90% እናቶች በእርግዝና ወቅት በሚጨምሩት ኪሎ ምክንያት የቆዳ መለጠጥ ምልክት በሰውነታቸው ላይ ይወጣባቸዋል። ሲጀምር ቀይ ወይም ደማቅ ሐምራዊ፣ እየቆየ ሲሄድ ነጭ ሆኖ የሚጎረጉደው ይህ ምልክት ትክክለኛ ምክንያቱ ይህ ነው ባይባልም በእርግዝና ጊዜ ባሉ የሆርሞን እና የሰውነት ለውጦች አማካኝነት እንደሚመጣ ይታወቃል።

Causes_of_Itchy_Stretch_Marks-235x300ለማጥፋት ከባድ ስለሆነ የሚሻለው እንዳይከሰት መከላከል ነው። ይህንም ማድረግ የሚቻለው በጣም ብዙ ኪሎ በቶሎ ባለመጨመር ወይም ባለመቀነስ እና የቆዳን እርጥበት በሞይስቸራይዘር በመጠበቅ ነው። በቀን ከሶስት እስከ አራት ጊዜ ሞይስቸራይዘሩን በደንብ ወደ ጡቶች፣ሆድ፣ ታፋና ቂጥ ቆዳ አሽቶ በማስገባት መጠቀም ይቻላል።

አንዴ ምልክቱ ከተከሰተ በኋላ ለማጥፋት ቢከብድም በገበያ ላይ የተለያዩ መድሃኒቶች ስለሚገኙ መጠቀም ይቻላል። ታድያ ካሉት መድሃኒቶች በተለይ የሬቲኖይድ መድሃኒቶች በፅንስ ላይ አደገኛ ችግር ስለሚፈጥሩ በመጀመሪያ ሐኪምሽን ማማከር ይኖርብሻል።

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የቆዳ መጥቆር 75% የሚሆኑ እናቶችን ያጠቃል። እንዲሁም እርጉዝ ባልሆኑ ግን የሆርሞናል የእርግዝና መከላከያ ክኒን እና መርፌ የሚወስዱ ሴቶች ላይ ሊከሰት ይችላል። የሚከሰትባቸው እናቶችም ሁኔታው በጣም ሊረብሻቸው ይችላል። የተለመደው የጥቁረቱ ስርጭት ጉንጮችን፣ ግንባርን፣ ላይኛውን ከንፈር፣ አፍንጫና አገጭን ያጠቃልላል።

የፀሃይ ጨረር ጥቁረቱን ስለሚያባብሰውና እንዲቆይ ስለሚረዳው የጨረር መከላከያ (sun screen) መጠቀም ይመከራል። በብዛት በአንድ አመት ውስጥ የሚለቅ ሁኔታ ቢሆንም አንዳንድ ሴቶች ላይ ሙሉ በሙሉ ላይለቅ ይችላል። ታድያ እርግዝናቸውን ላጠናቀቁ እናቶች ቆዳን የሚያነጡ/የሚያቀሉ መድሃኒቶች በሐኪማቸው ሊታዘዝላቸው ይችላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.