በኪዳኔ መካሻ (የሕግ ባለሙያ)

Kidane1983@yahoo.com

      

  • –   የግብረ ስጋ ግንኙነት ከተጀመረ በኋላ ሴቷ ፈቃደኛ አለመሆኗን መግለጿ ግንኙነቱን አስገድዶ መድፈር ያስብለዋል?
  • –   በአሜሪካ ፍ/ቤት የተዳኘ አስገራሚና ፈቅዳ ነው ወይስ ተገዳ? የሚያስብለው እውነተኛ የወንጀል ክስ ላይ የተደረገ ክርክር፤ እርሶ ዳኛ ቢሆኑ ምን ይወስኑ ነበር?

Madhuri-Dixit-Sanjay-Duttእንዴት ናችሁ? በዓል እንዴት ነበር? የዛሬ ወጋችን የእርስዎንም ዳኝነት የሚጠይቅ ነው። በአሜሪካን ሀገር በአንድ ፍርድ ቤት ታይቶ ውሳኔ ያገኘ የአስገድዶ መድፈር ጉዳይ ላይ ጁሪር ከህዝብ የተወጣጡና ተከሳሽ ጥፋተኛ ነው አይደለም ብለው በሚወስኑ ፈራጆች አንዱ ሆነው ውሳኔውን ለመስጠት ይዘጋጁ።

1 አርብ ማታ እዚያ ቦታ

ወ/ት ኬት ሳምሶን እና ማውሪስ ቬርኖን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ አብረው ሲማሩ ትውውቅ ነበራቸው። ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁም በኋላ መገናኘታቸውን ቀጠሉ። ከመተቃቀፍና ከጥልቅ መሳሳም የዘለለ ወሲባዊ ግንኙነት ግን አልነበራቸውም። ማውሪስ በድንገት ለኬት መደወሉንም እርግፍ አድርጎ ተወውና የጀመሩት ግንኙነት ተቋረጠ። ከዚያ በኋላ ለወራት ቆይተው ነበር የሁለቱም የጋራ ጓደኛቸው የሆነ ልጅ በአንድ ሰፊና የመዋኛ ገንዳ ጭምር ባለው መኖሪያ ቤት ውስጥ ባዘጋጀው ፓርቲ ላይ ነበር። በዚህ ዝግጅት ላይ ኬት እና ማውሪስ አብረው ሲደንሱ ሲጠጡ ስለነበር መፈላለጋቸው አሁንም ድረስ መዝለቁ አጠራጣሪ አልነበረም።

አብዛኛዎቹ እንግዶች ሲሄዱ ኬት እና ማድሪስ የመዋኛ ልብሳቸውን ለብሰው በመዋኛ ገንዳው ውስጥ አብረው እየዋኙ ነበር። ከመዋኛ ገንዳው አጠገብ አንዲት አነስተኛ የእንግዳ ማረፊያ ጎጆ ነበረች። ጥንዶቹ ወደ ጎጆይቱ ገቡና ልብሳቸውን አወላልቀው ከአልጋው ላይ ጋደም ብለው መጨዋወት ጀመሩ። ኬት ምንም እንኳን ለመጀመሪያ ጊዜቸው ቢሆንም ማውሪስ ብልቱን ወደ ብልቷ ሲያስገባ አልተቃወመችም። የወሲብ ግንኙነቱ ተሟሙቆ ቀጥሎ እያለ ኬት በድንገት ማውሪስን አቁም ስትል ጮኸችበት ከላይዋ ላይ እንዲነሳላትም ተማፀነችው ሆኖም ማውሪስ ውትወታዋን ቸል በማለት የእርካታ ጣሪያ ላይ እስኪደርስ የግብረስጋ ግንኙነቱን ቀጠለበት። ይህ የተከሰተው አርብ እለት ማታ ነበር። ኬት እስከመጪው ማክሰኞ ድረስ ጠበቀችና ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ፈፅሞብኛል ስትል ማውሪስ ላይ ምርመራ እንዲካሄድና ክስ እንዲመሰረት አመለከተች።

