ውድ ደበበ፡- ምን ማድረግ እንዳለብህ የምነግርህ ከዚህ በታች ያለውን ጥያቄ ስትመልስ ነው፡፡ ለመሆኑ ፍቅረኛህ በእርግጥ ትወደኛለች ብለህ ታስባለህ? ለምን ስላንተ ሳይሆን ስለ አለቃዋ ስሜት መጎዳት የምትጨነቅ ይመስልሃል? በመ/ቤቱ ውስጥ ያለውን ሁኔታስ በየጊዜው እየመጣች ላንተ የምትነግርህ ለምንድን ነው? ለማስቀናት ነው? እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን በጥሞና አስበህባቸው ለመመለስ ሞክር፡፡

በመጀመሪያ ማድረግ ያለብህ ፍቅረኛህ ለምን ስለ ራሷ ተፈላጊነት ብቻ ስታወራ ላንተ ስሜት እንደማትጨነቅ ጠይቃት፡፡ በእርግጥ ብዙ ሴቶች በፍቅረኞቻቸው ወይም በባሎቻቸው የመረሳት ወይም የመተው ስሜት እንዳይሰማቸው በሌሎች ወንዶች እንደተፈለጉ አድርገው ማውራት ይቀናቸዋል፡፡ የምትወድህና አንተ እንዳልከው ወደ ፊት አብራህ በትዳር ለመኖር ሀሳቡ ካላት ግን አንተን ለማስቀናት አትሞክርም፡፡ በዚሁ ድርጊት መቀጠል የምትፈልግ ከሆነ ግን ከአለቃዋ ጋር ከማስቸገር የዘለለ ግንኙነት አላት ለማለት ያስደፍራል፡፡ ምክንያቱም አለቃዋ አንተን ከተዋወቀ በኋላ እንኳን ሀሳቡን ለመቀየር ፍላጎት እንደሌለው ነው የሚታየው፡፡ እሷም አንተን ወስዳ ካስተዋወቀች በኋላ ከአለቃዋ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቆም ነበረባት፡፡ ግን ጭራሽ ፍቅረኛሽን ተይውና አብረን እንሁን እዳላት ነው የነገረችህ፡፡ ይህ ታዲያ ምን ማለት ነው? ግንኙነታቸው በመ/ቤት ደረጃ ብቻ የተወሰነ ላለመሆኑ የራስህን ማጣራት መስራት አለብህ ባይ ነኝ፡፡ ይህንን ካረጋገጥክ በኋላ የራስህን ውሳኔ ለመወሰን ትችላለህ፡፡ መልካም ዕድል፡፡

እርስዎ ለዚህ ሰው ምን ዓይነት ምክር ይሰጡታል። በኮመንት ቦክስ ላይ ይጻፉ:

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.