ራስ ወዳድ በመሆኔ የፀነስኩትን ልጄን እንዴት አሳድገው ይሆን?

01_teenmom_560x375ምላሽ፡- አንዲት እናት ልጇን ከመውለዷ በፊት ከሆስፒታል ባገኘችው ፈቃድ ከሰው ልጅ ጋር በመዋልና በማደር እናትነትን ለመለማመድ ችላለች፡፡ ለዚህ ደግሞ የሥነ ልቦና ጥናት ያደረገችውና ሕፃናትና የመንከባከብ ልምድ በሚመለከት መጽሃፍ ያሳተመችው ማርታ ሲምሰር የተባለችን እናት ተሞክሮ መጥቀስ ጠቃሚ ነው፡፡ ቀደም ሲል ለሕፃናት ደንታ የሌላትና ከራሷ ጋር ፍቅር ወድቃ የነበረችው ማርታ ስታከናውነው የነበረው ልምምድ የወለደች ያህል እናታዊ ፍቅርን እና ቅርርቦሽን እንደፈጠረላት ትናገራለች፡፡ በተግባር ከህፃናቱ ጋር መቀራረብ መፅሐፍን አንብቦ ከሚገኘው እውቀት በተሻለ ደረጃ በራስ መተማመንን እንደፈጠረላት ትናገራለች፡፡

ማርታ ስምንት ልጆችን ወልዳ አሳድጋለች፡፡ ‹‹…ዛሬ እኔም ሆንኩ ባለቤቴ ልጅ ከመውለዳችን በፊት ከነበርንበት ሁኔታ ፍፁም ተለይተናል›› የምትለው ማርታ እሷና ባለቤቷ ልጆች በማሳደግ ሂደት ውስጥ በርካታ አድካሚ እና አስቂኝ ሆኔታዎችን አሳልፈዋል፡፡ ይህ ደግሞ በራሱ ሕፃናትን ይበልጥ እንድንወዳቸው እና እንድናፈቅራቸው ያደርገናል የምትለው ማርታ ከልምዷ በመነሳት በአሁኑ ወቅት እየተበራከተ ስለመጣው ሕፃናትን የመንከባከብ ወይም የሞግዚትነትን የንግድ ስራ በተመለከተ ባሳተመችው መጽሐፍ ውስጥ በሃያኛው ክፍለ ዘመን እናትነት በተለይም ደግሞ ከስልጣኔ ጋር ተያይዞ የተጧጧፈ የገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ትጠቁማለች፡፡ ከድሮው በተለየ ሁኔታ ሰዎች ከጊዜ እጥረት የተነሳ አንዳንዴም ደግሞ ለተሻለ ዓላማ ሲሉ ልጆቻቸውን ለባለሙያ አሳዳጊዎች አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡ ልጆቻቸው ምን ያህል ደስተኛ ሆነው እንደሚያድጉ፣ ስለ ወደፊት ስኬታቸውና ተያያዥ ጉዳዮች አስቀድመው ይጨነቃሉ፣ ይጠበባሉ፡፡

ደራሲዋ ማርታ እንደምትለው ለልጆች አስተዳደግ ይበጃል የሚባል አንድ ወጥ የሆነ ወይም በሳይንሳዊ ጥናት የተረጋገጠ የአስተዳደግ ስልት የለም፡፡ እንዲያውም አብዛኞቹ ጥናቶች አዎንታዊ ጎን ካላቸው የአስተዳደግ ስልቶች ይልቅ አሉታዊ ጎኖችን በማጉላት ላይ ያተኩራል፡፡ ከዚህም በላይ በርካታ የስነ ልቦና ባለሙያዎችም በልጆች አስተዳደግ ውስጥ ለሚታየው ችግር ሁሉ እናቶችን ብቻ ተወቃሽ ያደርጋሉ፡፡

ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ በርካታ የጉዲፈቻ አገልግሎት በሚሰጡ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች በሕፃኑ ልጅ ላይ የሚፈጥሩትን አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ መመዘን ከባድ ነው፡፡ የሰው ልጅ ባህሪ ወጥነት የሌለውና እንደሁኔታው የሚቀያየር መሆኑ እንዲሁም የሕፃናቱ ለጋነት ለጥናት ስለማይመች መደምደሚያ ላይ መድረሱ ከባድ ነው ይላሉ፡- የሥነ ልቦና ምሁራን፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ከሆነ ደግሞ ስለ እናትና ልጅ መልካም ግንኙነት ከማንም በላይ መናገር የሚችሉት ከአጥኚዎች ይልቅ በርካታ ሕፃናትን በማሳደግ ልምድ ያላቸው እናቶች ናቸው፡፡ በሳይንሳዊ መንገድ ለሚደረገው ጥናት ምንም አይነት ተጨባጭ ምሳሌ ማቅረብ አይቻልም፡፡

ስለ ውጤታማ እናቶች ማወቅ ከፈለግን ግን ቤተሰባቸው ውስጥ የሚታየው መልካም ነገር ሁሉ ልብ ማለት በቂ ነው ይላሉ፡፡ ማርታና የእሷን ሀሳብ አራማጅ የሆኑ የፓርንቲንግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ለመልካም የልጅ አስተዳደግ አታችመንት ፓረንት ኢን ቤቢስ (Attachment parent in Babies) ለሁሉም የተሻለ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት የእናትና ልጅ ግንኙነት እንዲኖራቸው ያዛል፡፡ እናትየው የሕፃኑን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴና ስሜት መረዳት ይጠበቅባታል፡፡ ልጅ በሚያለቅስበት ወቅት በጣme ስሜታዊ የሆነ ምላሽ መስጠት፣ ሲተኛ አብሮ አልጋ ላይ መሆን እንዲሁም የረሃብ ስሜቱን አዳምጦ ጡት ማጥባትን የመሳሰሉ ቅርርቦሽን ይፈልጋል፡፡ ታዲያ ለዚህ አይነቱ ዘዴ አባትየው ለሕፃኑም ሆነ ለእናትየው የሚያሳየው እንክብካቤ ለውጤታማነቱ ወሳኝ ነው፡፡

በአታችመንት ፓረንቲንግ ዘዴ ውስጥ ካለው ቅርርቦሽ የተነሳ እናትየው ልጇ የሚያስበውን አስቀድማ እስከ ማወቅ ድረስ ትደርሳለች፡፡ ሕፃኑም እናቱ ለምታደርግለት እንክብካቤ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፡፡ ይህ የሁለቱ ቁርኝት ለልጁ የነገ የተሻለ ሕይወት በትልቅ ግብአትነት ያገለግላል፡፡

ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.