የጡት ካንሰር

የጡት ካንሰር ማለት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የጡት ሴሎች ዕድገት ማለት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በዚህ በሽታ የሚጠቁት ሴቶች ቢሆኑም የጡት ካንሰር በወንዶችም ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡

breast cancer1የጡት ካንሰር ዋነኛ ምልክቶች  ዕጢ፣ እብጠት እና የቆዳ ለውጥ ሲሆኑ አንዳንድ ጊዜ የጡት ካንሰር ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ ሊከሰት ይችላል፡፡ እነዚህ ምልክቶችም የሚከሰቱባቸው ሰዎች ግዴታ በጡት ካንሰር በሽታ ተይዘዋል ማለት አይደለም፤ ነገር ግን እነዚህን ምልክቶች ካዩ ወደ ክሊኒክ በመሄድ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ፡፡

በጡት ላይ የሚደረግ የግል ፍተሻ  በየወሩ ቢደረግ ጠቃሚ እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። በማንኛውም ዕድሜ ላይ ያሉ ሴቶች ይህን በማድረግ ራሳቸውን ከጡት ካንሰር መጠበቅ እንደሚችሉም  ይመክራሉ፡፡ ይህን ለማድረግ ምቹ ጊዜ የወር አበባ መጥቶ ከሄደ በኃላ በሚከቱሉት ቀናት ቢሆን ይመከራል፡፡ አብዛኞች ሴቶች የራሳቸውን የጡት ካንሰር የሚያገኙት በጡቶቻቸው ላይ ያለውን ለውጥ በመመልከትና በጡታቸው አካባቢ ያለውን ስሜታቸውን በመረዳት ነው።

የጡት ካንሰር ምርመራ  መጀመር ያለበት ምንም ዓይነት የበሽታው ስሜት ባይሰማዎትም ጭምር ነው፡፡ በተለይ ከ40 ዓመታቸው በላይ ያሉ ወይም በቤተሰባቸው ውስጥ የጡት ካንሰር ታሪክ ያለባቸው ሴቶች በየሁለት ዓመቱ አንዴ የማሞግራም ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ፡፡ ማሞግራም አነስተኛ ጨረር በመጠቀም ጡቶችን በሁለት ከፕላስቲክ በተሰሩ ጠፍጣፋ ትሪዎች መሃከል አድርጎ በመጫን ከተለያየ አቅጣጫ ምስልን በማንሳት የሚደረግ የጡት ምርመራ ነው፡፡

በጡት ላይ በሚደረግ ፍተሻ ወቅት የጡት እባጭ የሚገኝባቸው ታካሚዎች በተጨማሪ የአልትራ ሳውንድ እና የኤም.አር.አይ (MRI) ምርመራ ሊታዘዝላቸው ይችላል፡፡ ከነዚህ የተገኘውም ውጤት አጠራጣሪ ሆኖ ሲገኝ ከእባጩ ላይ በመርፌ ናሙና በመውሰድ (Fine Needle Assessment ወይም Biopsy) ካንሰር መሆኑን ወይም አለመሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እባጩ ካንሰር ያልሆነ እጢ (benign tumor) ሆኖ ይገኛል፡፡ ካንሰር የሆነ እባጭም (malignant tumor) በሚገኝበት ጊዜ በቶሎ እርምጃ በመውሰድ በዘመናዊ ህክምና ታክሞ መዳን ይቻላል፡፡

የጡት ካንሰር ደራጃዎችና ክፍሎች

የጡት ካንሰር አምስት ደረጃዎች እና ሶስት ክፍሎች/ይዘቶች አሉት፡፡ ደረጃዎቹ የሚወሰኑት በእጢው የትልቀት ልክ፣ በሊምፍ ኖድ ውስጥ በመሰራጨቱ፣ እና በሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨቱ ሲሆን ክፍሎቹ ደግሞ በእጢው የዕድገት ፍጥነት ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡

ደረጃ 0

በዜሮ ደረጃ የሚገኘው የጡት ካንሰር በወተት ማፍሰሻ ትቦ ውስጥ የተወሰነ (ductal carcinoma in situ) ሲሆን የሚታይ የካንሰር ሴል ላይኖር ይችላል፡፡

