ከየኛ ፕሬስ

teeth  የድድ መድማት ዕድሜና ፆታ ሳይለይ በበርካታ ሰዎች ዘንድ የሚከሰት ሲሆን መንስኤዎቹም ብዙ ናቸው፡፡ ይህ ችግር ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ከጥርስ ጋር የተያያዘው ነርቭ ሲቆጣ፣ በድድ በሽታ፣ በጥርስ ቆሻሻ፣ በጥርስ መበስበስ፣ በድንገተኛ አደጋና በጥርስ መነቀል ምክንያት ነው፡፡ የጥርስ መነቀል የጥርስ መሸረፍን የሚያጠቃልል ነው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት ብዙውን ጊዜ ለጥርስ ወይም ለድድ መድማት እንደ ምክንያት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ አንዳንዴ ከጥርስና ድድ አካባቢ ውጭ የሚከሰት ህመም ወደ አፍም ውስጥ በመስፋፋት የድድ ወይም የጥርስ በሽታን ሊያስከትል ይችላል፡፡

ይህ ብዙውን ጊዜ በመንጋጋ መገጣጠሚያ አካባቢ ችግር ሲፈጠር ሲሆን ይህም የመንጋጋ መገጣጠሚያ በህክምናው አጠራር ቴምፖሮ ማንዲቡለር ጆይንት (TMS) ተብሎ የሚጠራ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የጆሮ ህመም አንዳንዴም የልብ ችግርና የጥርስ ውስጥ ህመምን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሊከሰት የሚችልን የጥርስና የድድ ህመም በቀላሉ መከላከል ይቻላል፡፡

የጥርስ ሐኪሞች የአንድን ሰው ጥርስ ንፁህ ለማድረግ ፍሎራይድና ሌሎችንም ኬሚካሎች ሊያዙ ይችላሉ፡፡ በተለይ ለህፃናት ጥርስ ህክምና እነኚህ ኬሚካሎችና ጥርሶችን የሚያጣብቁ ሙጫዎች ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፡፡

የጥርስ ህመም መንስዔዎች

የጥርስ ህመም ፐልፕ በተሰኘው የጥርስ ማዕከላዊ ቦታ በሚገኘው የአካል እብጠት ምክንያት የሚከሰት ነው፡፡ ፐልፕ ለህመም ተጋላጭ የሆነ የነርቭ ጫፍ የሚገኝበት አካል ነው፡፡ የፐልፕ ውስጥ እብጠት በጥርስ ጎድጓዳ ቦታዎች ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጉዳትና ኢንፌክሽን የፐልፕ እብጠት ሊያስከትል ይችላል፡፡

የጥርስ ህመም ምልክቶች

የጥርስና የድድ ህመሞች ተመሳሳይ ምልክቶች አሏቸው፡፡ አንድ ሰው በጣም ቀዝቃዛ ወይም በጣም የሞቀ ምግብ ወይም መጠጥ ሲወስድ ህመም ሊሰማው ይችላል፡፡ ህመሙ በጣም ሃይለኛና ከ15 ሴኮንድ በላይ የሚቆይ ከሆነ ይህ ከባድ የጥርስ ወይም የድድ ህመም ምልክት ሆኖ ሊቆጠር ይችላል፡፡

በጥርስ ውስጥ ያለው ህመም እየሰፋ ከሄደ ህመሙ በጉንጭ አካባቢዎች ሊከሰት የሚችል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ይህ የጥርስ እብጠት የጆሮና የመንጋጋ ህመም ሊያስከትል ይችላል፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ምልክቶች አንድ ሰው ለጥርስ ወይም ለድድ ህመም ሊጋለጥ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው፡፡

 • ስናኝክ ህመም መታየት
 • ለቀዝቃዛ ወይም ሙቅ ነገሮች በቀላሉ ለህመም መጋለጥ
 • በጥርስ አካባቢ ወይም በድድ መድማት
 • በጥርስ ዙሪያ፣ በመንጋጋና በጉንጭ ውስጥ እብጠት መከሰት
 • ድንገተኛ ጉዳት ወይም ህመም እና በየጊዜው የሚታዩ የጥርስና የድድ ህመምና መቅላት የጥርስ ህመም ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የጥርስ ህመም ከሌሎች በፊት ወይም በአፍ ውስጥ ከሚከሰቱ ህመሞች ተለይተው መታየት ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይም ከአፍንጫ፣ ከጆሮ ወይም ከጉሮሮ እንዲሁም ከመንጋጋ መገጣጠሚያ ህመም ጋር የማይገናኙ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡ አንዳንድ ሰዎች የመንጋጋ በሽታን ከጥርስ በሽታ ጋር አዛምደው ይገልፁታል፡፡ ይህ ግን የተሳሳተ ግንዛቤ ነው፡፡

የህክምና ክትትል የሚያስፈልግባቸው ጊዜያቶች

አንድ ሰው ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ውስጥ የአንደኛውን ምልክት በራሱ ላይ ካስተዋለ በአፋጣኝ ወደ ጥርስ ህክምና ተቋማት መሄድ ይኖርበታል፡፡