ክሱ ተመሰረተ። ከሳሽ ዐቃቤ ሕጓም ሆኑ የተከሳሽ ተከላካይ ጠበቃ እድሜያቸው በሃያዎቹ መጨረሻ ላይ የሚገኙ ሴቶች ናቸው። ተከሳሽ ማውሪስ ወርቃማ ፀጉር ያለው ገና ሃያኛ ዓመቱን የያዘ ወጣት ነው። አጭር የክስ መክፈቻ ንግግሯን ካደረገች በኋላ ዐቃቤ ሕጓ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈፀመብን ብላ ክስ ያቀረበችውን ወ/ት ኬት ሳምሶንን ወደ ምስክርነት መስጫው እንድትቀርብ ጠራቻት። ኬት ቅርፀ መልካም ስትሆን ጥቁር ዘንፋላ ፀጉሯ አንደኛው አይኗን በመጠኑ ጋርዳቷል። እድሜዋ 18 ዓመት መሆኑን ለፍ/ቤቱ ገለፀች።

ዐቃቤ ሕግ፡- ወ/ት ኬት ተከሳሹን ለምን ያህል ጊዜ ታውቂዋለሽ?

ኬት፡- ለሁለት ዓመት ገደማ ያህል።

ዐቃቤ ሕግ፡- እንዴት እንደተገናኛችሁ ብትገልጭልኝ?

ኬት፡- ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እያለን ነበር በአጋጣሚ የተዋወቅነው። እሱ በክፍል ይበልጠኛል ድንገት በአጋጣሚ ተዋወቅን። የተለየ ግንኙነት አልነበረንም። አብሮ መውጣት (የፍቅር ቀጠሮ አልነበረንም። ሁለተኛ ደረጃ ከጨረስን በኋላ እኔ ወደሲቲ ኮሌጅ ገባሁ። እሱም እዛ ስለነበር በይበልጥ ለመተዋወቅ ቻልን።

ዐቃቤ ሕግ፡- በይበልጥ መተዋወቅ ስትይ ምን ለማት ነው?

ኬት፡– መክሰስ ወይም ምሳ አብረን የኮሌጁ ግቢ ውስጥ እንበላለን። ከዚያ አብረን ሆነን ሲኒማ ለመግባት ተሰማማን። የመጀመሪያ የፍቅር ቀጠሮአችን (አብረን የወጣነው) ያኔ ነበር።

ዐቃቤ ሕግ፡- ያለው ነገር ተከስቶ ያውቃል?

ኬት፡- እጅ ለእጅ እንያያዛለን እሱን ማለትሽ ከሆነ። ደህና እደሪ ብሎ ሲሰናብተኝም ይስመኝ ነበር። ይሄው ብቻ ነበር።

ዐቃቤ ሕግ፡- በድጋሚስ ወጥታችኋል?

ኬት፡- አዎን የሆነ ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባህሩ ዳርቻ ሄደን ነበር። የተወሰነ ሰዓት አብረን በእግር ሽርሽር አድርገናል።

ዐቃቤ ሕግ፡- አካላዊ ንክኪ ያለበት ነገር አርጋችሁ ነበር?

ኬት፡– አዎን አርገናል በመኪናው ውስጥ በጣም ነበር አካል ለአካል የተነካካነው ሆኖም ከዚያ ዘለለ ሌላ ነገር አላደረግንም። ሁልጊዜም ቢሆን እሱ ፍፁም ጨዋ ልጅ ነበር።

ዐቃቤ ሕግ፡- ከዚያ በኋላስ በፍቅር ግንኙነት መውጣት ቀጠላችሁ?

ኬት፡- እሱማ በክረምቱ ጊዜ ደውሎልኝ ስለማያውቅ መገናኘት አቋረጥን። ከሌላ ሰው ጋር እየወጣ እንደነበር ሰማሁ።

ዐቃቤ ሕግ፡- ከዚያ ቀጥሎስ መቼ ነበር ያየሽው?

