎች የማለፍ ጠንካራ አቋም ሊኖረው ይገባል፡፡ በወዳጆቹ ወይም በጋባዦቹ ውትወታ እና የአብሮነት ጥሪ ከውሳኔው የሚንሸራተት ከሆነ ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ነበረበት ሊመለስ ይችላል፡፡

ሁኔታ ሦስት

የአልኮል ተጠቂው ዘወትር በድብቅ ወይም  ብቻውን የሚጠጣ ከሆነ ላለመጠጣት ሲወስንና ሲያቆም የለመደ አመሉ ተሎ ላይለቀው ይችላል፡፡ ወደ ቤቱ እያመራ እግሮቹ ሳያስበው አልኮል ወደሚያዘወትርበት ስፍራ ሊጥሉት ይችላሉ፡፡ ይህም ቢሆን የሚወስደውን የአልኮል መጠን ከቀድሞው በመቀነስ ቀስ በቀስ ከአልኮል ጥገኝነት ነፃ የሆነ አዲስ ህይወት እንዲኖረው መጣር ይኖርበታል፡፡

ሁኔታ አራት

በመጥፎ የህይወት አጋጣሚዎች የተነሳ ራሳቸውን አልኮል በመጠጣት ለመደበቅ የሚጥሩ ሰዎች የተሰማቸው ንዴት፣ ብስጭትና መጥፎ ስሜት አልኮል ሲጠጡ ጥሏቸው እሚሄድ ወይም የሚበርድ ይመስላቸዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ለማቆም ከወሰኑ በኋላ የሚያናድድ አጋጣሚ ሲገጥማቸው በቀላሉ ውሳኔያቸውን ይቀለብሳሉ፡፡

ከላይ የገለፅናቸው ሁኔታዎችን ከግምት በማገባት በትዕግስት መፍትሄ ማበጀት ይጠቅማ፡፡ የአልኮል ሱስ ተጠቂነት በአንድ ጀንበር ሊላቀቁት የሚችሉ አይደለም፡፡ ቀስ በቀስና በትዕግስት ግን መላቀቅ ይቻላል፡፡

አዕምሮን ማሳመን

የመጀመሪያው አስተሳሰብን ወይም ዕይታን መለወጥ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ለአዕምሮ መንገር ያስፈልጋል፡፡ የራስን ጤና ለመንከባከብ ከራስ በላይ ባለቤት እንደሌለ ማሳመን፡፡ በአጠቃለይም አዕምሯችንን ለማሳመን የሚረዱ ጠቃሚ ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡

 • የአልኮል ሱሰኛ በመሆኔ ያገኘሁት ጥቅም ምንድን ነው?
 • የአልኮል ጥገኝነቴ ከቤተሰቦቼና ከሌሎች የቅርብ ወዳጆቼ ጋር ያለኝን ግንኙነት ጤናማ አድርጎታል?
 • እለኮል በማዘውተሬ በስራ ላይ ያሳደረብኝ ተፅዕኖ ምንድን ነው?
 • አልኮል በማዘውተሬ ከጤና አንፃር ምን ጉዳት አስከትሎብኛል? ወደፊትስ ምን ጉዳት ሊያስከትልብኝ ይችላል?የመሳሰሉት የአልል ተጠቂነትን ለመቀነስ የሚረዱ ጥቂት ነጥቦች ነቸው፡፡

 

Spread the love
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  
 •  

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.