(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
child_asthmaየአስም ሕምተኛ ከሆኑ ስለአስም ሕመም ቀስቃሽ ስለሆኑ ሁኔታዎች በሚገባ ሊያውቁት ይገባዎታል፡፡

የአስም ሕመምዎን የሚቀስቅሱ ሁኔታዎችን ማስወገድ ሕመሙ እንዳይነሳብን ይረዳል፡፡

1) ሲጋራ ማጤስ

ሲጋራ ማጤስ ጉዳትን የሚያስከትል እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ለአስም ሕመምተኞች ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ሕመሙን ስለሚቀሰቅስ ሲጋራን የምናጤስ ከሆነ ልናቆም ይገባል፡፡

2) በቤት ውስጥ የሚገኙ ተባዮች

በቤትዎ ውስጥ የሚገኙ ተባዮች ለአስም ሕመም መቀስቀስ ምክንያት ሊሆኑ ስለሚችሉ ተባይ ማጥፊያ በመጠቀም ማጥፋት ተገቢ ነው፡፡

3) የቤት እንስሳዎች

በቤትዎ የሚያሳድጓቸው የቤት እንስሳት የፀጉራቸው ብናኝ አስም ቀስቃሽ ስለሚሆን የእንስሳቱን ንፅህና መጠበቅ እና ከተቻለ ከአስም ሕመምተኞች አካባቢ እንዲርቁ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

4) ሻጋታ

በሞቃታማ ጊዜያት በቤትዎ ውስጥ ሻጋታ ሊፈጠር ስለሚችል የአስም ሕመምዎን ይቀሰቅሳል፡፡ ስለዚህም ቤትዎን በሚገባ ማፅዳት ያስፈልጋል፡፡

5) የአካባቢ አየር ብክለት

ከፋብሪካ፣ከመኪና እና ከሌሎች ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች የሚወጡ አየርን የሚበክሉ ሽታዎች የአስም ሕመምን ስለሚቀሰቅሱ አካባቢያችንን በማፅዳት የግላችንን አስታዋፅኦ ማበርከት ይገባናል፡፡

6) ከከሰል ወይንም ከእንጨት ማቃጠል የሚፈጠር ጭስ

እነዚህን ዓይነት ጭሶች በምንተነፍስበት ጊዜ የአስም ሕመምን የመቀስቀስ ሁኔታዎችን እጅግ ይጨምራሉ፡፡

7) ሌሎች ቀስቃሽ ሁኔታዎች እንደ ጉንፋን ሕመም፣አለርጂዎች፣ ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣የአየር ንብረት ለውጦች፣ቅዝቃዜ እና ሽቶዎች የአስም ሕመምን ሊቀሰቅሱብን ይችላሉ፡፡

እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ

ጤና ይስጥልኝ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.