ኬት፡- ወደ አንድ የፓርቲ ዝግጅት ላይ ሁለታችንም ተገኘን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሴት ጓደኛዬ ጄን ሊትሜየር የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጓደኞች መገናኛ አነስ ያለ ዝግጅት አዘጋጅቷ ስለነበር ሁለታችንም እዛ ዝግጅት ላይ መጥተን ነበር።

ዐቃቤ ሕግ፡- እባክሽ እዚያ የተከሰተውን ነገር ለፍ/ቤቱ አስረጅልኝ?

ኬት፡- የጓደኛችን የጄን ቤት ትልቅ ነው። ሁለት ፎቅ ነው። በርካታ ክፍሎችና ትልቅ የመዋኛ ገንዳም አለው። ወደ ሰላሳ የሚሆኑ ልጆች ነበሩ። እኔና ማውሪስ አብረን ደነስን። በኋላ እየመሸ ሲሄድ አብዛኞቹ እንግዶች ወደቤታቸው ሄዱ። እኛ ደግሞ አብረን ለመዋኘት ወሰንን። የመዋኛ ገንዳ ውስጥ ብቻችንን ነበርን። በውሃው ውስጥ እየዋኘን ስንቦራጨቅ ቆየን። ከዚያም እዚያው ውሃ ውስጥ እሱ ጎትቶ ያዘንና ይስመኝ ጀመር።

ዐቃቤ ሕግ፡- እንዳይስምሽ ተቃውመሽዋል?

ኬት፡- ኧረ አልተቃወምኩትም በጣም የሚያስደስት ነበር። ያኔም ገና ሁኔታውን እወደው ነበር።

ዐቃቤ ሕግ፡- ቀጥሎስ ምን ተከሰተ?

ኬት፡– የሆኑ ልጆች የመዋኛ ገንዳው ድረስ ጥቂት ቢራዎች አመጡልን። እኔና ማውሪስም ምንም እንኳን መጠጣት ባይኖርብንም አንዳንድ ቢራ ጠጣን።

ዐቃቤ ሕግ፡- ቀጥይ?

ኬት፡- ከዛማ ትንሽ እዛው ገንዳው ውስጥ ስንጨዋወት ቆየን። ሰዓቱ እየመሸ ነበር። ከመዋኛ ገንዳው ውስጥ ስንወጣ ገንዳው አካባቢ የቀረነው እኛ ብቻ ነበርን። ወደጎን አለፍ ብሎ ትንሽዬ የእንግዶች ማረፊያ ጎጆ አለች። በሯ ገርበብ እንዳለ ነበር። ማውሪስ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ አየና እንድመጣ በእጁ ጠራኝ። ምን ማለቱ እንደሆነ እርግጠኛ አልነበርኩም እጄን ይዞ ወደውስጥ እየመራኝ ገባን።

ዐቃቤ ሕግ፡- ምንም የተቃወምሽው ነገር አልነበረም?

ኬት፡– እ. . . የተቃወምኩት አይመስለኝም ጎተት አርጎኝ ነበር። ወደውስጥ ያስገባኝ እውነቱን ለመናገር ግን አልተቃወምኩትም። “ምን ልናደርግ ነው?” ብዬ ጠይቄለሁ እሱም ሳመኝና “በጣም ቆንጆ ፍጡር ነሽ” አለኝ። ከዚያም በሩን ከውስጥ ቆለፈው። እኔም “ይህን ማድረግ ግን አልነበረብንም ነበር” አልኩት። እሱም ኧረ እንዲውም ማድረግ ነው ያለብን” አለኝ።

ዐቃቤ ሕግ፡- ፈርተሸ ነበር?

ኬት፡- በእውነቱ አልፈራሁም እሱ ሁሌም ቢሆን ጨዋ ልጅ ነበር።

ዐቃቤ ሕግ፡- እሺ ከዛስ በኋላ? በትክክል የተከሰተውን ነገር ንገሪን?

ኬት፡- የዋና ልብሳችን እንደለበስነው ነበር። በሩ ላይ እንደቆምኩ ድንገት ትከሻዬ ላይ እቅፍ አድርጎ አስጠጋኝና በክንዶቹ እቅፍ ውስጥ እንዳለሁ በረጅም ጊዜ ሳመኝ። አሳሳሙ በጣም በጥልቅ ስሜት የተሞላ ነበር።

ዐቃቤ ሕግ፡- ያኔስ አልተቃወምሽውም?

