ስለ ትክትክ/ደረቅ ሳል (ፐርቱሲስ) በሽታ ማወቅ የሚገባዎት

0

whoopingcough

ሌላ ያልተስተካከለ እንቅልፍ የታየበት ሌሊት፡፡ እናት ከንቅልፏ ተነስታ የልጇን ሳል በማዳመጥና ለማባበል በመሞኮር ላይ ነች፡፡ በጣም ስለሚያሳስባት ዛሬ ማታ መተኛት ኣትችልም፡፡ ላለፉት ኣራት ቀናቶች፣ ልጇ በአስቸጋሪው ሳል ሰበብ መብላት፣ መጠጣት፣ እንዲሁም መተኛት አስቸጋሪ ሆኖበታል፡፡ ነገ፣ ልጇን ለመንከባከብ ለተጨማሪ ኣንድ ቀን ከስራ ትቀራለች፡፡ መቼ ነው የሚያልቀው በማለት ትገረማለች፡፡ እሷ በጣም ደክሟታል አንዲሁም ልጇም በመጥፎ ሁኔታ ላይ ነው፡፡ መጥፎ ኣጋጣሚ ሆኖ፣ መጨረሻው ቅርብ ኣይደለም ምክንያቱም ይህ ሳል ትክትክ/ደረቅ ሳል ስለሆነ፣ እንዲሁም ለረጂም ግዜ የሚዘልቅ በመሆኑ “የ100-ቀን ሳል” በመባል ይታወቃል፡፡
ትክትክ/ደረቅ ሳል (ፐርቱሲስ)– ከባድና በጣም ተዛማች የማስተንፈሻ ኣካል በሽታ ሆኖ፣ ምልክቱም ተከታታይና ከባድ የሳል ጥቃት ሲሆም ልዩ መግለጫው በሽተኛው አየር ወደ ውስጥ ሲያስገባ የሚሰማው “የመጮህ አይነት” ድምጽ ማስከተሉ ነው፡፡ በማንኛውም ሰው ላይ ጉዳት ያደርሳል፣ ሆኖም ግን በልጆች ላይ ሞት ሊያስከትል ይችላል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ፣ በሚነሶታ ከ3,500 ሰው በላይ በትክትክ በሽታ መለከፋቸውን በምርመራ ተረጋግጧል፡፡
ደግነቱ ግን፣ የትክትክ በሽታን መከላከል የሚችሉ ክትባቶች አሉ፡ የሚነሶታ የጤና ቢሮ (MDH) ጨቅላዎችና ልጆች ከትክትክ/ደረቅ ስል፣ ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ፣ አንዲሁም መንጋጋ ቆልፍ (DTaP) በሽታዎችን በማካተት የሚከላከል በ2 ወር፣ 4 ወር፣ 6 ወር፣ አንዲሁም ከ15 አስከ 18 ወር የልጅነት ዕድሜ የሚሰጥ ክትባት መውሰድን ይመክራሉ፡። የDTaP ማጠናከርያ ክታበት ከ4 አስከ 6 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ይሰጣል፡፡ከ DTaP የሚገኘው መከላከል ከጊዜ በኋላ ስለሚዳከም፣ የሚነሶታ ጤና ቢሮ(MDH) ሌላ Tdap የሚባል የትክትክ/ደረቅ ሳል ክትባት ለወጣቶች( ከ10-12 ዕድሜ ክልል ውስጥ) አና ለታዳጊዎች እንዲሰጥ ይመክራል፡፡ በቅድመ-ወጣትነት ዕድሜያቸው የTdap ክትባት ያልወሰዱ አዋቂዎች አሁን ኣንድ ክትባት መውሰድ ኣለባቸው፡፡ በዕድሜ ከፍ ያሉ ልጆችና ኣዋቂዎች እራሳቸውን በመከላከል፣ ዕድሜያቸው በጣም ትንሽ በመሆኑ በDTaP ክትባት ሙሉ መከላከያ ማግኘት ለማይችሉ በዙሪያቸው ለሚኖሩ ህጻናቶች የመከላከያ ክበብን መፍጠር ይችላሉ።።
የትክትክ/ደረቅ ሳል ክትባቶች በጣም ውጤታማ ናቸው፣ ሆኖም ግን አንደ ሁሉም ዓይነት ክትባቶች፣ 100% ውጤታማ ኣይደሉም፡፡ ምንም እንኳ ቢከተቡም፣ በበሽታው ሊጠቁ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ የትክትክ/ደረቅ ሳል በሽታ ኣብዛኛውን ጊዜ ተመርምሮ ሳይታወቅ ያልፋል ምክንያቱም ኣብዛኛውን ግዜ ጉንፋን በሚመስል ምልክት ስለሚጀምር፤ ሆኖም ግን ለሳምንታት ወይም ወራት የሚዘልቅ ተከታታይ የሆነ የሳል ጥቃቶች ሊለወጥ ይችላል፡። መጥፎ ኣጋጣሚ ሆኖ፣ ኣንዳንዶቹ በትክትክ/ደረቅ ሳል በሽታ መያዛቸውን ላያውቁ ስለሚችሉ ባለማወቅ ወደ ሌሎች፣ህፃናቶች ጭምር፣ ሊያስተላልፉት ይችላሉ፡፡
አንድ ሀኪም የትክትክ/ደረቅ ሳል በሽታን ከጠረጠረ፣ በሽታውን በምርመራ ለማረጋገጥ ምርመራ ሊደረግ ይችላል፡፡ በምርመራ የማወቅ ሂደቱ ኣስቀድሞ ከተደረገ፣ የበሽታው ምልክቶች ከባድነት ለመቀነስና አንዳይተላለፍ ለማድረግ የፀረ-ነፍሳት(አንቲባዮቲክስ) መድሃኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ የርስዎ ወይም የልጅዎ ሳል ትክትክ/ደረቅ ሳል ነው ብለው የሚያስቡ ከሆነ፣ ከህፃን ኣጠገብ ስለመሆን ጉዳይ ሀኪሙን ማናገር ኣስፈላጊ ነው፡፡ ልጅዎ በትክትክ/ደረቅ ሳል በሽታ ተለክፏል ብለው የሚያስቡ ከሆነ፣ ወድያውኑ ሀኪም ዘንድ ይሂዱ፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንድ ህፃን አመላካች የሆነውን ሳል ወይም ትክትክ የሚል ድምፅ ኣይኖረውም፣ ስለዚህ ከባድ የማስተንፈስ ችግር አንዳይኖር በንቃት ያስተውሉ፡፡

 

ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል።

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.