መንታ እርግዝና የሚፈጠረው እንቁላል በሚለቀቅበት ወቅት (ovulation) ሁለት እንቁላሎችን አዘጋጅተሽ እነርሱ ከሁለት የወንድ የዘር ህዋሶች ጋር ስለተዳቀሉ ወይም አንድ እንቁላል ከአንድ የዘር ህዋስ ጋር ተዳቅላ የፈጠረቻት የፅንስ ህዋስ ለሁለት ተከፍላ ሁለት ፅንሶች በመስራቷ ነው። (link to ovuation)

twins_week24_rollover_indexመንታ ማርገዝ ድርብ ምርቃት ነው። ቢሆንም መንታ ማርገዝሽ በሰውነትሽ ላይ ሊፈጥረው ስለሚችለው ተጨማሪ ጫና ወይም በፅንሶቹ ላይ ሊፈጠሩ ስለሚችሉ ችግሮች ልትጨነቂ ትችያለሽ። ታድያ ስለ መንታ እርግዝና ማወቅ የሚገባሽ ከስር የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ጉዳዮች ነው።

በሰላሳዎቹ እና በአርባዎቹ ውስጥ ከሆንሽ መንታ የማርገዝ እድልሽ ዕድሜያቸው ከዛ በታች ከሆኑ እናቶች ጋር ሲወዳደር በጣም ከፍ ያለ ነው። ይህም የሚሆነው እድሜ እየጨመረ ሲሄድ የወር አበባ መዛባት ስለሚኖር እንቁላል አዘጋጅተሽ በምትለቂበት ጊዜ ሁለት የእንቁላል ከረጢቶች አዘጋጅተሽ የመልቀቅ እድልሽ ከፍ ስለሚል ነው። በተጨማሪም በቤተሰብሽ ውስጥ በተለይ በእናትሽ ወገን መንታ የወለደች የቅርብ ዘመድ ያለሽ እንደሆን ከፍ ያለ መንታ የማርገዝ እድል አለሽ።

መንታ ያረገዘች እናት ለእርግዝና የሚያስፈልጓት ንጥረ ነገሮች መጠን ከፍ ይላል። ከነዚህ ዋንኛው ግን ፎሊክ አሲድ የተባለው ንጥረ ነገር ነው። በቀን መውሰድ ከሚገባት መጠን በመንታ እርግዝና ጊዜ ሁለት እጥፍ ያስፈልጋታል። ፎሊክ አሲድ ለእርግዝና በተለይም ለፅንሱ ጤንነት በጣም አስፈላጊ ንጥረ ነገር ነው። ይህ ንጥረ ነገር በክኒን መልክ ተዘጋጅቶ ስለሚቀርብ የምትከታተልሽን ሃኪም እርግዝናሽን እንዳወቅሽ እንድትሰጥሽ መጠየቅ ጥሩ ሃሳብ ነው።

በመንታ እርግዝና ጊዜ በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ሳምንታት የሚሰማው ማቅለሽለሽና ማስታወክ የባሰ ሊሆን ይችላል። ይህም የሚሆነው የችግሩ መንስኤ ነው ተብሎ የሚታመነው ሆርሞን ኤች.ሲ.ጂ (H.C.G) Human Chorionic Gonadotropin በመንታ እርግዝና ጊዜ መጠኑ ከባለአንድ ፅንስ እርግዝና ከፍ ያለ ስለሚሆን ነው። ጉዳዩ ብዙም ሊያሳስብሽ አይገባም። እንደማንኛውም እርግዝና ከ12ኛው-18ኛው ሳምንት ላይ ይተውሻል።

በማህፀንሽ ያሉት ፅንሶች ሁለት እንደመሆናቸው በእርግዝናሽ ወቅት የምትጨምሪው ኪሎ ከሌሎች እናቶች የበለጠ ይሆናል።

መንታ እርግዝና በሚኖርሽ ጊዜ በማህፀን ደም የመታየት፣ በእርግዝና ምክንያት የሚከሰት የደም ግፊት በሽታ፣ በእርግዝና ምክንያት የሚከሰት የስኳር በሽታ፣ ያለጊዜው የሚመጣ ምጥ እና ሌሎችም የእርግዝና ችግሮች የመከሰት እድላቸው ከፍ ስለሚል የእርግዝና ክትትልሽ የበለጠ ጠበቅ ያለ ይሆናል። ይህም ማለት በርከት ያሉ የሐኪም ቀጠሮዎች እና ተጨማሪ ምርምራዎች ይደረጉልሻል ማለት ነው።

ከላይ እንደተገለፀው መንታ እርግዝና ምጥ ቀደም ብሎ እንዲመጣ ምክንያት ስለሚሆን ሌሎች እናቶች በአብዛኛው በ40ኛው ሳምንት ሰሞን ምጥ ሲይዛቸው አንቺ ከ 36-37ኛው ሳምንት ላይ ምጥ ሊጀምርሽ ይችላል። በተጨማሪም በመንታ እርግዝና ጊዜ ሊከሰቱ በሚችሉ የተለያዩ የእርግዝና እክሎች ምክንያት በቀዶ ጥገና የመውለድ እድልሽ ከፍ ያለ ይሆናል።

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.