 • በመደበኛ መድኃኒቶች የማይድን የጥርስ ህመም ሲገጥመው፤
 • ጥርሱን ከተነቀለ በኋላ ከሁለት ቀናት በላይ ከባድ ህመም ከገጠመው የጥርሱ መሰኪያ ቦታ በሚገባ ያለመዳኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ በህክምናው አጠራር ‹‹dry socket syndrome›› የተሰኘውን የጥርስ ህመም ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ ህመምተኛው በተቻለ ፍጥነት የጥርስ ሀኪሞችን መጎብኘት ይኖርበታል፡፡
 • በድድ እና በፊት አካባቢ ከሚከሰት እብጠት ጋር የተያያዘ እጥረት፣ የጥርስ መነቃነቅ እና ትኩሳት በአፍ ውስጥ ለተከሰተ ችግር የሚጠቀሱ ምልክቶች ናቸው፡፡ እነኚህ ምልክቶች በድድና ጥርስ ውስጥ ለተፈጠረ ኢንፌክሽን ገላጮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ትኩሳትና እብጠት መግል መፈጠሩን የሚጠቁሙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በጥርስ ውስጥ የሚፈጠር መግል ደግሞ የአንቲባዮቲክስ ህክምና በቀዶ ጥገና መግል የቋጠረውን አካል መክፈትን ሊጠይቅ ይችላል፡፡
 • የጥርስ መሰበር ወይም መውለቅን በተመለከተ ይህ ችግር በአጋጣሚ ብዙዎች ላይ ሊያጋጥም የሚችል ነው፡፡ ይሄ ሲያጋጥምም ወደ ሀኪሞች ዘንዳ መሄድ የማይቀር ነው፡፡ በወቅቱ ወደ ጥርስ ሀኪም ከተሄደም በቀላሉ ሊፈወስ ይችላል፡፡ በተለይም ሕፃናት የመጀመሪያ ጥርሳቸው ከወለቀ ወይም ከተሸረፈ የሚያደርጉት ህክምና ሁለተኛ ጥርሳቸው ተስተካክሎ በጤናማ ሁኔታ እንዲወጣ የሚያግዝ ነው፡፡
 • አንድ ሰው አፉን በሚከፍትበት ጊዜ ህመም የሚሰማው ከሆነ ይህ ምልክት የመንጋጋ መገጣጠሚያው መጎዳቱን ወይም ማበጡን የሚያሳይ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ በአደጋ አሊያም ጠንካራ ነገር በመብላት ሊከሰት ይችላል፡፡
 • መንጋጋ በሚወልቅበት ጊዜ በጎደለው አካባቢ የሚገኘው ድድ ማበጡ የተለመደ ነገር ነው፡፡ ይህም የድድ ህመምን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ህመሙ ወደሌላው መንጋጋና ጆሮ ሊሸጋገር ይችላል፡፡ ችግሩ የከፋ ከሆነ ደግሞ ወደ ጉሮሮና የአፍ ወለል በመሸጋገገር ለመዋጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡

ቀደም ሲል በጥርስ ላይ የደረሰ ጉዳት፤ በጥርስ ውስጥ የሚከሰት ህመም፤ የልብ ህመምና ሽፍታ የጥርስ ህመምን ሊያባብስ ይችላል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምልክቶች የጥርስና የድድ ህመም ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ከፍኛ ትኩሳትና የጉንፋን ህመም፡- ከፍኛ ትኩሳትና ጉንፋን ብዙ ጊዜ አስከፊ የድድ ወይም የጥርስ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ከአንቲባዮቲክ ያለፈ ጠንካራ ህክምና ሊያደርግ ይችላል፡፡

በቅርብ ጊዜ በጭንቅላት ወይም አንገት ላይ የደረሰ አደጋ፡- በዚህ አይነቱ አደጋ የተጠቃ ሰው የራስ ምታት፣ የማቅለሽለሽ ስሜት፣ ትውከት ወይም ሌላ አይነት የህመም ስሜት ከተሰማ ሰፋ ያለ ህክምና ያስፈልጋል፡፡

ፊት ላይ የሚከሰት ሽፍታ

በመንጋጋ አካባቢ የሚከሰት ህመም፡-

በቤት ውስጥ የሚካሄድ ህክምና ለጥርስ ህመም

     ለመደበኛ የጥርስ ህመም አክታምፒኖርን ወይም ኢቡ ፕሩፊን መጠቀም ጊዜያዊ እፎይታ ሊሰጥ ይችላል፡፡ በጣም የሞቀ ወይም የቀዘቀዘ ምግብን ማስወገድም ያስፈልጋል፡፡ ጤናማ አመጋገብና አፍንና ውስጣዊ ክፍል ለማፅዳት የሚጠቅመውን ፍሎራይድ መጠቀም፡፡ አንድ ሰው ቢያንስ በዓመት ሁለቴ በጥርሱና በአፉ ውስጣዊ ክፍል በዴንታል ሃይጅኒስት እንዲፀዳ ማድረግ ከጥርስ በሽታ ራስን መከላከል ይቻላል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.