_73480118_180404557
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሴቶች በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ወራት አነስተኛ ወይም መካከለኛ መጠን ያለው አልኮል ቢወስዱ ፅንሱ ላይ ችግር እንደማያጋጥም አንድ ጥናት ጠቆመ።

በብሎግ ጆርናል ለህትመት የበቃው የዴንማርክ ጥናት እንደሚያሳየው በሳምንት ከአንድ አስከ ስምንት መለኪያ አልኮል በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ቢወስዱ ለጉዳት አያጋልጣቸውም።

ሆኖም ከፍተኛ መጠን ያለው መጠጥ በእርግዝና ጊዜ መውሰድ ለውርጃ፤ ለተለያዩ የፅንስ በሽታና የፅንስ ክብደት መቀነስ እንደሚያጋልጥም ጥናቱ ጠቁሟል።

የዴንማርክ ተመራማሪዎች በእርግዝና ወቅት ስለሚወሰድ የአልኮል መጠጥና ተያያዥ ጉዳዮች አምስት ያህል ጥናታዊ ጹሑፎች ያዘጋጁ ሲሆን፤ በመጀመሪያ የእርግዝና ወራት ውስጥ የሚገኙ 1ሺ 600 ነፍሰጡር ሴቶችን በጥናታቸው አካተዋል።

በጥናቱ ከተካተቱት ውስጥ ግማሾቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረገዙ ሲሆኑ፤ ሲሶዎቹ ደግሞ በእርግዝና ወቅት እያጨሱ የሚገኙ ናቸው።

ሁሉም ስለሚወስዱት የአልኮ መጠን ጥያቄ ቀርቦላቸው ከአንድ እስከ አራት  መለኪያ በአማካኝ በሳምንት እንደሚወስዱ ገልፀዋል። በጥናቱ ወቅት በእርግዝና ወቅት ምንም አይነት መጠጥ የማይጠጡ ሴቶችም ተካተዋል።

ተመራማሪዎቹ አልኮል የሚጠጡ ነፍሰጡር እናቶች በሚወልዷቸው ልጆች ላይ መጠጡ የሚያሳድረው ተፅዕኖ እንዳለው ለማየት የሞከሩ ሲሆን፤ መጠጥ የሚጠጡ እናቶች የወለዷቸው ልጆች እድሜያቸው አምስት አመት ከሞላቸው በኋላ በህጻናቱ የአእምሮ ልቀት፣ የትኩረት ደረጃና የአእምሮ እቅድ ክህሎት ደረጃ ላይ፣ ነገሮችን የማደራጀትና እራስን የመቆጣጠር ክህሎታቸው ሲመዘን ምንም ችግር አላጋጠማቸውም።

በተጨማሪም በመጀመሪያ የእርግዝና ወራቶች ውስጥ እናቶቻቸው በሳምንት ከአራት እስከ ስምንት መለኪያ አልኮ ይወስዱ የነበሩ እናቶች ልጆች እናቶቻቸው አልኮን ከማይወስዱት ጋር ሲነጻጸር ምንም ልዩነት አያሳይም።

ነገር ግን በእርግዝና ወቅት በሳምንት ከዘጠኝ መለኪያ በላይ ይወስዱ ከነበሩ እናቶች የተወለዱ ህጻናት የትኩረት ጥልቀት ባህሪ ችግር እንደሚታይባቸው ጥናቱ አረጋግጧል።

የአርሃስ ዩኒቨርሲቲ የጥናቱ ዋና አስተባበሪ የሆኑት አልሪክ ሹለር ኬስ ሞዴል እና የኮፐንሃገን ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ኤሪክ ላይኪ ሞርትሰን እንደገለጹት፤ እናቶች  በእርግዝና ወቅት ለከፍተኛ አልኮል የሚጋለጡ ከሆነ የሚወልዷቸው ህጻናት ከነርቭ ጋር ተያያዥነት ላለቸው ችግሮች ተጋላጭ ይሆናሉ።

ጥናቶቹ እንደሚያስረዱት ከአነስተኛ እስከ መካካለኛ መጠነ ያለው አልኮል በእርግዝና ወቅት የሚወስዱ እናቶች ልጆቻቸው አምስት አመት ሲሞላችው ለተጠቀሱት ችግሮች አይጋለጡም።

በእንግሊዝ የሮያል ኮሌጅ የወሊድና የማህፀን ህክምና ማዕከል ቃል አቀባይና የወሊድ አማካሪ ፓትሪክ ኦብራይን በበኩላቸው፤ ጥናቱ ቀደም እንዳሉት ጥናቶች  የሴቶችን የኋላ ታሪክ ብቻ ከማጥናት ይልቅ ሴቶቹ ነፍሰጡር  በሆኑበት ወቅት ምን ያህል የአልኮል መጠን እንደሚወስዱ መጠየቃቸውና የልጆቻቸውን ሁኔታ ለረጅም ጊዜ በመከታተል የባህሪ ለውጦቻቸውን በማየት የተካሄደ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

እንዲሁም ሴቶች በእርግዝና ወቅት ከአልኮል እንዲታቀቡ የሚመክር ሲሆን፤ ለመጠጣት ከወሰኑም ከ12 ወራት የእርግዝና ጊዜ በኋላ በሳምንት ከአንድ ወይም ከሁለት መለኪያ እንዳይበልጥ ያስጠነቅቃል።

እንደ ዶክተር ኦብራይን ገለፃ የጥናቱ ግኝት የሚያሳየው ከአነስተኛ አስከ መካከለኛ መጠን ያለው አልኮን የሚወስዱ እናቶች በልጆቻቸው ላይ ምንም አይነት የጤና ችግር እንደማይፈጠር ቢሆንም በእንግሊዝ ለነፍሰ ጡሮች ከሚመከረው የአልኮል መጠን በላይ እንዲወስዱ የሚያደርግ መሆን የለበትም።

በሮያል ኮሌጅ የጤና ትምህርት ክፍል በበኩሉ ነፍሰጡር ሴቶች በእርግዝና ወቅት ስለሚወስዱት የአልኮል መጠን ለማወቅ ከፈለጉ የህክምና ባለሙያዎችን ማነጋገር ይገባል ብሏል።

በዴንማርክ የአንድ ሰው ሳምንታዊ የመጠጥ ፍጆታ በአማካኝ 12 ጋሎን ሲሆን፤ በእንግሊዝ ደግሞ 7 ነጥብ 9 ጋሎን መሆኑን መረጃዎች ይጠቁሟሉ።

በእንግሊዝ ነፍሰጡር እናቶች መጠጥ እንዳይወስዱ ምክር የሚሰጣቸው ቢሆንም ባለሙያዎች ግን ያረገዙ ሴቶች በሳምንት ከአንድ ወይም ከሁለት መለኪያ ያልበለጠ ቢወስዱ ችግር እንደማይፈጥርባቸው ይናገራሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.