የሸንኮራ የጤና ጠቀሜታዎች

dc2a1ae8ac60464700aa7be25ea2c408_Generic ኢትዮጵያን ጨምሮ ሸንኮራ አገዳ በበርካታ ሃገራት ለምግብነት ይውላል፡፡ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂም ተወዳጅ መጠጥ ነው፡፡ cane juice ተብሎ የሚጠራው የሸንኮራ ጭማቂ ተፈጥሯዊ የሆነ የተሟላ ኃይል ሰጪ መጠጥ ነው፡፡

በስኳር በሽታ የመያዝ እድልን ይቀንሳል

ሸንኮራ አገዳ ከስኳር ጋር ሲነፃፀር ለስኳር በሽተኞች ተመራጭ ነው፡፡ ስኳር የደም የስኳር መጠንና የኢንሱሊን መጠን እንዲዛባ የሚያደርግ ሲሆን ሸንኮራ ግን ከዚህ ጉዳት የፀዳ ነው፡፡ ሸንኮራ ዝቅተኛ የ glycemic index (ግሉኮስና ካርቦሃይድሬትስ በሰውነታችን ዑደት የሚያደርግበት ፍጥነት) አለው፡፡ ዝቅተኛ የግይሴሚክ ኢንዴክስ የሚታይባቸው ምግቦች ዝቅተኛ ኢንሱሊን እንዲመረት የሚያግዙ ሲሆን የደም ስኳር መጠንን ለማገዝም ይረዳሉ፡፡ በዚህ የተነሳም በደም ውስጥ ዝቅተኛ የስብ መጠን ስለሚኖር በስኳር በሽታ የመያዝ እድልዎ ይቀንሳል፡፡

ቁስልን ይፈውሳል

Plantcultures.org የተባለ ተቋም ባደረገው ጥናት ሸንኮራ አገዳ ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች ቁስል በፍጥነት የማዳን አቅም አላቸው፡፡ የበሽታ መከመላከል አቅምንም ያሳድጋል ብሏል፡፡

ብርድና ጉንፋንን ይከላከላል

የሸንኮራ አገዳ ጭማቂን በሚያዘወትሩ ሰዎች ዘንድ ጭማቂው የቆሰለ ጉሮሮን ከመፈወሱም በላይ ብርድና ጉንፋንን በሩቁ ይከላከላል ተብሎ ይታመንበታል፡፡

የውስጥ አካላትን ጥንካሬ ያሳድጋል

ሸንኮራ ለበርካታ የውስጥ ብልቶቻችን ሃይል ያቀርባል፡፡ ልብ፣ ኩላሊት፣ አንጎል፣ ጉበትና ዐይን ከሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ከፍተኛ ጥቅም ያስገኛሉ፡፡

ሸንኮራና የካንሰር ህመምተኞች

በፎስፈረስ፣ ካልሲየም፣ አይረን፣ ማግኒዝየምና ፖታሲየም የበለፀገው የሸንኮራ አገዳ በነዚህ ንጥረ ነገሮች የተነሳ ካንሰርን ለሚፋለሙ ሰዎች ጠቃሚነቱ የጎላ ነው፡፡ በሸንኮራ ጭማቂ ላይ የተደረጉ ጥናቶች የፕሮስቴትስና የጡት ካንሰር ሴሎችን በብቃት መከላከሉን ዘግበዋል፡፡ በተጨማሪም ሰውነት በቂ ፈሳሽ እንዲኖረው በማድረግ በኩልም ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል፡፡ በውስጡ በከፍተኛ መጠን የያዛቸው ካርቦሃይድሬትና ፕሮቲን ለዚህ ጠቀሜታው በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡ በውስጡ የያዛቸውን ቫይታሚኖችና ሚኔራሎች ኩላሊት፣ ልብና አዕምሮ በአግባቡ ተግባራቸውን እንዲወጡ ያደርጋል፡፡

ሙቀትን በሸንኮራ ጭማቂ

ሸንኮራ ሰውነት ቀዝቀዝ እንዲል ያደርጋል፡፡ በበርካታ ሸንኮራ በስፋት በሚያበቅሉ ሀገራት በሙቀት ወራት የሸንኮራ ጭማቂ መጠጣት የተለመደ ነው፡፡ ጭማቂው ከማቀዝቀዙ በተጨማሪ በሙቀቱ የተነሳ የልብ ድካም እንዳይከሰት ይረዳል፡፡

ኩላሊት ጠጠር ላለባቸው ጠቃሚ ነው

የሸንኮራ ጭማቂ በኩላሊት ጠጠር ለሚሰቃዩ ሰዎች ፍቱን ነው ይባልለታል፡፡ በህክምናው ቋንቋ renal colic የሚሰኘው በኩላሊት ጠጠር የተነሳ የሚከሰትን ህመም የሸንኮራ ጭማቂን በተደጋጋሚ በመውሰድ ማከም ይቻላል፡፡ ጭማቂው በተፈጥሮው ቶሎ ቶሎ የሚያሸና ነው፡፡ ሸንኮራ ጠጠሮቹን ከማስወገዱም በላይ የሽንት ቧንቧዎችን አጠቃላይ ጤንነት ይጠብቃል፡፡ ለመሽናት ያለመቻል ችግሮች ተብለው የሚጠቀሱትን auria እና dysuria በማስወገድ ኩላሊት በቀላሉ ሽንትን እንዲለቅ ያስችላል፡፡

እርጅና በሸንኮራ

በጥንታዊ የህንድ መዛግብት ላይ ሰፍሮ እንደሚገኘው የሸንኮራ አገዳ ጭማቂን አዘውትሮ የሚወስድ ሰው እርጅናን በሩቁ በማለት ‹‹አናረጅም እኛ›› እያለ መኖር ይችላል፡፡ በቅርቡ በተደረጉ ጥናቶች ደግሞ ጭማቂው በበርካታ አንቲኦክሲዳንቶች የበለፀጉ በመሆኑ እርጅናን በማዘግየት በወጣትነት ዘመን መቆየት እንደሚቻል ይገልፃሉ፡፡

ለጥርስ ይበጃል

ጥርሶቻችን አዘውትረን በምንመገባቸው ለስላሳ ምግቦች የተነሳ ደካች ይሆናሉ፡፡ እንደ ሸንኮራ ያሉ ምግቦች ጥርሶችን ስለሚያሰሩ ጠንካሮች እንዲሆኑ ከማስቻላቸውም በላይ የጥርስን ንፅህና ይጠብቃሉ፡፡

የወፍ በሽታ(joundice) እና ሸንኮራ

ቆዳን ቢጫ በማድረግ የሚታወቀው የወፍ በሽታ ለመከላከል የተለመደው መድሃኒት የስኳር ጭማቂ ነው፡፡ የወፍ በሽታን ደካማ የጉበት እንቅስቃሴና የተደፈነ የሃሞት ፈሳሽ የሚፈጥሩት ነው፡፡ ፈጣን ፈውስ ለማኘት ሁለት ብርጭቆ የሸንኮራ ጭማቂ ከሎሚና ጨው ጋር ቀላቅለው ይውሰዱ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.