ስትሮክ ምንድን ነው?

0

ላይፍ መፅሄት

aneurysm_cerebralየአንጎል ህዋሳት ሥራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ በደም ስር አማካኝነት የማያቋርጥ የኦክስጅንና የጉሉኮስ አቅርቦት ያስፈልጋዋል፡፡ እስትሮክ የሚፈጠረው ደግሞ ወደ አንጎላችን የሚያመራው የደም አቅርቦት ሲዛባ የሚፈጠረው በቂ ያልሆነ የኦክስጅን አቅርቦት የአንጎል ህዋሳት እንዲሞቱ ሲያደርግ ነው፡፡ የደም ፍሰቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሊዛባ ይችላል፡፡

መንስዔ

በአንጎል ውስጥ የሚገኙ ጥቃቅን ደም ቅዳዎች መጥበብ ስትሮክ ሊያከትል ይችላል፡፡ የአንድ የደም ቅዳ ተቀጥላ ስር መዘጋት በአነስተኛ የአንጎል ክፍል ላይ ጉዳት በማስከተል በቦታው ያለው ህብረ ህዋስ እንዲሞት ሊያደርግ ይችላል፡፡ አንጎላችን ደም የሚያገኘው በአራት ዋና የደም ስሮች አማካኝነት ነው፡፡ እነኚህ ደም ቅዳዎች በስብማ ክምችት፣ በሳር መሰል አገናኝ ህብረ ህዋስ (filrouse lesion) መጎዳት፣ አሊያም በኮሌስትሮል ሳቢያ ከጠበቡ በውስጣቸው ያለው አላስፈላጊ ነገር ተበታትኖ ከደሙ ጋር በመፍሰስ ወደ አንጎል የሚያመራውን የደም አቅርቦት ሊደፍነው ይችላል፡፡

በአንዳንድ አጋጣሚዎች የደም መርጋት በልብ ውስጥ ሊፈጠር ይችላል፡፡ ይሄው የረጋ ደም አንጎል ውስጥ ወደሚገኙ ደም ቅዳዎች በማምራት እስትሮክ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ለእንደዚህ አይነቱ ችግር ዋነኛው መፍትሄ ያልተለመደ የልብ ምት ነው፡፡

በአንጎል ውስጥ ደም የሚፈሰው ብዙውን ጊዜ ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ከፍተኛ ደም ግፊት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቀላሉ ሊበታተኩና ሊደሙ የሚችሉ የደም ስሮች ስብስብም ይህን መሰሉን ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡

ከባድ የራስ ምታት ያለባቸው ሰዎች አልፎ አልፎ ስትሮክ ያጋጥማቸዋል፡፡ በእንዲህ አይነቱ ሁኔታ ችግሩ የሚፈጠረው በአንጎል ደም ስሮች መጥበብ ሳቢያ ነው፡፡ ይሁንና ብዙውን ጊዜ የስትሮክ ምልክቶች ከራስ ምታት ጋር አብረው የሚጠፉ ናቸው፡፡

ለስትሮክ የሚያጋልጡ ነገሮች

በአጠቃላይ ሲታይ ለስትሮክ ከሚያጋልጡ ነገሮች ዋነኞቹ ቀጥሎ ይጠቀሳሉ፡-

 • ከፍተኛ የደም ግፊት
 • ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን
 • ሲጋራ ማጨስ
 • የስኳር ህመም
 • የዕድሜ መግፋ ናቸው፡፡

 

የስትሮክ ምልክቶች

የአንጎል ሕዋሳት የኦክስጅን እጥረት ሲያጋጥማቸው የተለመደ ስራቸውን ማከናወን ያቆማሉ፡፡ ስትሮክን ተከትሎ የሚመጡ የበሽታው ምልክቶች በተጎዳው የአንጎል ክፍልና ጉዳት በደረሰበት የአንጎል ህብረ ህዋስ መጠን ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡

አነስተኛ ስትሮክ ምንም አይነት የበሽታ ምልክት ላያሣይ ይችላል፡፡ ይሁንና የአንጎል ህብረ ህዋስን ሊጎዳ ይችላል፡፡ አምስት ዋነኛ የስሮክ ምልክቶች አሉ፡፡

 1. በአንድ የሰውነት ጎን የሚያጋጥም ድንገተኛ የፊት፣ የእጅ ወይም የእግር ድንዛዜ ወይም ዝለት ነው፡፡ እነዚህን የሰውነት ክፍሎች ማንቀሳቀስ አለመቻል ወይም ስሜት የሌለባቸው መሆን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመንዘር ስሜት እንዲሰማን ሊያደርግ ይችላል፡፡
 2. በድንገት ግራ መጋባት፤ ለመረዳት ወይም ለመናገር መቸገር፤ አንዳንዴም በፊት ጡንቻዎች ላይ የሚፈጠረው ዝለት መንዘፍዘፍን ሊያስከትል ይችላል፡፡
 3. በድንገት በአንድ ወይም በሁለት አይኖች ለማየት መቸገር
 4. በድንገት ለመራመድ መቸገር፤ ራስ ማዞር ወይም ሚዛን መጠበቅ አለመቻል፡፡
 5. ምንም አይነት መንስኤ የሌለው ድንገቴ የራስ ምታት መፈጠር ናቸው፡፡

ስትሮክ ሲያጋጥም ምን ማድረግ አለብን

ከላይ የተጠቀሱት የበሽታው ምልክቶች በድንገት ሲያጋጥሙ የድንገተኛ ጊዜ ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ሳያበቃም ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ህክምና ማድረግ አለበት፡፡ የህክምና ርምጃ በመውሰዱ በኩል ከዘገየን ሁኔታውን ለመቀልበስም ሆነ ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ዋጋ አይኖረውም፡፡

አንቡላንስ እስከሚመጣ ድረስ የሚከተሉትን እርዳታዎች ማድረግ እንችላለን፡-

 • ጉዳት የደረሰበት ሰው ደም ወደ አንጎሉ እንዲፈስ በጀርባው መንጋለል አለበት፤
 • ራሱን ካዞረው፣ ምላሽ መስጠት ካልቻለ ወይም ካቅለሸለሸው እንዳይታፈን በጎኑ መጋደም አለበት፤
 • አስፕሪን ስትሮኩን ለመከላከል ትልቅ ሚና ቢጫወትም የበሽታው ምልክቶች መታየት እንደጀመሩ ህመምተኛው ተጨማሪ ህክምና እስከሚያገኝ ተጨማሪ አስፕሪን ባይወስድ ይመረጣል፡፡ ስትሮኩ ከደም መፍሰስ ጋር ከተያያዘ ደግሞ አስፕሪኑ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ሊያባብሰው ይችላል፡፡

የችግሩ ሰለባ ለስትሮክ ተጋልጦ እንደሆነ ለማወቅ የሚያግዙ ሦስት መሰረታዊ ትዕዛዞች አሉ፡፡ ሕመምተኛው የሚከተሉትን እንዲያደርግ መጠየቁ እገዛ ያርጋል፡፡

 1. ፈገግ እንዲልና ፊቱ እንደበፊቱ ቢሆን
 2. ሁለቱን እጆቹን ከፍ እንዲያደርግ፤ ይህን ጊዜ በሰውነቱ አንድ ጎን ችግር መኖር አለመኖሩን ማወቅ ይችላል፡፡
 3. ተራ አረፍተ ነገር እንዲናገር፤ ስትሮክ እንዳጋጠመው የተጠራጠርነው ሰው እነኚህን ሦስት ነገሮች ማድረግ ካልቻለ ወዲያውኑ አምቡላንስ መጥራት ያስፈልጋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.