ኬት፡- ኧረ የለም እደሚመስለኝ እኔም እንደሱው ስሜት ውስጥ ገብቼ ነበር እውነቴን ነው የምነግራችሁ ልጁን እወደው ነበር።

ዐቃቤ ሕግ፡- እባክሽን ቀጥይ። ለከብድሽ እንደሚችል አውቃለሁ ሆኖም አሁን ፍ/ቤት ውስጥ ነን ያለነው ስለዚህ እውነቱን ማወቅ አለብን፡

ኬት፡- ከላይና ከታች የተለያየ የመዋኛ ልብስ ነበር የለበስኩት። በቀስታ ከላይ የለበስኩትን ቁልፉን ከፈተና አወለቀው። እንዳቀፈኝ ነው። ከዚያ. . . ይነካካኝ ጀመር ጡቶቼን ነካካቸው። ከዚያም አልጋው ላይ ቁጭ አልን። እርስ በእርስ አይን ለአይነት እየተያየን ነበር። ከዚያም ድንገት በሩ ተንኳኳና ጄን ተጣራች “ኬት?” እያለች። “በደህናሽ ነው?” ስትል ጠየቀችኝ።

ዐቃቤ ሕግ፡- ጥያቄዋን መለስሽ?

ኬት፡- እኔም “ደህና ነኝ ጄን በሰላም ነው” ብዬ መለስኩላትና እሷም ከዚያ አካባቢ ሄደች።

ዐቃቤ ሕግ፡- አልጋ ላይ ተቀመጠን ብለሽ ነበር ያቆምሽው ከዚያስ?

ኬት፡– ማወሪስ አየት አድርጎኝ ልብሱን አወላለቀ። የኔንም ከታች የለበስኩትን ወደታች ጎትቶ ዝቅ አደረገው። እኔም ከታች የለበስኩትን አወልቄ አልጋው ላይ ተያይዘን ተጋደምንና ተቃቅፈን መነካካት ጀመርን። በጣም ስሜት ውስጥ ገብተን ነበር። እኔ ከዚያ በፊት እንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ገብቼ አላውቅም ነበር።

ዐቃቤ ሕግ፡- አሁን እግዲህ ኬት በጣም ግላዊ የሆኑ ጥያቄዎችን ልጠይቅሽ ነው። ምናልባት መልስ ለአንቺ ግልፅ ቢሆንም እንደመዘገቡልኝ መጠየቅ አለብኝ። (ኬት እራሷን በማወዛወዝ መስማማቷን ገለፀች) ብልቱን ብልትሽ ውስጥ ከትቷል?

ኬት፡– አዎ

ዐቃቤ ሕግ፡- አንቺስ ፈቅደሽለት ነው?

ኬት፡- እኔ . . . እኔም አልተቃወምኩትም።

ዐቃቤ ሕግ፡- አሳመመሽ?

ኬት፡- መጀመሪያ ላይ አዎ ህመም ነበረው። ሆኖም ጠብቄው ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜዬ በመሆኑ

ዐቃቤ ሕግ፡- እንደሚያም እንዲያው አድርገሻል?

ኬት፡- እንደሚመስለኝ ጮኬያለሁ ወይም የሆነ የጩኸት የሚመስል ድምፅ ስላወጣው እንዳመመኝ አውቆ ነበር።

ዐቃቤ ሕግ፡- ይህን እንዴት አወቅሽ?

ኬት፡- ምክንያቱም “ካሳመምኩሽ አዝናለሁ እኔ ላሳምምሽ ወይም ልጎዳሽ አልፈልግም” ብሎናል እኔም “ምንም አይደል ደህና ነኝ” ስል መልሼለታለሁ።

ዐቃቤ ሕግ፡- ከዚያስ ምን ተከሰተ?

