ሳይኮሎችስት ዶ/ር ጋሪ ቻፕማን ከ30 አመት የትዳር አማካሪነት ልምዳቸው በመነሳት “አምስቱ የፍቅር ቋንቋዎች” (The Five Love Languages) በሚለው መጽሃፋቸው መሰረታዊ ብለው ያቀረብዋቸው አምስት የፍቅር ቋንቋዎች ናቸው። ፍቅር በእነዚህ አምስት መንገዶች ብቻ ይገለጻል ማለት አይደለም። ነገር ግን ሳይኮሎጅስቱ አምስቱን እንደ ዋና ዋና የፍቀር ቋንቋዎች መድበዋቸውነው።

ቋንቋዎቹ አነዱ ከሌላው አይበላለጡም። አምስቱ ቋንቋዎች እነሆ፦

make-loveቃላት፦ ፍቅር በቃላት ሲገለጽላቸው ቶሎ ሚገባቸው ፤ ሲደነቁ ፣ ሲመሰገኑ ፣ ሲሞገሱ ስሜታቸው ይሚፈነድቅ ሰዎች ዋናው የፍቅር ቋንቋቸው ቃላት ነው። ቃላት ሰዎችን ያበረታታሉ ፣ ተስፋን ያድሳሉ። ፍቅር በቃላት ሲገለጽላቸው የሚወዱ ሰዎች ፣ ለቃላት ባጣም ስሜታቸው ከሌሎች የፍቅር ቋንቋዎች ይበልጥ ቅርብ ነው። ማመናጨቅ ፣ ማንቋሸሽ ፣ ማሽሟጠጥ ፣ ማላገጥ እና የመሳሰሉት ጎጂና ኋላቀር የአነጋገር መንገዶች ፍቅር በቃላት ሲገለጽላቸው ለሚመቻቸው ሰዎች የስሜት መርዝ ናቸው። ከነዚህ ስሜትን ከሚሰብሩ አነጋገሮች ራስን ማረምና መቆጠብ ፍቅር በቃላት ከሚመቻቸው ሰዎች ጋር በደስታና በሰላም አብሮ ለመኖርና ለመግባባት እጅግ በጣም ወሳኝ ነው።

ጊዜ፦ የሚወዳቸው ሰው ሙሉ ሃሳቡን እንዲሰጣቸው ፣ ቲቪ ጠፍቶ ፣ ጎን ለጎን ተቀምጦ ፣ ወይ አብረው ጋደም ብለው ፣ ሲመች ደግሞ እጅ ለጅ ተያይዞ ሽር ሽር መሄድ የፍቅር ቋንቋቸው ይሆኑ ሰዎች ፍቅር በልዩ በቀላሉ ሚገባቸው ውዳጃቸው ጊዜ ሲሰጣቸው ነው። ከፍቅረኛቸው ጋር ልዩ ጊዜ ሲያገኙ የፍቅር ጎተራቸው የሞላል፡፡ ጊዜ ግን ካላገኙ ፤ ቸል የተባሉ ፣ ቅድሚያ ይልተሰጣቸው ፣ ምናልባትም ያልተፈለጉ ሆነው ሊሰማቸው ይችላልና ፤ ፍቅር በጊዜ ሲገልጽላቸው ለሚሹ ፍቅረኞች ለስራ ፣ ለጓደኞቻችንና ለሌሎች ምርጥ ጊዤያችንን ሰጥተን ትርፍራፊውን እንስጣችሁ ብንላቸው ችግር ይፈጠራለና ምርጥ ምርጡን ጊዜ ለፍቅረኛ ማበርከት ነው።

