አስም

Asthma (1)አስም የሳምባ በሽታ ሲሆን በአተነፋፈስ ላይ ከፍተኛ ችግር ይፈጥራል፡፡ አስም ያለበት ሰው በድንገት አስሙ ሲነሳበት ወደ ሳምባው አየር የሚያስገቡት ቱቦዎቹ  ያብጣሉ፡፡ ይህም ወደ ሳምባው በቂ ኦክስጅን እንዳይገባ ይከለክላል፡፡  የአስም በሽታ በጣም ከባሰ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል፡፡

አስምን ሊያስነሱ  የሚችሉ የተለያዩ ምክኒያቶች አሉ፡፡ አስምን ከሚያስንሱ ዋነኞቹ አቧራ፣ የአበባ ሽታ፣ ጭስ፣ ስፖርት፣ የእንስሳት ሽታ እና ቀዝቃዛ አየር ናቸው፡፡ የአስምን በሽታ  ምን እንደሚቀሰቅስ በርግጠኝነት ለማወቅ ያስቸግራል፡፡

ማንኛውም ሰው አስም ሊይዘው ይችላል::  ሆኖም ግን በአብዛኛው ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው የከተማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ተጠቂ ይሆናሉ፡፡

የአስም በሽታ ምልክቶች

  • የአተነፋፈስ ችግር
  • ማሳል
  • በጣም ችኩል መሆን/ መንቀዥቀዥ

ለድንገተኛ የሆነ የአስም ጥቃት የሐኪምዎን መመሪያ ይከተሉ::  ምን ማድረግ እንዳለብዎት ካላወቁ ሐኪምዎን  በአስቸኳይ ያማክሩ::

የአስም ጥቃት በጣም አደገኛ ሊሆን ይችላል፡፡   ከዚህ በታች ያሉትን ምልክቶች  በልጅዎ ወይም አጠገብዎ ባለ ሰው ካዩ ባስቸኳይ ወደ  ሆስፒታል ይውሰዷቸው::

  • ልጅዎ መተንፈስ አቅቶት ሲጣጣር ካዩት
  • የልጅዎ ከንፈር ወይም ጥፍሮች ግራጫ ወይም ሰማያዊ መልክ ከያዙ
  • በአንገታቸው ወይም ደረታቸው ዙሪያ ያለው ቆዳ በጣም ከተወጠረ

ልጅዎን ወደ ድንገተኛ ክፍል ይዘው ሲሄዱ የመደበኛ  ሐኪምዎን ስምና ስልክ ቁጥር  እና ልጅዎ  የሚወስደውን  የአስም መድኃኒት ስም ዝርዝር መያዝ ያስታውሱ፡፡

Source -thebeehive.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.