በሮማንቲክ ግንኙነት ውስጥ ላሉ ሰዎች መሳሳም ልዩ ትርጉም አለው። መሳሳም የመባዳትን ያህል ያቀራርባል፣ ያቆራኛል። በስሜት ሌላ ዓለም ውስጥ ይከታል። ድንግሎች ድንግልናቸውን በመጀመሪያ ደረጃ የሚያጡት ከናፍርታቸው ላይ ነው።

መሳሳም ፍቅረኞችን እንደ ማግኔት ያጣብቃል። ራሱን የቻለ መስተፋቅር ነው። ሁለት የሚዋደዱ ሰዎች፣ ፍቅረኞች መሆናቸውን ለዓለም የሚያበስሩት በመሳሳም ነው። መተሻሸት፣ መባዳት የሚመጣው ከመሳሳም በኋላ ነው።

መሳሳም ከወሲብ የበለጠ ክቡርና ውድ ነገር ነው። ለምሳሌ ሴተኛ ተዳዳሪዎች፣ ከንፈሮቻቸውን በጣም ለሚወዱት ወንድ ካልሆነ፣ ለማነኛውም ተራ ደንበኛ፣ ካልሰከሩ በስተቀር አያስቀምሱም።

አንድ ወንድ በአሳሳሙ ፍቅረኛውን ሊያከንፍ ይችላል። አንድ ሴት በአሳሳሟ ፍቅረኛዋን ልታከንፍ ትችላለች። አሳሳምህን የማትወድ ከሆነ የፍቅር ግንኙነታችሁ ሊቋረጥ ይችላል። አሳሳምሽን ካልወደደ ፍቅራችሁ ሊቀዘቅዝ ይችላል። ሆኖም የመሳም ጥበብን ከእናቱ ማህጸን ይዞ የሚወጣ የለም። በልምድ የሚሻሻል ችሎታ ነው። ብዙ በሳምክ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ የመሳም ጥበብን ትካናለህ። ብዙ በሳምሽ ቁጥር ጥሩ ሳሚ ይወጣሻል።

ጥሩ ሳሚ ለመሆን የግድ ወንዶች ከተለያዩ ሴቶች፣ ሴቶች ከተለያዩ ወንዶች ጋር መውጣት የለባቸውም። ከአንድ ሰው ጋር ሆኖ የመሳምን ጥበብ በመማር ጠቢብ ሆኖ መገኘት ይቻላል። የተለያዩ የመሳሳም ስልቶች አሉ። እነዚህን ስልቶች ማወቅና ማዳበር ለጥሩ የፍቅር ግንኙነት በር ይከፍታል።

አንተ ጥሩ ሳሚ ሆነህ እሷ መሳም የማትችል ከሆነች፣ እሷን መናቅና ማጣጣል የለብህም፤ አስተምራት። አንቺ ጥሩ ሳሚ ሆነሽ እሱ ግን ገና ጀማሪ ከሆነ፣ አትሳለቂበት፤ አስተምሪው። ሁለታችሁም ጥሩ ሳሚዎች ካልሆናችሁ፣ ፊልም እያያችሁ ተማማሩ። መማማር ፍቅራችሁን በይበልጥ ያጠነክረዋል።

ይህን ያውቁ ኖሯል፦

ሀ) ከንፈሮቻችን የብዙ ነርቮች መከማቻ ናቸው። ስትሳሳሙ ቁላህ የሚገተርበትና ቂንጥርሽ የሚቆምበት ምክንያት ነርቮቹ ስሜታችሁን ስለሚቀሰቅሱ ነው።

ለ) ጥናት የተደረገባቸው 40% ምዕራባውያን ወንዶች መሳሳም የወሲብ ፍላጎታቸውን በእጥፍ እንደሚጨምር ይናገራሉ።

ሐ) ጥናት የተደረገባቸው በ18 እና በ24 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 54% ምዕራባውያን ሴቶች ሌላ ሴትን ስመው እንደሚያውቁ ይናገራሉ። በ25ና በ34 የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት ደግሞ ቁጥሩ ወደ 43% ይወርዳል።

መ) ወንዶች የፈለጓትን ሴት “አሳሳሟ ደበረኝ” ብለው ከመብዳት ወደ ኋላ አይሉም። ሴቶች ግን አንድ ወንድ አሳሳሙ ካስጠላቸው ከመበዳት ሊቆጠቡ ይችላሉ።

ሠ) ፍቅረኛሽ “ቻው” ሲልሽ፣ ሁልጊዜ በቸልተኝነት ሳም አድርጎ የሚተውሽ ከሆነ፣ ፍቅራችሁ እየቀዘቀዘ ለመምጣቱ ምልክት ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.