የጀርባ ህመም የበሽታ አይነት ሳይሆን በተለያዩ በሽታዎች ምክኒያት የሚመጣ የበሽታ ምልክት ነው። አብዛኛውን ጊዜ የሚመጣበት ምክኒያት የማይታወቅ ሲሆን በዚህም ምክኒያት በቤት ውስጥ እረፍት በማድረግ ብቻም ሊታገስ ይችላል።
 

የጀርባ ህመም እንዴት ይከሰታል?

women_back_painበሽታው በተለያዩ ምክኒያቶች ሊመጣ ይችላል። ይህም ማለት በጀርባችን ላይ ከሚገኙት አካላት፤ ከቆዳ፣ ከጡንቻ፣ ከአጥንት፣ ከአከርካሪ፣ ከነርቭ ላይ ህመሙ ሊነሳ ይችላል። ከነዚህም መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡

 • የአጥንት ወይም የጀርባ ጡንቻ መጎዳት
 • የነርቭ መጎዳት
 • የዲስክ መንሸራተት (ዲስክ ማለት በአከርካሪ አጥንቶች መሃል የሚገኘው የሰውነት አካል ነው።)
 • የአከርካሪ አጥንት ኢንፌክሽን
 • ካንሰር
 • የነርቭና የጡንቻ ቁስለት
 • የእንቁላል ማኩረቻ በሽታዎች
 • የሆድ እቃ ችግሮች

የጀርባ ህመም መቼ ሊያሰጋኝ ይገባል?

 • ከፍተኛ አደጋ ሲያጋጥም ለምሣሌ፡ የመኪና ግጭት፣ ከፎቅ የመውደቅ አደጋ
 • ዕድሜያቸው ከ50በላይ የሆኑ ከሆኑና ቀላል አደጋ በሚያጋጥም ጊዜ ለምሣሌ፡ ተንሸራቶ በመቀመጫ መውደቅ
 • ከዚህ በፊት የአጥንት ስብራት አጋጥሞት ከሆነ
 • ካንሠር በሽታ ካለብዎት
 • በቅርብ ጊዜ ማንኛውም ኢንፌክሽን ካጋጠመዎት
 • ትኩሳት ካለ
 • ምክኒያቱ ያልታወቀ ክብደት መቀነስ
 • የሆድ ዕቃ ችግር ካለቦት
 • ህመሙ ቁጭ ሲሉ የሚብስ ከሆነ
 • መራመድ ወይም እግር ማንሳት ያለመቻል
 • ሰገራ ወይም ሽንት መቆጣጠር አለመቻል
 • በፊት የታዘዘ መድሀኒት ከነበረ እና ህመሙን ማስታገስ ካልቻለ

እነዚህ ችግሮች ከታዩ በአፋጣኝ ወደሐኪሞ በመሄድ የበሽታውን መነሻ መመርመር ያስፈልጋል።

የጀርባ ህመም ህክምናው ምንድነው?

ህክምናውን ለማስጀመር የተለያዩ ምርመራዎችን ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል። የተከሰቱትን ምልክቶች በማገናዘብና አጠቃላይ የሰውነት ምርመራ በማድረግ መነሻውን ለማወቅ ጥረት ይደረጋል። እንደተገኘው የበሽታ አይነትም የህክምናው አይነት ሊለያይ ይችላል። ይህም በቤት ውስጥ እረፍት ከማድረግ ጀምሮ፤ መድሀኒት እስከመውሰድ እና አፕሬሽን እስከማድረግ ይደርሳል። የበሽታዎን አይነትና የህክምናውን አማራጮች ከሐኪምዎ ጋር መወያየት ይኖርብዎታል።

 ምንጭ — አዲስ ጤና

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.