ቀለማት ስሜታችሁን ሊለውጡ የሚችሉባቸው 9 መንገዶች

የሰው ልጅ ቀለማትን የሚያይበት መንገድ ውስብስብ ሳይንስ ነው፡፡ የተለያየ የሞገድ ርዝመት ያላቸው ጨረሮች የብርሃን ሃይል በአይናችን ሬቲና ላይ በሚያርፉበት ጊዜ ወደ ተለያየ ቀለምነት ይተረጎማሉ፡፡ ሰዎች ቀለማትን የሚረዱበትና የሚመርጡበት መንገድ ግን ከስሜት ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ቀለማት ስሜትንና ጠባይን እንዴት ሊለውጡ እንደሚችሉ መረዳት ለሳይኮሎጅ ባለሙያዎች፤ ለሰዓሊያንና ዲዛይነሮች፤ ለሽያጭ ሰራተኞች እንዲሁም ዘወትር ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይጠቅማል፡፡

ቀለማት ስሜታችሁን ሊለውጡ የሚችሉባቸው 9 መንገዶችቀለማትን የታመሙና በተለይም አእምሮአቸው የተነካ ሰዎችን ለማከም ‹‹ከለር ቴራፒ›› መጠቀም ከጥንት ግሪካውያን፣ ግብፃውያንና ቻይናውያን ጀምሮ የነበረ ጥበብ ነው፡፡ አዩቬርዳ የተባለው ባህላዊ ህክምና ጥበብ ውስጥም ቀለማት ጉልህ ቦታ አላቸው፡፡

ቀለማትና የምግብ ፍላጎት

በ2012 የኮርኔል ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ምግብ የሚቀርብበት ሰሀን ከምግቡ ጋር ‹‹ማች›› በሚያደርግበት ወቅት ተመጋቢዎች 22 ፐርሰንት ይበልጥ ሊመገቡ እንደቻሉ ተረድተዋል፡፡ ትንሽ ብቻ መመገብ የምትፈልጉ ከሆነ ከምግባችሁ ቀለም ጋር የማይጣጣም ቀለም ያለው ሰሃን ተጠቀሙ ይላሉ፡፡ አረንጓዴ ነገር በብዛት የመመገብ ፍላጎት ያላችሁ እንደሆነ በአረንጓዴ ሰሀን ምግባችሁን አቅርቡ፡፡ ተመራማሪዎች እንደገለፁት መጠኑ ትንሽ የሆነ ሰሀን የሚጠቀሙ ሰዎች ትንሽ መገባሉ፡፡

አንዳንድ ቀለማት ሰዎች የርሃብ ስሜት እንዲሰማቸው የማረግ ዝንባሌ ሳኖራቸው አይቀርም፡፡ ፈጣን ምግቦችን ‹‹ፋስት ፉድ›› የሚሸጡ ኩባንያዎች በብዛት ቀይና ቢጫ ቀለም ያላቸውን ሰሀኖች ይጠቀማሉ፡፡ ቀይ ቀለም ችኩል ያደርጋችኋል፡፡ ቶሎ እንድታዙ፣ እንድትመገቡና ቶሎ እንድትሄዱ ይገፋፋል፡፡

ቢጫ ቀለም ለተሻለ ትኩረት

ቢጫ ቀለም ቢሮአችሁን መቀባት ትኩረታችሁን ለመሰብሰብ ይረዳችኋል፡፡ ንቁ መሆን የምትሹ ከሆነ ቢጫ አበባ፣ ቢጫ ፍሬምና ቢጫ ምንጣፍ ቢሮአችሁ ውስጥ እንዲኖር ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ ነገር ግን ዋና የቀለም ምርጫችሁ ቢጫ መሆን የለበትም፡፡ ምክንያቱም እረፍት አልባነትና መጠነኛ ጭንቀት እንዲሰማችሁ ሊያደርግ ይችላል፡፡ የስራ ቦታ ቀለማት ምርጫችን ቀላል የማይባል ተፅእኖ ስራችን ላይ ያሳርፋሉ፡፡ ትኩረትን ለመሰብሰብም በእጅጉ ይረዳሉ፡፡

