olympic-baby-gene-testingበቤተሰብዎ ውስጥ ስለተከሰተ የበሽታ ዝርዝር ያውቃሉ? በጣም በጉልህ ስለሚነገሩትና ስለሚታዩት በሽታዎች ያውቁ ይሆናል፡፡ ምናልባት ቅድም አያትዎ እና እህቶቻቸው የጡት ካንሰር ይዟቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው ይሆናል፡፡ ወላጅ አናትዎ ግን ከዚህ በሽታ ነፃ ሆነው ይሆናል፡፡ ወይም ምናልባት ወላጅ አባትዎ እና ወንድማቸው የደም ብዛት ችግር ይኖራቸው ይሆናል፡፡ ወይም ምናልባት ወላጅ አባትዎ እና ወንድማቸው የደም ብዛት ችግር ይኖራቸው ይሆናል፡፡ ብዙም ትኩረት የማይሰጧቸው በቤተሰብዎ ውስጥ ያሉ የተለያዩ በሽታዎች ይኖራሉ፡፡ የተወሰኑ በሽታዎች በዘር ወደ ልጅ ወይም ወደ የልጅ ልጅ እየተላለፉ ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ በሽታዎች በተፈጥሮ የሰውነት አወቃቀር ምክንያት የሚመጡ፤ አንዳንዶች ደግሞ ተመሳሳይ የመኖሪያ ቦታን በመጋራት፣ ተመሳሳይ ምግብ ሁሌ በመመገብ እና በመሳ ሰሉት ምክንያቶች ሊይዝዎት ይችላሉ፡፡ ከእነዚህ በዘር ከሚተላለፉ በሽታዎች ውስጥ የተወሰኑትን ከዚህ ቀጥሎ በአጭሩ እንመለከታለን፡፡

8. የጡት ነቀርሳ (ካንሰር)
የጡት ካንሰር ጂን 1 እና የጡት ካንሰር ጂን 2 በመባል የሚታወቁ በዘር የሚተላለፉ የሰውነት መዋቅሮች (ጂኖች) አሉ፡፡ የቤተሰብዎ አባላት በተለይም እናትዎ፣ እህትዎ ወይም ሴት ልጅዎ የጡት ካንሰር ተጠቂ ከሆኑ በቶሎ እርስዎም መመርመር ይኖርብዎታል፡፡
7. የማህፀን ካንሰር (ነቀርሳ)
ይህን ዓይነት ካንሰር የጡት ካንሰር ጂኖች እራሳቸውን በመለወጥ ሊያመጡት ይችላሉ፡፡ እናቶ፣ የሴት ልጅዎ ወይም እህትዎ የማህፀን ካንሰር ተጠቂ ከሆኑ እርስዎም በህይወትዎ የ 5 በመቶ በዚህ በሽታ የመያዝ ዕድል አለዎት፡፡ በሽታው ሳይባባስ በጊዜ ለማወቅ መመርመር ይበጃል፡፡
6. ከፍተኛ የደም ግፊት
ከፍተኛ የደም ግፊትን ተመርምሮ የታዘዘን መድኃኒት በተገቢው መልክ በመከታ ተል፣ ጤናማ አመጋገብ በመመገብና የሰውነት እንቅስቃሴ (ስፖርትን) በመሥራት ልንቆጣጠ ረው እንችላለን፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰዎች በሽታ ው በጣም እስኪባባስ ድረስ እንዳለባቸው አያውቁትም፡፡ ከወላጆች አንዳቸው የደም ብዛት ተጠቂ ከሆኑ፤ በየጊዜው በመመርመር ጤናዎን መከታተል ይኖርብዎታል፡፡
5. ከፍተኛ ኮሌስትሮል
ኮሌስትሮል የምንለው በቀይ የደም ሴሎች (በደምዎ) ውስጥ የስብ ብዛትን ነው፡፡ በበዛ ቁጥር ለጤና በጣም አደገኛ ነው፡፡ የኮሌስትሮል መጠንዎን ጤናማ አመጋገብን በመከተልና ስፖርት በመስራት ሊቆጣጠሩት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የኮሌስትሮል መጠንዎን የማይቆጣጠሩት ከሆነና ወላጅዎ ወይም ልጅዎ ከ55 ዓመታቸው በፊት ለልብ ህመም የተጋለጡ ከሆነ አደጋ ላይ እንደሆኑ ይወቁ፡፡ የኮሌስትሮል መጠነንዎን በየጊዜው ይከታተሉ፡፡
4. የስኳር በሽታ
ሁለቱም ዓይነት 1 አይነት እና 2 የሚባሉት የስኳር በሽታ አይነቶች በዘር ይተላለፋሉ፡፡ በየትኛውም ዓይነት የስኳር በሽታ ተጠቂ የሆነ የቤተሰብ አባል ካሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ የደሞን የስኳር መጠን እየተመረመሩ ይከታተሉት፡፡ ምንም እንኳን ዓይነት 1 የስኳር በሽታን እንዳይዘን ማስቀረት ባይቻልም፤ ዓይነት 2 ግን እንችላለን፡፡ ይህም የሚሆነው በጤናማ አመጋገብና ስፖርትን በመሥራት ነው፡፡
3. ግላውኮማ
ግላውኮማ በዘር የሚተላለፍ የዓይን በሽታ ነው፡፡ በቤተሰብዎ ውስጥ የግላውኮማ ችግር ካለ ጨርሶ እንዳይዝዎት ማድረግ ባይቻልም በህክምና ማዳን ግን ይቻላል፡፡
2. ድብርት
በድብርት ምክንያት የመጣ የአእምሮ ህመም በቤተሰብዎ ውስጥ ካለ ያ የታመመ ሰው በዘር ተላልፎበት ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ ነገር ግን ልብ ይበሉ፡፡ ይህ በሽታ ሁሌ በዘር ብቻ ተላል ፎ አይዝም፡፡ በቤተሰብዎ ውስጥ ይህ በሽታ ባይኖርም እርስዎ በራሶ ሊይዝዎት ይችላል፡፡
1. አለርጂ እና አስም
አለርጂ የምንለው ለምሳሌ የአበባ የወንዴ አባላዘር ብናኝ ሲሸተን ዓይናችንን የመቆጥቆጥ እና የመቅላት፣ የመተንፈሻ አካሎቻችን ማሳከክ እና ለመተንፈስ መቸገር ዓይነት ምልክት ካሳየን አለርጂ ብለን እንጠራዋለን፡፡ ይህም አለርጂ በዘር ይተላለፋል፡፡ ከወላጅዎ አንዳቸው በአለርጂ ከተጠቁ እርስዎም 50 በመቶ የመያዝ ዕድል አሎት፡፡ ሁለቱም ወላጆቾ ደግሞ ካለባቸው የ75 በመቶ የመያዝ ዕድል አለዎት ማለት ነው፡፡ አስምም ብዙ ጊዜ ከአለርጂ ጋር በአብዛኛው ዝምድና አለው ተብሎ ይታመናል፡፡ አብዛኛዎቹ አስም ያላቸው ህፃናት አለርጂም አለባቸው፡፡ ሁለቱም ደግሞ በዘር ይተላለፋሉ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.