ኬት፡– ያው የግብረስጋ ግንኙነቱን ማድረጉን ቀጠልን። እዛው ላይ ሀቁን መደበቅ አልፈልግም። ይህ ጉዳይ ከፍተኛ ቁምነገር መሆኑን አውቃለሁ። እኔም ግን እንደሚመስለኝ የሱን ያህል ገብቼበት ነበር። የምለውን ከተረዳችሁኝ።

ዐቃቤ ሕግ፡- ጠንካራ ጥያቄዎችን በታማኝነት መመለስሽን እናደንቃለን። ከዚያስ የሆነ የሚያስከፋሽ ነገር ተናገረሽ?

ኬት፡– በደምብ እንጂ እንዴት ውብ እንደሆንኩ ሲናገር ቆየና ግብረስጋ ግንኙነት እያደረግን በመሀል ላይ “በጣም ድንቅ ልጅ ነሽ ፔጊ በፍቅርሽ አበድኩልሽ” ሲል በጆሮዬ አንሾካሾከልኝ።

ዐቃቤ ሕግ፡- ፔጊ ሲል ሰምተሸዋል?

ኬት፡- በርግጠኝነት ከዚያም ደገመው እንጂ” በጣም ቆንጅዬ ነሽ ፔጊ” አለኝ።

ዐቃቤ ሕግ፡- ፔጊ ማን ነች?

ኬት፡- እኔም መጀመሪያ ስሰማው ጆሮዬን ማመን አቅቶኝ ነበር። ከዛ ትዝ ሲለኝ ለካ ፔጊ ማት በክረምት ከኔ ጋር ተዘጋግተን አብሯት የነበረችው ልጅ ነች።

ዐቃቤ ሕግ፡- ይህን ማለት ከመጠን በላይ አስቆጣሽ?

ኬት፡- በጣም እንጂ። ከእኔ ጋር ፍቅር እየሰራ ከእሷ ጋር ፍቅር እንደሚያደርግ ነው እያሰበ የነበረው። በጣም ስለከፋኝ ተናደድኩበት።

ዐቃቤ ሕግ፡- ይሄኔ ምን አረግሽ?

ኬት፡- “አቁም እባክህን አቁም” ስል በከፍተኛ ድምፅ ጮኸኩበት።

ዐቃቤ ሕግ፡- እሱስ ወሲብ መፈፀሙን አቆመ?

ኬት፡– አይ አላቆመም። ቀጠለበት።

ዐቃቤ ሕግ፡- አንቺስ እንዲያቆም መጠየቅሽን ቀጠልሽ?

ኬት፡- እኔማ ወሲብ ማድረጉን እንዲያቆም ለመንኩት።

ዐቃቤ ሕግ፡- ሰምቶሻል?

ኬት፡- በደምብ አድርጎ ሰምቶኛል “እባክሽ እንደሱ አትበይኝ እባክሽ አሁን እንዳቆም አትጠይቂኝ እጅግ በጣም ድንቅ ልጅ ስለሆንሽ ማቆም አልችልም” ሲለኝ “ማውሪስ አቁም ተወኝ እኔ አልፈልግም” እያልኩ በመጮኸ ከላይ ላይ ልገፋው ብሞክርም በጣም ጠንካራ ስለነበር ማድረጉን ቀጠለበት።

ዐቃቤ ሕግ፡- ስሜቱ እስኪረካ ቀጠለ?

ኬት፡- ለሱማ አዎ ስሜቱን እስኪያረካ ድረስ ቀጠለ ለኔ ግን ስሜቴ እንደሱ አልነበረም።

ዐቃቤ ሕግ፡- ከዚያስ በኋላ?

