በመላኩ ብርሃኑ

Vaccinationበቀድሞው የአቅም ግንባታ ሚኒስቴር  ውስጥ በአስተዳደር ኦፊሰርነት ይሠራ  የነበረው የ32 ዓመት ወጣት የሕ  ይወቱን መስመር ወደ አሸናፊነት  ለመምራት ያደረገውን ትግልና የከፈ  ለውን መሥዋዕትነት ሲያስበው ዛሬ ለደረሰበት  ደረጃ ባበቃው የመንፈስ ጽናቱ ይኮራል፡፡ ጳውሎስ  ደሳለኝ ሆሣዕና ከተማ ውስጥ ለቤተሰቡ የመጀመሪያ  ልጅ ሆኖ ሲወለድ ጤነኛና የደስ ደስ የነበረው ሕፃን  ነበር፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ የገጠመውን ከባድ  የጤና እክል ለማዳን ወላጆቹ የተለያዩ የባሕል  ሕክምና መፍትሔዎችን ሲሞክሩ ቆይተዋል፡፡ ያ  ግን ለጳውሎስ የጠቀመው አንዳች ነገር አልነበረም፡፡
ሕመሙ ለሕይወቱ አስጊ ደረጃ እስኪደርስና ወላጆቹም  ተስፋቸው እስኪሟጠጥ ድረስ ሕፃኑን ዘመናዊ  ሕክምና ወደሚገኝበት ጤና ጣቢያ የመውሰድ ሐሳብ  ያመጣ ሰውም የለም፡፡ በመጨረሻ በአንድ የአካባቢው  ነዋሪ ምክር ጳውሎስ ወደ ሆሣዕና ከተማ ጤና ጣቢያ  ሲወሰድ የያዘው ሕመም ፖሊዮ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡  ፖሊዮ የልጅነት ልምሻ ተብሎ የሚታወቅና ሕፃናትን  ለሞትና ለከባድ የአካል ጉድለት የሚዳርግ በሽታ  ነው፡፡ ጳውሎስ የተወለደው ጤና ጣቢያ ባለመሆኑና  ወላጆቹም ሕፃናትን ስለማስከተብ ጥቅም የሚያውቁት  ነገር ስላልነበር በአራስነቱ በጠብታ መልክ ሊሠጠው  የሚገባውን የፖሊዮ ክትባት የመውሰድ ዕድል  አላገኘም፡፡ በአስጊ ሕመም ላይ ሆኖ ወደ ሕክምና  መስጫ ጣቢያ የደረሰው ሕፃን ከሞት ቢያመልጥም  በሽታው ግን ዕድሜ ልክ የማይድንና ከወገቡ በታች  ያለውን አካል የሚያሰንፍ ጠባሳ ትቶበት አለፈ፡፡  ይህም እግሮቹን ሰላላና መንቀሳቀስ የማይችሉ  አደረጋቸው። —– [ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—-

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.