MalnutritionLargeያልተመጣጠነ ምግብ ሰውነታችን በአግባቡ እድገቱን ሊፈፅም የሚያዳግተው ቢሆንም የተዋከበው ኑሯችን፣ የስራ ፀባያችንና አንዳንዴም የአመጋገብ ልማዳችን የቫይታሚን እጥረት እንዲከሰትብን ያደርጋል፡፡ ሰውነትዎ ምን እንደጎደለው ለማወቅና የሚያስፈልገውንም ለማሟሟላት እንዲረዳዎ ሰውነትዎን ማዳመጥ ተገቢ ነው፡፡

እጆች

እጆችዎ ቀዝቃዛ ከሆኑ የማግኒዝየም እጥረት አለብዎ፡፡ የታይሮይድ እጢም thyroxin እና triiodothyronine የተሰኙ ሆርሞኖችን በተገቢው ሁኔታ ባለማምረቱም ይከሰታል፡፡ ከባድ ድካምና ዝቅተኛ የልብ ምትም እጆች እንዲቀዘቅዙ ያደርጋሉ፡፡

ቆዳ

የመሸብሸብ ምልክቶች ከታዩ የዚንክ እጥረት ይታይቦታል ማለት ሲሆን መግል የያዙ እብጠቶች በቆዳዎ ላይ ከታዩ በቫይታሚን ኤ እጥረት የሚመጣው follicular hyperkeratosis የተሰኘው ችግር ተከስቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ጭንቅላትዎ ደረቅ ከሆነና የፀጉርዎ ስሮች አካባቢ ቀላ ያሉ ሽፍታዎችን ከተመለከቱ የቫይታሚን ሲ እጥረት ሲሆን እጅዎ የውስጠኛው ክፍል (palm) ቢጫ ከሆነ ሰውነትዎ ከሚፈለገው በላይ ቤታ ካሮቲን ይዟል ማለት ነው፡፡

ወደ ትከሻችን አቅራቢያ የሚገኘውና ብዙ ግዜ ክትባት የሚያርፍበት የእጃችን ክፍል አካባቢ ቆዳችን ሻካራ ከሆነ (chicken skin) የ Essential fatty acid deficiency እንዳለብዎ ያመለክታል፡፡

ልብ

ያልተለመደ የልብ ምት፣ ከፍተኛ የደም ግፊትና ልብ መጠኑ ባልተለመደ ሁኔታ ሲጨምር (cardiomegaly) መንስኤው የማግኒዝየም እና በሰውነታችን የሚመረተው (coenzyme Q10) የተሰኘ ንጥረ ነገር እጥረት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ካፌይን የማይስማማቸው ሰዎች ቡናን የመሳሰሉ በካፌን የተሞሉ ነገሮችን ሲወስዱም ሊከሰት ይችላል፡፡

ጥፍሮች

ጥፍሮችዎ ነጣነጣ ያሉ ነጠብጣቦች ካሉባቸው የሚኒራል – በዋነኝነትም የዚንክ እጥረት እንዳለ ያሳያል፡፡ ጥፍሮችዎ መስመር ካለባቸው ተጠያቂው የዚንክ እጥረት ነውለ፡፡ በቀላሉ የሚሰባበር ስለ ጥፍሮች ባለቤተት በሀጆኑም የማግኒዝየመ እጥረት አጋጥሞዎታል፡፡ ጥፍርዎትን የሚበሉ ከሆነ አጠቃላይ የሚኒራል እጥረት ተከስቶዎበታል ማለት ነው፡፡

የፊት ቆዳ

የፊት ቆዳ ቀላ ያለ ወዛምነት ከታየበት (በተለይ በአፍንጫዎ ዳርና ዳር ላይ) የቫይታሚን ቢ2 እጥረት መከሰቱን ያሳብቃል፡፡ በአፍንጫ ላይ የሚከሰት መቁሰልና በግንባር ላይ ብጉር ከታየ የቫይታሚን ቢ6 እጥረት አለ ማለት ነው፡፡

አፍ

የገረጣና የተሰነጣጠቀ ምላስ የአይረን እጥረትን ሲያመላክት ምላስዎ እብጠትና ህመም ያለው የተሰነጣጠቀ ከሆነ የቫይታሚን ቢ3 እጥረት መከሰቱን ያሳያል፡፡ የሚያቃጥል የምላስ እብጠትና የከንፈር መላጥ ከታየ መንስኤው የቫይታሚን ቢ2 እጥረት ነው፡፡ ያበጠና ጥርስ አካባቢ ያለው የምላስ ክፍል ገባ ገባ ያለ ከሆነ የማይስማማዎን ምግብ ተመግበዋል፡፡ ሲታይ ለስላሳ ቢመስልም እብጠቱ ህመም የሚያስከትል ከሆነ የፎሊክ አሲድ እጥረት እንዳለብዎ ያሳያል፡፡ የተሰነጣጠቀ ከንፈር የቫይታሚን ቢ2 እጥረት እንዳለ ያመለክታል፡፡