ኬት፡– ከዚያማ ከላዬ ላይ ተንከባሎ ወረዳና ሁለታችንም ጎን ለጎን በጀርባችን ተኛን። ሊስመኝ ሲሞክር ፊቴን አዞርኩበት። በጣም ቅር ተሰኝቼበታለሁ። የተጠቀመብኝ ሆኖ ነው የተሰማኝ ። በጣም የተበሳጨሁት ደግሞ አቁም እያልኩት ባለማቆሙ ነው። እሱ የራሱን መንገድ ተጠቅሞ ስሜቱን መቆጣጠር ነበረበት። ሆኖም ግን ለኔ ስሜት አንዳችም ደንታ አልነበረውም። እሺ እኔ ምንድነኝ? ባጣ ቆየን ነኝ ፔጊ ስለሌለች የምተካ ነኝ? ስለኔ አንዳችም ግድ አልነበረውም። ጭራሹኑ የኔ ነገር ግድም አልሰጠው (እንባ በአይኖችዋ ግጥም አለ)

ዐቃቤ ሕግ፡- የተከበረው ፍ/ቤት እረፍት እንድናረግ ይፈቅዳል ስትል ጠየቀች?

ዳኛው፡– አዎ እረፍት ማድረግ አለብን። ክቡራትና ክቡራን ከማንም ጋር ስለክርክሩ መነጋገር አይፈቀድም ከ15 ደቂቃ በኋላ ችሎቱ ይቀጥላል። ችሎቱ መልሶ ተሰየመ። ኬት እምባዋን እያበሰች ነበር ቦታዋን ያዘች። ዐቃቤ ሕግ ጥያቄዋን ቀጠለች፡

ዐቃቤ ሕግ፡- ሊስምሽ ሲል ፊትሽን ስታዞሪበት ምን አለሽ?

ኬት፡– ምን ሆንሽ? ምንድነው ችግሩ? ሲል ጠየቀኝ እኔም “ችግሩንማ ታውቀዋለሁ አቁም ብዬ እየለመንኩህ ነበር” አልኩት

ዐቃቤ ሕግ፡- ምን ብሎ መለሰልሽ አለቻት።

ኬት፡– “ታዲያ ምን እንዳረግ ነበር የምጠትብቂው በጣም ስሜት ውስጥ ገብቻለሁ እኔ የፈለግሽ ነበር የመሰለኝ። ቆይ ምንድነው እንዲህ ያስቆጣሽ? ሲል ጠየቀኝ። እኔም አንተማ ሊገባህ አይችልም ብዬ መለስኩለት። ከዚያ ተነስቼ ለብሼው የነበረውን የዋና ልብስ ለብሼ ከጎጆዋ ወጣሁ።

ዐቃቤ ሕግ፡- ከመውጣትሽ በፊት ያልሽው ነገር ነበር።

ኬት፡– አዎ አንተና ፔጊ ደስተኛ እንደሆናችሁ ተስፋ አለኝ” አልኩት።

ዐቃቤ ሕግ፡- አመሰግናለሁ ወ/ት ኬት ሳምሶን የተከላካይ ጠበቃዋ ጥያቄ ካላት መቀጠል ትችላች አለቻት።

የተከላካይ ጠበቃ፡- የዚያኑ ምሽት ነው ወደ ፖሊስ የሄድሽው?

ኬት፡– አይደለም።

የተከላካይ ጠበቃ፡- በነጋታው ቅዳሜስ?

ኬት፡- አልሄድኩም። እያሰብኩበት ነበር ምን ማድረግ እንደነበረብኝም አላውቅም ነበር።

የተከላካይ ጠበቃ፡- እሁድስ?

ኬት፡– አልሄድኩም ወንጀል መሆኑንም እርግጠኛ አልሆንኩም ነበር ቁኑን ሙሉ ሳስብበት ዋልኩ።

የተከላካይ ጠበቃ፡- ሰኞስ?

ኬት፡– ሰኞ በዓል ነበር

የተከላካይ ጠበቃ፡- በእረፍት ቀን እንዲደወልልሽ ጠብቀሽው ነበር?

ኬት፡– እ. . . አዎ ይቅርታ ይለኛል ብዬ አስቤ ነበር የሰራውን ጥፋት ስለሚያውቀው።

የተከላካይ ጠበቃ፡- እሱ ግን አልደወለም?

ኬት፡– አልደወለም።

የተከላካይ ጠበቃ፡- በዚህ ምክንያት የበለጠ ተናደድሽበት?