አፍቃሪ ፍለጋ ላይ መሆናችሁን ይገልፃል

ሰዎች እና ሌሎች እንስሳቶችም ጭምር ቀይ ቀለም ስሜታቸውን እንሰሚያነሳሳ ሮቼስተር ዩኒቨርስቲ ውስጥ የተካሄደ ጥናት አሳይቷል፡፡ ቀይ ቀለም የወንዶችን የወሲብ ፍላጎት ይቀሰቅሳል፡፡ ሴቶችም ቀይ ቀለም ወንዶች ላይ በሚመለከቱበት ወቅት ማራኪ እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ ወደ እንስሳት አለም ስንሄድ አልፋ ወንድ ጦጣዎች ሰውነታቸው ቀላ ያለ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ሴት ጦጣዎች ከአልፋ ወንዶች ጋር ነው ወሲብ መፈፀም የሚፈልጉት፡፡

ወይን ጠጅ ቀለምን ብቸኛ የሆኑ ሰዎች በብዛት እንዲጠቀሙት ይመከራል፡፡ ይህ ቀለም ለራስ ያለን ፍቅር እና በጎ ስሜት ያንፀባርቃል፡፡

ዕድሜን ለማራዘም

ቀለማት በሁለት መንገድ እርጅናን ይከላከላሉ፡፡ በአንድ በኩል ውጥረትን በመቀነስ በሌላ በኩል ደግሞ የኮላጂን እድገትን በማበረታታት፡፡ ውጥረት ለበሽታ አጋልጦ ሰጣል፤ እድሜንም እንዲሁ ያሳጥራል፡፡ አንዳንድ ቀለማትን በተመስጦ መመልከት የውጥረት መጠንን ይቀንሳል፡፡ ይህ በበኩሉ ለእድሜ መርዘም ሚና ይጫወታል፡፡

ይህ ብቻ ሳይሆን ቀይ ቀለምን በቆዳችን በኩል ወደ ውስጥ እንስባለን፡፡ በ1942 በራሽያ ሃገር በተካሄደ ጥናት ተመራማሪዎች ቀይ ቀለም ሲመፓታቲክ ነርቨስ ስርዓትን የማነቃቃት ኃይል እንዳለው ደርሰውበታል፡፡

ቀይ መብራት ቴራፒ (red light therapy) በአሁኑ ሰዓት የኮላጂን ምርት እንዲጨምር ለማድረግ የሚውል ዘዴ ነው፡፡ የኮላጂን ምርት በዚህ መልኩ ሲጨምር ፊታችን ይበልጥ የወጣትነት ገፅታ ይላበሳል፡፡ ስፓ በመሄድ አልያም ደግሞ ቀይ መብራት ቤታችሁ ውስጥ ገዝታችሁ ልትጠቀሙ ትችላላችሁ፡፡ መብራቶቹን ስገዙ 600 ናኖ ሜትር አማካይ የሞገድ ርዝመት ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል፡፡ ለ18 ደቂቃ ያህል ሙሉ ፊትን በእነዚህ መብራቶች አልፎ አልፎ ማስመታት የወጣት ገፅታዎ ሳይተፋ እንዲቆዩ ያደርጋል፡፡

ሀዘንን እና ድብርትን ይቀንሳል

እንደ ቢጫ፣ ብርቱካናማ እና ቀይ ቀለማት የመሳሰሉትን መመልከት ድብርትን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ድብርት ውስጥ ስትሆኑ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ እና ግራጫ ቀለማትን ከአጠገባችሁ አርቁ፡፡

የድብርታችሁ ምንጭ የፀሃይ ብርሃን እጥረት ወይም የሜላቶኒን ቁጥር ማነስ ከሆነ ግን የሰማያዊ ብርሃን ቴራፒ ከድብርት ስሜታችሁ ውስጥ እንድትወጡ ሊረዳችሁ ይችላል፡፡ ዓይናችን ለሰማያዊ ቀለም ምላሽ የሚሰጡ ፎቶሪሴፕተሮች አሉት፡፡