በማግኒዚየም የበለፀጉ ምግቦች

ጡንቻዎችና ነርቮች ሥራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የበሽታ መከላል አቅምን በማሳደግ፣ የልብ ምትን በማስተካከል ጠንካራ አጥንት እንዲኖረን በማድረግ ከሚታወቁት አስፈላጊ ሜኔራሎች ውስጥ ማግኒዚም ዋነኛው ነው፡፡ የሚኔራሉ እጥረት እንዳይከሰትብን ለማድረግ አረንጓዴ የጓሮ ተክሎች፣ ኦቾሎኒና የቅባት እህሎች፣ አሳ፣ ጥራጥሬ፣ ያልተፈተገ ስንንዴ፣ አቦካዶ፣ እርጎ፣ ሙዝ፣ ጠቆር ያሉ ቸኮሌቶች በዋናነት እንድንመገባቸው ይመከራሉ፡፡

ዚንክ

የማሽተት አቅምን ለመጠበቅ፣ የበሽታ መከላከል አቅም እንዳይጎዳ ለማድረግ፣ ፕሮቲን ለመገንባ፣ ኢንዛይሞችን ለማነሳሳትና DNA ለመስራት ወሳኝ የሆነውን ዚንክ የባህር ምግቦች (ክራብ፣ አይስተር፣ ሎብስተር)፣ ቀይ ስጋ፣ የስንዴ ዳቦ፣ ስፒናች፣ የዱባ ፍሬ፣ ኦቾሎኒ፣ ካካዎና ቸኮሌት፣ የአሳማ ወይም ዶሮ ስጋ፣ ባቄላና እንጉዳይን በመመገብ ማግኘት ይቻላል፡፡

ቫታሚን ኤ

ከአስፈላጊ ቫይታሚኖች አንዱ የሆነው ቫታሚን ኤ ለአይን ብርሃን፣ የበሽታ መከላከል አቅምን ለማሳደግና ለቆዳ ጤንነት ጠቃሚ ነው፡፡ ጉበት፣ በርበሬና ሚጥሚጣ፣ ስኳር ድንች፣ ካሮት፣ አትክልቶች፣ ሠላጣ፣ በቫይታሚን ኤ ከበለፀጉ ጥቂቶች ናቸው፡፡

ቫይታሚን ሲ

የተጎዱ ጅማቶችን፣ የደም ስሮች፣ ቁስልና ጭረቶችን ሁሉ ለማከም የሚረዳው ቫይታሚን ሲ ሚጥሚጣ፣ ዘይቱን፣ የፈረንጅ ቃሪያ፣ አረንጓዴ ተክሎች፣ ብሮኮሊና አበባ ጎመን፣ ፓፓየ፣ ብርቱካንና እንጆሪ መገኛዎች ናቸው፡፡

ቫይታሚን ኬ

ቫይታሚን ኬ አጥንት የሚያሳሳውን አስቲኦፓሮሲስ እና የአልዛይመርን በሽታዎችየማም ብቃት አለው፡፡ ከቫይታሚኑ ከበለፀጉት ምግቦች መካከልምሥራ ሥሮች፣ አረንጓዴ አትክልቶች፣ ጥቅል ጎመን፣ ብሮኮሊ፣ ሚጥሚጣና በርበሬ፣ ባሮ ሽንኩርት፣ ጎመን ኩከምበርና ዘቢብ ይጠቀሳሉ፡፡

ቫይታሚን ቢ2

የዚህ ቫይታሚን እጥረት ከንፈር እንዲሰነጣጠቅ፣ አፍ እንዲቆስል፣ የአፍ አልሰርና የጉሮሮ ህመም እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ቫይታሚኑ የሚገኝባቸው ምግቦች ጉበት፣ ቅመማ ቅመምና በርበሬ፣ ቺዝ፣ አሳ፣ የቅባት እህሎች ጥቂቶች ናቸው፡፡

ቫይታሚን ቢ6

ሴሎች የሰውነት ዑደትን በተገቢው እንዲያከናውኑ የሚረዳው ቢ6 በስንዴ፣ በቅመማ ቅመም፣ ነጭ ሽንኩርት (ጥሬውን)፣ ጉበት፣ አሳና የአሳማ ስጋ ውስጥ ይገኛል፡፡

ቫይታሚን ቢ12

የሰው ልጅ ተመራምሮ ካገኛቸው የቫታሚን ነዘሮች ውስጥ ሰፊውና እጅግ ውስብስቡ ቢ 12 ሲሆን የቫዩታሚኑ እጥረት ለደም ማነስ፣ ድካም ድብርትና መጨናነቅ ያጋልጣል፡፡ ጉበት፣ ዓሳና አኩሬ አተር ምርቶች፣ ቀይ ስጋ፣ ወተት፣ ችዝና እንቁላል የቫይታሚኑ መገኛዎች ናቸው፡፡

ቫይታሚን ቢ3

በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ስብ ፕሮሰስ በማድረግ የኮሌስትሮል መጠንን ዝቅ ያደርጋል፡፡ የደም የስኳር መጠንን ያረጋጋል፡፡ ያልተፈተገ ስንዴ፣ ዓሳ፣ ጉበት፣ ሚጥሚጣና በርበሬ፣ ኦቾሎኒ፣ የዶሮና አሳማ ስጋ መገኛዎች ናቸው፡፡

                                                                                    ምንጭ፡- አዲስ ጉዳይ መፅሔት    

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here