ኬት፡– አዎ በርግጥም ተናድጃለሁ። ቅንጣት እንኳን ግድ አልነበረውም።

የተከላካይ ጠበቃ፡- በመጨረሻ ቅዳሜና እሁድ ሰኞ ይቅርታውን ጠብቀሽ ባለማግኘትሽ ማክሰኞ ከፖሊስ ክስ መሰረትሽበት?

ኬት፡- ወደ ሕግ ት/ቤት የገባች የ1ኛ ዓመት ጓደኛ ነበረችኝ የኔ ጉዳይ እንዳልሆነ አድርጌ ስለአስገድዶ መድፈር ሕግ ጠየኳት። ካለፍቃድ ወሲብ ከተፈፀመ አስገድዶ መድፈር መሆኑን ስትነግረኝ ተውኝ እያልኩት ባለመተው ይህን የሚቀጣ ሕግ መኖር አለበት ብዬ ከሰስኩ።

የተከላካይ ጠበቃ፡- በዛስ ደወለልሽ?

ኬት፡- አዎ መጨረሻ ላይ ደወለልኝ ሆኖም ፖሊሱ ለማንም ምንም እንዳታወሪ ስላለኝ ስልኩን ዘጋሁበት። አለች ቀጠዩ ደግሞ አለፍ ማውሪስ የተባለው የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሲሆን የኬትን ክስ ተቀብሎ የመረመረው መርማሪ ፖሊስ ነው። እሱም ክሱ እንደተመሰረተ የደረሰኝ ደውሎ ለጥያቄ እንደሚፈልገውና ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲመጣ እንደነገረው ሕገመንግስታዊ የሆነ ለሚጠየቀው ጥያቄ መልስ ያለመስጠት በጠበቃ የመከራከር መብት እንዳለውና የሚሰጠው ቃል ፍ/ቤት በማስረጃነት እንደሚቀርብበት በደምብ ለተከሳሹ እንዳስረዳው ለችሎቱ አስረዳ። ተከሳሹ ማውሪስ ቃሉን ለመስጠት እንደተስማማና ምንም የሚደብቀው ነገር እንዳሌለ እንደነገረው መርማሪ ፖሊሱ ለፍ/ቤቱ ከገለፀ በኋላ እንዲህ ሲል በአጭር ለፍ/ቤቱ ተከሳሹ ማውሪስ የሰጠውን ቃል አረጋገጠ።

በጣም ነበር የተባበረኝ እና ወ/ት ኬት ያለችውን ነገር በማረጋገጥ። በፈቃደኝነት የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ጀምረው እንደነበር ኬት እንደገለፀችው በተመሳሳይ አስረዳኝ። የሆነ ቦታ ላይ አቁም እንዳለችውም አልካደም። ሆኖም በጣም ተሟሙቆና ስሜት ውስጥ ስለነበርኩ መቆም እንዳልቻለ ቃሉን ሰጠኝ እሷ ባለችውና እሱ ባለው መካከል ምንም ልዩነት አልነበረውም።

ዐቃቤ ሕግ፡- ከዛስ ምን አደረክ?

መርማሪ ፖሊስ፡- ከዛም ባስገድዶ መድፈር ወንጀል ተጠርጥሮ እንደማስረው ነገርኩትና ወደ ማረፊያ ቤት ወሰድኩት የተከላካይ ጠበቃዋ መስቀለኛ ጥያቄ ጀመረች። ለምን አቁም እዳለችው ተከሳሻ ያውቅ ነበር?

መርማሪ ፖሊስ፡- ይህን እኔም ጠይቄው ነበር ሆኖም ደስተኛ ትመስል ስለነበር እንዳላወቀ ነግሮኛል።

የተከላካይ ጠበቃ፡- እንደምታስረው ስትነግረውምን ነበር ያለህ?