ደረጃ 1

በአንደኛ ደረጃ የሚገኘው የጡት ካንሰር እጢ ስፋቱ ሲለካ ከ2 ሳ.ሜ. የማይበልጥ እና ከወተት ማፍሰሻ ትቦ  ወጥቶ መስፋት የጀመረ ካንሰር ወይም በጡት ውስጥ እጢ ሳይኖር በሊምፍ ኖድ (lymphe node) ውስጥ ከ0.2-2 ሚ.ሜ የሚደርስ የካንሰር ሴሎች ሲገኙ ነው፡፡

ደረጃ 2

በሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው የጡት ካንሰር እጢው ከ2-5 ሳ.ሜ.የደረሰ እና ወደ ሊምፍ ኖዱ (lymphe node) የተሰራጨ ወይም ያልተሰራጨ ነው፡፡ የጡት ካንሰር እጢ ባይገኝም ከ2 ሚ.ሜ የሚበልጡ የካንሰር ሴሎች ከ1-3 የሚደርሱ አክሲለሪ ሊምፍ ኖዶች (axillary lymph nodes) ውስጥ ከተገኙ በዚህ ደረጃ ውስጥ ይጠቃለላል፡፡

ደረጃ 3

በሶስተኛ ደረጃ የሚገኘው የጡት ካንሰር ከ5 ሳ.ሜ. ከበለጠና ከ0.2-2 ሚ.ሜ የሚደርሱ የካንሰር ሴሎች በሊምፍ ኖዶች ውስጥ ከተገኙ፣ ወይም ምንም እጢ ሳይገኝ ከ4-9 የሚደረሱ ኦክሲለሪ ሊምፍ ኖዶች (axillary lymph nodes) ውስጥ የካንሰር ሴሎች ከተገኙ፣ ወይም እጢው ወደ ደረት ክፍልና ወደቆዳ ከተስፋፋ ነው፡፡

ደረጃ4

በአራተኛ ደረጃ የሚገኘው የጡት ካንሰር ከጡቱና ከአጠገቡ ካሉ ሊምፍ ኖዶች አልፎ  ካንሰሩ በሳንባ፣ ራቅ ባሉ ሊምፍ ኖዶች፣ በቆዳ፣ በአጥንት፣ በጉበትና በአንጎል ላይ የተሰራጨ ሰሆን ነው፡፡

ክፍል 1

በአንደኛ ክፍል (ዝቅተኛ ክፍል) ያሉ የካንሰር ሴሎቹ ከተለመደው ሴሎች ጋር ሲነፃፀሩ ልዩነት ያላቸው ሲሆን በዝግተኛ ፍጥነትም የሚባዙ ናቸው፡፡

ክፍል 2

በሁለተኛ ክፍል ያሉ የካንሰር ሴሎች በመካከለኛ ፍጥነት የሚባዙ ሲሆኑ የተለመደውን ጤነኛ ሴሎችን አይመስሉም፡፡

ክፍል 3

በሶሰትኛ ክፍል ያሉ የካንሰር ሴሎች በፈጣን ሁኔታ የሚባዙ ሲሆን በዓይነታቸው ከተለመደው ጤነኛ ሴሎች እጅግ በጣም የተለዩ ናቸው፡፡

<em “mso-bidi-font-style:=”” normal”=””>የጡት ካንሰር ህክምና  አብዛኛውን ጊዜ የሚጀመረው የቀዶ ጥገና በማድረግ ካንሰር የሆነውን እባጭ በማስወገድ ሲሆን ይህን ደግሞ የሚወስነው እባጩ የደረሰበት ደረጃ ነው፡፡

የጡት ካንሰር  ሶስት አይነት ህክምና ይኖረዋል

1.      ጨረር (Radiotherapy)
2.     ኬሞ ቴራፒ (Chemotherapy)
3.     ቀዶ ጥግና (Surgery)

አንዱ ወይም ሁሉም አይነት ህክምና ለአንድ ሰው ሊሰጥ ይችላል።

የመድሀኒት የጎኒዮሽ ጉዳት መድሀኒት በሚወስዱበት ጊዜ የሰውነት መቀነስ፣ ፀጉር ከሰውነት ላይ መርገፍ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የአፍ መቁሰል፣የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡ እንዚህን የጎኒዮሽ ጉዳቶችን መቀነስ የሚቻልበት መንገዶች ስላሉ ዶክተሮችን ማማከር አስፈላጊ ይሆናል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.