ግርማ በላቸዉ ጉተማ (ሌክቸረር መቐለ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት)
medicine-courierየሰዉ ልጆችና መድሃኒቶችን  የተለያዩ የበሽታ ዓይነቶችን ለማከም ወይም ለመፈወስ የመጠቀም ሂደት እጅግ በጣም ረጅም ሊባል የሚችል የታሪክ ቁርኝት ያላቸዉ ነገሮች ናቸዉ ፡፡ መድሃኒቶችበዘመናዊዉ ማቀነባበሪያ ስርዓት ተዘጋጅተዉና ተመርተዉ (at large Industrial level) ለገብያ መቅረብ እስከጀመሩበት እስከ 19ኛዉ መቶ ክ/ዘመን ድረስም የሰዉ ልጆች መድሃኒቶችን ከተለያዩተፈጥሮአዊ ይዘት ካላቸዉ ነገሮች አዘጋጅተዉና ቀምመዉ ሲጠቀሙ መቆየታቸዉን ታሪክ ይነግረናል፡፡
በኢትዮጵያም ዘመናዊ መድሃኒቶች ከዉጭ ሃገራት መግባት እስከጀመሩበት እስከ ሃፀይ ልብነድንግል ዘመነመንግስት ድረስ ህዝቡ ሙሉ በሙሉ መድሃኒቶችን ከዱር በመሰብሰብ ቀምሞና አዘጋጅቶ(በተለይም በባህል መድሃኒት አዋቂዎች በኩል) ይጠቀም እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን አሁንም ድረስ እነዚሁ የባህል መድሃኒት አዋቂዎች በጣም ጠንካራ ሊባል የሚችል ሚና በህብረተሰቡ ዉስጥእንዳላቸዉ ይታወቃል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘመናዊዉ የመድሃኒት ትምህርት (Modern Pharmaceutical Education) በሌላዉ ዓለም ነጥሮ ወጥቶ እንደ አንድ በጣም አስፈላጊ የሙያ ዘርፍ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትዉስጥ መሰጠት የጀመረዉ በ13ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ማለትም በ1278 ዓ.ም አካባቢ የነበረ ሲሆን በኢትዮጵያ ይህ ተግባር የተጀመረዉ በ20ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ማለትም በ700 ዓመታትዘግይቶ እንደነበረ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ በዚሁ ወቅት በሃገሪቱ መስፋፋት ከጀመረዉ አጠቃላይ የከፍተኛ ትምህርት ጋር ተያይዞ በ1950ቹ መጀመሪያ በተከፈተዉ የመጀመሪያዉ የሃገሪቱየከፍተኛ ትምህርት ተቋም ማለትም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር የፋርማሲ ት/ክፍል ተመስርቶአል፡፡ ስለሆነም ይህ ት/ክፍል ከአንጋፋዎቹ የዩኒቨርሲቲዉ መርሃግብሮች (programs) መካከል አንዱየነበረ ሲሆን በ1970 አካባቢ ወደ ሙሉ ፋከልቲነት አድጎ ዘመናዊዉን የመድሃኒት ሳይንስ በቅርቡ የትምህርት ክፍሉ በሃገሪቱ ዉስጥ እየተስፋፉ በሚገኙት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መስፋፋትእሰከጀመረበት ጊዘ ድረስ ብቸኛዉ የፋርማሲ ትምህርት ማስተማሪያ ሆኖ ቆይቶኣል፡፡ በዚሁ ከግማቨ ምእተ ዓመት በላይ በዘለቀዉ የሃገሪቱ የዘመናዊ የፋርማሲ ትምህርት ታሪክ የስርዓተ ትምህርቱአጠቃላይ ይዘት (curricular content) እና የትምህርቱ አሰጣጥ የመድሃኒት ምርት ተኮር (product-centered) እንደነበረ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት ዲን ዶ/ር ተፈሪ ገዲፍከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደለጉት ቃለመጠይቅ ገልጠዉ ነበር፡፡
ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችና አሁን ዘርፉ በኢትዮጵያ ያለበት ደረጃ