ጠብ እና ጥል ራቁ

ብዙ ሰዎች ቀይ ቀለምን ከጠብ እና ጥል ጋር አዛምደው ያስቡታል፡፡ በመሆኑም ግንኙነታችሁ ውስጥ ጥል የበዛ እንደሆነ የቀይ እና ብርቱካናማ ቀለማት አጠቃቀማችሁን በልኩ አድርጉት፡፡ በምትኩ ሰማያዊ፣ ወይንጠጅ እና አረንጓዴ ቀለማት ምርጫችሁ ይሁኑ፡፡ ሰማያዊ ቀለም መረጋጋትን እና መግባባትን ለመፍጠር የሚረዳ ምትሃት አለው፡፡

ጥሩ እንቅልፍ

ጥሩ እንቅልፍ ለማግኘት ራስን በቀለማት ማረጋጋት ይመከራል፡፡ ሰማዊ፣ አረንጓዴ፣ ወይንጠጅ እና ግራጫ ቀለማት የልብ ምት ፍጥነት እንዲቀንስ እና የሰውነት የሙቀት መጠን ዝቅ እንዲል ስለሚረዱ የመኝታ ክፍልን ለማስዋብ ተመራጭ ናቸው፡፡ መኝታ ክፍል የተስተካከለ እና ከኤሌክትሮኒክ እቃዎች የጸዳ እንዲሆን ማድረግም ጥሩ እንቅልፍን ያበረታታል፡፡ ራዳጅ የሚባሉ የቀለም ባለሙያ ‹‹ሞቃት ቀለማትን መኝታ ክፍላችሁ ውስጥ ማብዛት ያለባችሁ ከፍቅረኛችሁ ጋር ጣፋጭ የፍቅር ምሽት ለማሳለፍ ስታስቡ ብቻ ነው›› ይላሉ፡፡

የሰማያዊ መብራት ቴራፒ (blue light therapy) እንቅልፍ እጅግ ዘግይተው የሚወስዳቸው ሰዎች ችግር ሊያቃልል ይችላል፡፡

አካዳሚያዊ ችሎታን ማሻሻል

ኢሊዮት የሚባል ተመራማሪ በአካሄደው ጥናት ቀይ እስክሪብቶ በብዛት መጠቀም የተማሪዎችን አካዳሚያዊ ችሎታ ሊቀንስ ይችላል፡፡ ቀይ፣ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ እና ግራጫ ቀለም ያላቸውን ቁጥሮች እና ወረቀቶች ለተሳታፊዎቹ በመስጠት ፈተና እንዲወስዱ ከተደረገ በኋላ ቀይ ቀለም የተጠቀሙ ተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤት ሊያስመዘግቡ ችለዋል፡፡ ቀይ ቀለም ከውድቀት ጋር የተያያዘ ስለሆነ ተነሳሽነትን ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ አስተማሪ ከሆኑ አስተያየት ወይም ማሻሻያ ተማሪዎችዎ ወረቀት ላይ በሚደርጉበት ወቅት ከቀይ ይልቅ አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ ቀለምን እንዲጠቀሙ ይመከራል፡፡

ጥናቶች ቀለማት እንዴት የነርቭ ስርዓት ላይ ጫና እንደሚያሳርፉ፣ ስሜትን የሚቀይሩ ሆርሞኖችን እንደሚያነቃቁ እና አልፋ የሚባሉትን የአንጎል ሞገዶች እንቅስቃሴ በመለወጥ ንቃትን እንዴት ሊጨምሩ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡ አልቤርታ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አንድ አስደናቂ ጥናት ተካሂዷል፡፡ 14 ዓይነ ስውራን እና በጠባይ አስቸጋሪ የሆኑ ልጆች የሚገኙበትን ክፍል ቀለም በመቀያየር የደም ግፊታቸው መጠን እና አስቸጋሪ ጠባያቸውን ለመቀነስ ተችሏል፡፡ ሳይንቲስቶቹ ልክ እንደ ፀሃይ ብርሃን ሁሉ ቀለማትም በቆዳ በኩል ወደ ሰውነት ይገባሉ የሚል መላ መተዋል፡፡

ምንጭ፡- ጤና ይስጥልን

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.