ከሊሊ ሞገስ

1. ኪስ /Kiss/ የሚለው ቃል ከጥንታዊው የእንግሊዝኛ ቋንቋ Lyssan የመጣ ሲሆን፣ መነሻው ደግሞ በጀርመንኛ Kussijanan ወይም Kuss የሚለው ቃል ነው፡፡ ይህም በመሳሳም ወቅት የሚደመጠውን ድምፅ ይወክላል፡፡

download2. አንዲት ቻይናዊት ፍቅረኛዋ በጆሮዋ ውስጥ ምላሱን አስገብቶ ሲስማት የጆሮ ታምቡር በመበጠሱ መስማት የተሳናት ልትሆን ችላለች፡፡ ይህንንም ሮይተርስ የዜና አውታር ዲሴምበር 8 ቀን 2008 ‹‹The kiss of Deaf Chinese Man Ruptures Girlfriends Eardrum›› በሚል ርዕስ ዘግቦት ነበር፡፡

3. ስለመሳሳም የሚያጠና ሳይንስ ፊሌማቶሎጂ /Philematology/ ይባላል፡፡

4. Kiss my Ass የሚለው የስድብ ቃል የተጀመረው ከ1705 አንስቶ ነው፡፡

5. ከንፈሮች ከጣቶች በ100 እጥፍ የበለጠ ስሜታዊ ናቸው፡፡ ብልቶች እንኳ የከንፈሮችን ያህል ስሜትን አይጭሩም፡፡

6. ወደ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑ ሰዎች በሚሳሳሙበት ወቅት ጭንቅላታቸውን ወደ ግራ ዘመም የማድረግ ልማድ አላቸው፡፡ አንዳንድ ምሁራን ይሄን ልማድ በማህፀን ውስጥ እያሉ የጀመሩት መሆኑን ይናገራሉ፡፡

7. ከጁላይ 5 እስከ 6 ቀን 2005 የለንደን ጥንዶች በመሳሳም የዓለምን ሪከርድ ጨብጠዋል፡፡ እነዚህ ፍቅረኛሞች በተጠቀሰው ቀን ለ31 ሰዓታት፣ 30 ደቂቃዎችና 30 ሰከንዶች ያለማቋረጥ ተሳስመዋል፡፡ ይህም ረጅሙ መሳሳም ተብሎ በጊነስ ተመዝግቦላቸዋል፡፡

8. በመሳሳም ወቅት በጣም ጠቃሚው ጡንቻ አርቢኩላሪስ ኦሪስ (Orbicularis Oris) የሚባለው ሲሆን፣ እሱም ከንፈሮችን የሚያፍታታ ነው፡፡

9. በፍሬንች ኪሲንግ ወቅት በፊታችን ላይ ያሉት 34ቱም ጡንቻዎች ይሳተፋሉ፡፡

10. የወንድም ሆነ የሴት ከንፈሮች ከሴት ብልት ከንፈር ጋር ይመሳሰላሉ፡፡

11. ‹‹French Kiss›› የሚለው ሐረግ እንግሊዝኛ ቋንቋን የተቀላቀለው ወደ 1923 ገደማ ነበር፡፡ ያኔ ፈረንሳዊያን ለወሲብ ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጡ ለማሳየት ሲባል የተቀመጠ ሐረግ ነው፡፡ በፈረንሳይ ይህ አሳሳም የምላስ ወይንም የመንፈስ አሳሳም ተብሎ የሚቀመጥ ሲሆን፣ ምክንያቱ ደግሞ በትክክል አሳሳሙ ከተከናወነ የሁለቱ ተሳሳሚዎች ነፍስ ወደ አንድ እንደሚገጥም ስለሚታመንበት ነው፡፡

12. በስነ ፅሑፍ ዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ስለመሳሳም የተፃፈው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1500 በታተመው The Four Vedic Sanskrit የተሰኘ መፅሐፍ ነበር፡፡

13. ሮማዊያን መሳሳምን በሶስት ክፍሎች መድበውታል፡፡

አንደኛው፡- Osculum ሲሆን የጉንጭ ለጉንጭ መሳሳም ነው

ሁለተኛው፡- Basium ሲሆን ከንፈርን መሳም ነው

ሶስተኛው፡- Svolium ሲሆን ጥልቀት ያለውን መሳሳም ይገልፃል፡፡

14. በጥልቅ ፍቅር ውስጥ የሚከናወን መሳሳም በደቂቃ 6.4 ካሎሪ ያቃጥላል፡፡ በመሆኑም 26 ካሎሪን ለማቃጠል ወይ አምስት ደቂቃ በእግር መጓዝ አልያም ለአራት ደቂዎች መሳሳም ያስፈልጋል፡፡

15. ሴት ልጅ በመሳሳም ብቻ የስሜት እርካታ ላይ ልትደርስ ትችላለች፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.