ኡመር ታፈሰ ከአፕል ቫሊ –

kissing-lessonsመሳሳም 29 የፊት ጡንቻዎች እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋል – ፍቅረኛሞች ሲሳሳሙ ቅባቶች፣ ማዕድን ያላቸው ጨዎችንና ፕሮቲኖችን የመሳሰሉ ንጥረ ነገሮች ያሉበትን ምራቅ ይለዋወጣሉ፡፡ የቅርብ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከላይ ያሉትን ንጥረ ነገሮች መለዋወጥ የሰውነትን በሽታ የመቋቋም አቅም ከፍ ያደርጋል፡፡ – በመሳሳም ወቅት 66 ፐርሰንት የሚሆኑት ዓይናቸውን ይጨፍናሉ፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በፍቅረኞቻቸው ፊት ላይ የሚፈጠረውን የደስታ ስሜት በማየት እርካታን ያገኛሉ፡፡

– በአሜሪካ በተከናወነው ጥናት መሰረት አንዲት አሜሪካዊት ሴት ከማግባቷ በፊት በአማካይ ከ80 ወንዶች ጋር ትሳሳማለች፡፡ – ከንፈር ላይ ያለው ስሜት የእጅ ጣቶች ላይ ካለው ስሜት 200 እጥፍ ይበልጣል፡፡ – ወደ ስራ ሲሄዱ ቻው በማለት የሚስቶቻቸውን ከንፈር የሚስሙ ወንዶች ይህን ከማያደርጉ ወንዶች ተጨማሪ አምስት ዓመት የመኖር እድል አላቸው፤ የሚስቶቻቸውን ከንፈር የማይስሙ ባሎች ለትራፊክ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ ነው፡፡ – መሳሳም ሴትን ዘና እንድትል በማድረግ ከጭንቀት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ያስወግድላታል፡፡ – በአማካይ አንድ ሰው በህይወቱ ሁለት ሳምንታትን በመሳሳም ያሳልፋል፡፡ – በዚህች ምድር ላይ ያለ ማንኛውም ሰው የመጀመሪያው የፍቅር መሳሳም 14 ዓመት ዕድሜው ላይ ከመድረሱ በፊት የተፈፀመ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.