ስጦታ፦ ቀለበት ፣ ሽቱ ፣ አበባ ፣ ቾኮሌት ፣ ክትፎ ፣ ፍርፍር ፣ መጽሃፍ ፣ gift card … ስጦታ አይነቱ ብዙ ነው። አበባ ሲያዩ ፊታቸው ሚፈካ ፣ ቀልበት ሲሰጣቸው ሚሽኮረመሙ ጥቂት አይደሉም። ፍቅር በስጦታ ሲገለጽላቸው ቶሎ ሚገባቸው ሰዎች ስጦታ ያከብራሉ ፣ ለስጦታ ትልቅ ትርጉም ይሰጣሉ ፤ ስጦታን አስቦና ትርጉሙን አገናዝቦ የሚሰጣቸውን ሰውም ያደንቃሉ። ስጦታ ሁሉ የግድ በጣም ውድ መሆን የለበትም ፤ ባጣምም ርካሽና ዋጋ የለለው ከሆነም ትርጉሙን ሊያጣ ስለሚችል ፤ ጊዜ ወስዶ ፣ አስቦ ፣ አውጥቶና አውርዶ ስጦታ መምረጥ ስጦታን ያሳምራል። ተሯሩጦ ፣ በጥድፊያ ስጦታ ከምግዛት ፣ አስቀድሞ ረጋብሎ ስጦታ የመፈለግ ተሞክሮን ማዳበር ቁም ነገር ነው።

ስራ፦ ፍቅር በስራ መግልጽ ማለት ፤ ምግብ በማብሰል ፣ ልጆችን በመንከባከብ ፣ ቤት በማጽዳት … ማለት ነው። ሰው ሲያገልግላቸው የበላይነት ስሜት ማይሰማቸው ፣ እንዲያውም ፍቅር የሚገባቸው በሚደረግላቸው መስተንግዶና እንክብካቢ የሆነ ሰዎች ብዙ ናቸው። ለምሳሌ፦ ምግብ በስሎ ፣ በጠረጴዛ ላይ ሲቀርብላቸው ፤ ምግቡን ለማዘጋጀት የሚውስደውን ድካም ስለሚረዱ ምግብ ላዘጋጀው ሰው ልዩ ምስጋና የሚያቀርቡ ፣ የይገባኛል ስሜት ማይሰማቸው ሰዎች ፍቅር በምግባር ቶሎ የሚገባቸው ናቸው። ባላቸው ልጆች ሲንከባከብ ፣ ቤት ውስጥ አብሯቸው ደፋ ቀና ሲል ስሜታቸው ደስ የሚለውና ባላቸው እንደሚወዳቸው የሚገባቸው ሚስቶች አሉ። በባህላችን ምንም እንኳ ሴቶች የቤት ስራ ሃላፊነት ቢጫንባቸውም ፣ ወንድ ልጅ ማድቤት አይግባ የሚለውን ኋላቀር ፈሊጥ ወደ ኋላ ትተን ፣ ከትዳር ጓደኛ ጎን አብሮ መቆም ነው።

መዳሰስ፦ ትክሻና ወገብን ዳሰስ-ዳሰስ ፤ እግርና እጅን አሸት-አሸት ፤ ጸጉርን ዳበስ ፤ ጉንጭና ከፈርን ሳም-ሳም ሲደረጉ ከሌሎች የፍቅር ቋንቋዎች ይልቅ ፍቅር ቶሎ የሚጋባቸው ሰዎችም አሉ። በአደባባይ እጅ መያዝ ፣ መታቀፍ ፣ መሳም የመወደዳቸው ስሜት መገለጫ ነው። ካልተዳሰሱ ፣ ካልተዳበሱና ካልተሳሙ ፤ “ምነው ምን ተፈጠረ?” ብለው ይሰጋሉ። ፍቅር በዚህ ቋነቋ ቶሎ የሚገባቸው ሰዎች ካለተዳበሱ ይከፋቸዋል ፣ ቅር ይላቸዋልና ዳበስ-ዳበስ ማድረግ ነው። በአደባባይ ፍቅርን መግለጽ ለመጀመሪያ ሊያሳፍር ይችላል ፤ ግን ቀስ በቀስ እጅን ከመያያዝ ፣ ከዚያም ጉጭን በመሳም ራስን ማለማመድ ይቻላል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.