(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) |

How-to-lose-weight-fastአመጋገብዎን እየተቆጣጠሩ እና በመደበኛ ሁኔታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እያደረጉ ክብደትዎ ግን ሊቀንስ አለመቻሉ ያሳስብዎት ይሆናል፡፡

ከዚህ በታች ለክብደትዎ አለመቀነስ አንዳንድ ምክንያቶች ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን እገልጻላችኋለሁ፡፡

1) መድኃኒቶች

አንዳንድ መድኃኒቶች ለምሳሌ አንዳንድ የወሊድ መቆጣጣሪያዎች፣ ሆርሞንን ለመተካት የሚወስዱ መድኃኒቶች እና የመሳሰሉት ከጥቅማቸው ባለፈ አንዳንድ ጉዳቶችን በተጓዳኝነት ያስከትላሉ ከነዚህም ጉዳቶች አንዱ የሰውነት ክብደት መጨመር ነው፡፡

2) የንጥረ ነገሮች እጥረት

የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ለማድረግ አቅም የማጣትዎ እና የድካም ስሜት መሰማትዎ መንስዔ በአንዳንድ የንጥረ ነገሮች ዕጥረት ምክንያት ለምሳሌ ቫይታሚን ዲ፣ማግኒዝየም እና አይረን ሲሆን ይህም የካፊን እና ጣፋጭ ምግቦችን እንደ ኃይል ማግኛ እንድንጠቀም ስለሚያደርገን የሰውንት ክብደታችንን መቀነስ አንችልም፡፡

3) ዕድሜ

ዕድሜዎ የገፋ ከሆነ የሰውነትዎ ሜታቦሊዝም (Metabolism) ከሌላው በተለየ ሁኔታ እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ ስለዚህም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በዕድሜ ለገፉ እና ክብደት ለመቀነስ ለሚፈልጉ ሰዎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ መንገድ ነው፡፡

4) የሚመገቡትን ምግብ ይምረጡ

አንዳንድ ፕሮቲኖች ከሌላው በተለየ በፍጥነት የሚቃጠሉ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ በዝግታ ነው፡፡ ስለዚህ የምንመገባቸው ምግቦች ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦች መሆናቸውን መምረጥ ለክብደት መቀነስ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡

5) የአጥንት ሕመም

ማንኛውንም ዓይነት የአጥንት እና የመገጣጠሚያ ሕመም ያለብዎ ከሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከማድረግ ይታገዳሉ፡፡ ስለዚህም ሕመም ያለብዎ ከሆነ ሕክምናን መውሰድ አልያም ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን እና እንደ ውሃ ዋና ያሉ ስፖርቶችን በማድረግ ክብደትዎን መቀነስ ይችላሉ፡፡

6) መደበት

የመደበት ሕመም ያለብዎ ከሆነ በተዘዋዋሪ የክብደት ችግር ይኖርዎታል፡፡ በአብዛኛው የመደበት ሕመም ተጠቂዎች ምግብን እንደጓደኛቸው የማየት ችግር ይታይባቸዋል፡፡ ይህም ለክብደት መጨመራቸው መንስዔ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ለመደበት ሕመም ተብለው የሚሰጡ መድኃኒቶችም የሰውነት ክብደትዎ መጨመር ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

7) ዝግተኛ የሆነ የምግብ አፈጫጨት ሂደት ያለዎ ከሆነ

ዝግተኛ የሆነ የምግብ መፈጨት ሥርዓት ያላቸው ሰዎች ለክብደት መጨመር ይጋለጣሉ፡፡ የሆድ ድርቀት የሚያስቸግርዎ ከሆነ ፈሳሽን በብዛት መውሰድ እና በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ የሆድ ድርቀትዎን ለመከላከል እና የምግብ መፈጨትን እንዲፋጠን ያደርጋል፡፡

እባክዎን ለወዳጅዎችዎ ያካፍሉ!!!
ጤና ይስጥልኝ

ይህንን ምክር በእንግሊዘኛ ያዘጋጀሁት ሲሁን በዚህ አድራሻ መመልከት ይችላሉ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.