ብዙዎች ልጅ ሊወልዱ እንደሆነ ሲያውቁ በጣም ደስተኛ ይሆናሉ። አንዳንድ ወላጆች ግን የተደባለቀ ስሜት ሊኖራቸው ይችላል። ለእናቶች እርግዝና የሰውነት እንዲሁም የአስተሳሰብ ለውጥ ይፈጥርባቸዋል። ለአባቶች እውነት እውነት አልመስል ሊል ይችላል።
 
open-uri2እርግዝና ሁሌ ታቅዶ አይከሰትም፤ ሆኖም ጥንዶች በደስታ ሊቀበሉት ይችላሉ። በአንፃሩ ለረጅም ጊዜ እርግዝናን ሲሞክሩ የቆዩ ጥንዶችም እርግዝና ሲከሰት ከአቅም በላይ በሆነ ስሜት ውስጥ በመግባት ሊወዛገቡ ይችላሉ። ስለ ኑሮ አጋራቸው ትክክለኛነት፣ ልጅ ለመውለድ ትክክለኛ ጊዜ ስለመሆኑ፣ እንዲሁም ወላጅ ለመሆን ብቁ ስለመሆናቸው ሊጨነቁ እና ሊጠራጠሩ ይችላሉ። እንዲህ ያሉ ስሜቶች ግን ተፈጥሮአዊና የተለመዱ ናቸው። ነፍሰ ጡር በሆንሽበት ወቅት ስለሚሰሙሽ ስሜቶች ከኑሮ አጋርሽ ወይም ከሌላ ከምታምኚው ሰው ጋር መወያየት ትልቅ ጥቅም አለው።

የሴቶች ስሜት

እርጉዝ ስትሆኚ በሰውነትሽና በስሜትሽ (ፀባይሽ) ላይ ለውጦች ታስተውያለሽ። ለምሳሌ የበለጠ ግልፅ መሆን፣ ሌሎች በሚሉት/በሚያደርጉት በቀላሉ ስሜትሽ የመነካት (መከፋት)፣ በአቅራቢያሽ ያሉ የማይረዱሽ ሰዎችን ማስከፋት የሚያጋጥሙ ክስተቶች ናችው። በተለይም በእርግዝናሽ መጀመሪያ አካባቢ የስሜት አለመረጋጋትና የደስታና የመከፋት ስሜቶች ተደባልቆ የመሰማት ሁኔታ ሊኖር ይችላል። ግን አያሳስብሽ፤ ይህ የሚሆነው ሰውነትሽ አዲስ ህፃን (ፍጡር) ወደዚህ ዓለም ለማምጣት እየተዘጋጀ ስለሆነ ነው። ስለእርግዝና ማንበብ ወይንም ከሚያነቡ ሰዎች ጋር መማከር፣ እናም ቀስ በቀስ እርግዝናውን መላመድ ይቻላል።

የወንዶች/ የኑሮአጋሮች ስሜት

አባቶች (የኑሮ አጋሮች) የባለቤታቸውን እርግዝና ሲያውቁ ደስታና ኩራት ከጭንቀት ጋር ተቀላቅሎ ሊሰማቸው ይችላል። ስለወደፊት ሁኔታ ሃሳብ፣ “ምን አይነት ወላጆች እንሆናለን”፣ “የባለቤቴ ጤና እንዴት ይሆን?” የሚሉ ጥያቄዎች ማንሳት የተለመደ ነው። በዚህ ሁኔታ ካለፉ የቅርብ ወዳጆች ጋር መማከር እና መወያየት ብዙ መልሶች ይሰጣል። እናቲቱ ለእርግዝና ክትትል ወደ ነርሷ/ ሐኪሟ ስትሄድ አብሮ በመሆን ሊኖሩ የሚችሉትን ጥያቄዎች በማንሳት መረዳትም ተገቢ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.