መርማሪ ፖሊስ፡- ምን አጠፋሁ? “እኔ አንድም ጥፋት እንደሰራሁ አላውቅም። እሷ ራሱ ፈቅዳ ነው ያደረግነው” ነበር ያለኝ።

እኔም የተጠረጠረበትን ጥፋት ማመኑንና ከማሰር ውጭ አማራጭ እንደሌለኝ ነገርኩት። በጣም ነበር የተባበረኝ ግራ ቢጋባም ምንም አላስቸገረኝም ሲል መልሶ መርማሪ ፖሊሱ ሲነሳ ዐቃቤ ሕግ ሌላ የምታሰማው ማስረጃ እንደሌለ ገለፀች። ምስክር የመሰማጡ ሂደት አበቃ የተከላካይ ጠበቃዋ ሁለት ነጥቦችን አንስታ የመዝጊያ ንግግር አደረገች። በዚህ ክርክር ላይ የተካዱ እውነታዎች አለመኖራቸውንና አከራካሪው ነገር ለሰማችሁት ጉዳይ ላይ ያስገድዶ መድፈር ሕግ ተፈፃሚ ይሆናል ወይ የሚለው ነው። ተከሳሹ አስገድዶ መድፈር ወንጀል መሆኑን ያውቃል ግን ተበዳይዋ ሙሉ ፈቃዷን ገልጻለች። ስለዚህ ሕግ ጥሻለሁ ብሎ የሚያምንበት ምክንያት የለም። ሆኖም መታሰብ ያለበት ተከሳሽ ማውሪስ አአስገድዶ ደፋሪ የሚለው ስያሜ እንዴት ይሰጠዋል? በማለት ተከሳሹ ጥፋተኛ መባል የለበትም ስትል ደመደመች።

ዐቃቤ ሕጓ በበኩሏ ተከሳሹ ኬት አቁም እያለችው የራሱን የስሜት ጥም ለማርካት ግንኙነቱን ቀጥሏል። ዋናው ነገር መጀመሪያ መፍቀዷ ላይ አይደለም። እንዳይቀጥል ከልክላዋለች። ልትገፋው ሞክራለች እሱ ግን አልሰማትም። ይሄን ማወቃችን ብቻ በቂ ነው። ከሕዝብ የተውጣጣችሁ የጥፋተኝነት ውሳኔ የምትሰጡ እንደመሆናችሁ ሕጉን ብቻ ነው መከተል ያለባችሁ። በመሆኑም ተከሳሽ አስገድዶ ግብረስጋ ግንኙነት በመፈፀሙ ጥፋተኛ መባል አለበት አለች።

ጉዳዩን የሚያዩት ዳኛም ወጣት ሴት ናቸው አንዲትን ሴት ካለፈቃዷ በሃይል አስገድዶ ግብረስጋ ግንኙነት መፈፀም ወንጀል መሆኑን በመግለፅ ከሕዝብ ለተወጣጡት የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጪ (የጂሪ አካላት) መመሪያ ሰጡ።

እርሶ ቢሆኑ ምን ይወስኑ ነበር? በነገራችን ላይ በአሜሪካዎቹ ሕግ ብቻ ሳይሆን የኛም የወንጀል ሕግ አንቀፅ 620 (1) ስለ አስገድዶ መድፈር እንዲህ ይላል “ማንም ሰው የሃይል ድርጊት በመጠቀም ወይም በብርቱ ዛቻ ወይም ህሊናዋን እንድትስት ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ መከላከል እንዳትችል በማድረግ ከጋብቻ ውጭ አስገድዶ ከአንዲት ሴት ጋር የግብረስጋ ግንኙነት የፈፀመ እንደሆነ ከአምስት ዓመት እስከ አስራ አምስት አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል።

በዚህ እውነተኛ በአሜሪካን ሀገር በቀረበ ክስ ላይ ተከሳሹ ማውሪስ የግል ተበዳይ ኬትን አስገድዶ በመደፈር ጥፋተኛ ነው ተብሎ ተወስኖበታል። ትረጉሙ የኔ ነው ምንጭ “You Be The Judee 20 True ctimes and cases to sceve” የሚለው በዳኛ ኖርበርት ኤረንፋረንድ የተፃፈውና በ2008 እ.ኤ.አ የታተመው መፅሀፍ ነው።

ለዛሬ በዚሁ ይብቃን!n

Source- www.sendeknewspaper.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.