የፋርማሲ አገልግሎት ዓለም አቀፍ ይዘት ከምን ጊዘዉም በበለጠ ህመምተኛ ተኮር (patient-centered) እየሆነ የመጣ ሲሆን በአብዛኛዉ የዓለማችን ሃገሮች ስርዓተ ትምህርቱም በዚሁ መንፈስእንዲቃኝ ተደርጎኣል፡፡ በኢትዮጵያም ይህንኑ ሁኔታ ለመከተል ትምህርቱን በሚሰጡ ተቋማት ያላሰለሰ ጥረት በመደረግ ላይ ያለ ሲሆን በመንግስት በኩል እየተደረገ ያለዉ ድጋፍና እገዛ የሚገባዉን ያህልእንዳልሆነ የዚህ ዕሁፍ አቅራቢ መገንዘብ ችሎኣል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በሃገሪቱ አጠቃላይ የመድሃኒት አገልግሎት ዘርፍ ዉስጥ በሰፊዉ ተሰማርተዉ የሚገኙት አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ለመስጠት ተገቢዉን የትምህርት ደረጃ ያልቀሰሙና ቢበዛበዲፕሎማ ደረጃ ያሉ ዝቅተኛ የመድሃኒት ባለሙያዎች (Pharmacy technicians) ሲሆኑ የዚህ ሁኔታ አዲስ አበባንና ዋና ዋናዎቹን የክልል ከተሞች ጨምሮ በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች ጎልቶመዉጣት ለአገልግሎቱ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ መገኘት እንደምክኒያትነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡
አሁን ዘርፉ ያለበት ችግሮች አመጣጥና ጠቋሚ መፍትሔዎች
ማህበረሰቡ ከአጠቃላይ የመድሃኒት አገልግሎት ዘርፍ ማግኘት የሚገባዉን ደረጃዉን የጠበቀ አገልግሎት እንዳያገኝ መነሻ የሆኑት ችግሮች ምንጫቸዉ ጠቅለል ተደርገዉ በሁለት ሊፈረጁ ይችላሉ፡፡የመጀመሪዉ በዘርፉ በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ (ማለትም በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ የሰለጠነ) ሙያተኛ የሰለጠነበት ስርዓተ ትምህርት ግድፈቶች አገልግሎቱን አሁን ሌላዉ ዓለም ባለበት ደረጃለመስጠት የማያበቃዉ መሆኑ ሲሆን አንድ ሙያተኛ እዉቀቱንና ክህሎቱን በቀጣይነት ማሻሻሉንና አገልግሎቱን ለመስጠት ብቁ ሆኖ መቀጠሉን ለማረጋገጥ የሚያስችልና በሌላዉ ዓለም እጅጉንየተለመደዉ ስርዓትም በኢትዮጵያ አልተዘረጋም፡፡ የዚህ ስርዓት አለመኖር አንድ ፋርማሲስት በግሉ ከመድሃኒት ጋር በተያያዘ ማንኛዉንም የአገልግሎት ፍቃድ ለማግኘት ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀ አምስትዓመታትን በስራዉ ዓለም መቆየት ብቻ እንዲጠበቅበት ያደረገ ሲሆን ይህም ለአገልግሎቱ በእጅጉ መቀጨጭ ከፍተኛዉን አስተዋጥኦ እንዳደረገ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ሁለተኛዉና በዋነኛነት የሃገሪቱንየመድሃኒት አገልግሎት ዘርፍ በእጅጉ እንዲቀጭጭ ያደረገዉ ኢትዮጵያ በየትኛዉም የአለማችን ሃገሮች ባልተለመደ መልኩ መድሃኒቶች በዝቅተኛ የፋርማሲ ሙያተኞች (የዲፕሎማ ምሩቃን እና ከዚያበታች ባሉ) እጅ እንዲገቡ ማድረጓ ሲሆን ይህም ሁኔታ ከዚህ ቀደም በዘርፉ ከፍተኛ የሰዉ ሃይል እጥረት የነበረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የተደረገ እንደሆነ እየታወቀ ሳይስተካከል በዚያዉ መቀጠሉ ችግሩንበእጅጉ አባብሶታል፡፡ ስለሆነም አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት የመድሃኒት ስርጭት ስራዎች የሚሰሩት የተማሩበት ስርዓተ ትምህርት እንኳን በግልዕስራዎቹን በብቸኝነት (independently) መስራት እንደማይችሉ በሚደነግግላቸዉ ዝቅተኛ የፋርማሲ ሙያተኞች መሆኑ ጉዳዩን በእጅጉ አሳሳቢ  አድርጎታል፡፡
ስለሆነም አሁን ሃገሪቱ በከፍተኛ መጠን እያፈራች የምትገኘዉ በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰዉ ሃይል በዘርፉ ያጋጥም የነበረዉን ችግር ከመሰረቱ እየቀረፈ ስለሚገኝ ትክክለኛዉን ሙያ ከትክክለኛዉባለሙያ ጋር የማገናኛዉ ወቅት አሁን መሆን ይገባዋል፡፡ በተጨማሪም ሙያዉና ሙያተኛዉ በተገናኙበት ሁኔታም እንኳን ቢሆን በሌላዉ ዓለም እንደተለመደዉ የስራ ላይ ተከታታይ ትምህርት (on service continuing education) እንዲሁም የሙያ ፈቃድ ለማዉጣትም ሆነ ለማሳደስ የሚሰጥ ፈተና (prerequisite exam for licensure and re-licensure) የሚኖርበትን መንገድ መቀየስበዘርፉ የሚታየዉን ከፍተኛ የሆነ የአገልግሎት መጓደል በእጅጉ ሊያሻሽለዉ ይችላል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.