በ ዳንኤል እሸቱ

  1. አመጋገብዎን ያስተካክሉ

በእርግዝና ወቅት ሰውነታችን በቀን እስከ 2500kcal ያክል ሃይል ያስፈልገዋል። ይህም የሃይል ፍላጎት የሚጨምረው ለጽንሱ እድገት እና ጽንሱን ለመሸከም በሚደረገው የሰዉነት ግንባታ ነው።

ይህንንም በበቂ ሁነታ ለማከናወን አንዲት ነፍሰ ጡር እናት የሚከተሉትን ኣይነት ምግቦች በየቀኑ መመገብ አለባት፡-

1 ሊትር ወተት ወይም የወተት ተዋእጾዎችን

1-2 እንቁላሎችን

አትክልት እና ፍራፍሬዎች

ጥራ-ጥሬ

ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ደግሞ ቀይ ስጋ እና አሳ ብትመገብ ይመከራል፤ ሌላው ደግሞ ቡና መቀነስ እንደሚኖርብን መዘንጋት የለበትም።

  1. ክብደትዎን ይቆጣጠሩ

አንዲት ነፍሰ ጡር እናት እርግዝና ከጀመረችበት ቀን አንስቶ እስከ 3ኛው ወር ድረስ 2ኪ.ግ ትጨምራለች፣ ከ3ኛው – 6ኛው ወር 5ኪ.ግ እና ከ6ኛው – 9ኛው ወር ደግሞ ሌላ 5ኪ.ግ ትጨምራለች።

አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት በአጠቃላይ 12 ኪ.ግ ትጨምራልለች ማለት ነው። እርሶም በዚህ መሰረት ክብደትዎን ይከታተሉ።

  1. ሲጋራ እና መጠጥ ያቁሙ

ሲጋራና መጠጥ በጽንሱ የአእምሮና የአካል እድገት ላይ ከፍተኛ የሆኑ ችግሮችን ይፈጥራሉ። ከዚህም አልፎ ተርፎ ጽንሱን እስከማጨናገፍ የሚያደርስ ጉዳት ሊያደርሱ ስለሚያስችሉ በእርግዝና ወቅት ፈጽሞ ሊወገዱ ይገባል።

  1. እንቅስቃሴ ያድርጉ
  2. በቂ እረፍት እና እንቅልፍ ያግኙ

ነፍሰ ጡር አናቶች በቀን የ2 ሰአትና በምሽት ደግሞ የ8 ሰአት እንቅልፍ እና እረፍት ማግኘት አለባቸው።

  1. አለባበስዎን ያስተካክሉ

ዘና ያሉ ልብሶችና ታኮአቸው ዝቅ ያሉ ጫማዎችን በመጫማት የጀርባ ህመምን እና የልጆን ጤና ይጠብቁ።

  1. ተከታታይ የእርግዝና ክትትል ያድርጉ

በአካባቢዎ በሚገኝ የጤና ተቋም የእርግዝና ክትትል በማድረግ በእርግዝና ወቅት የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችንና በሽታዎችን ይከላከሉ።

  1. በአውሮፕላን ጉዞ ወቅት ጥንቃቄ ያድርጉ
  2. የወሊድ ግዜ ሲቃረብ እረፍት ይዉሰዱ
  3. ያልተለመዱ ምልክቶች ሲታዩ በኣስቸኳይ ሃኪሞን ያማክሩ

በእርግዝና ወቅት ያልተለመዱ ምልክቶች(ለምሳሌ፡- ከብልት ዉስጥ የሚወጣ ፈሳሽ ወይም ደም ካለ፣ የሆድ ህመም፣ ለረዥም ሰአት የሚቆይ ራስ ምታት፣ ብዥታ፣ ለረዥም ግዜ የቆየ ማስመለስ፣ የእግርና የፊት እብጠት ወ.ዘ.ተ.) ሲታዩ በኣስቸኳይ ሃኪሞን ያማክሩ።

በእርግዝና ዙሪያ ያልተመለሱ ጥያቄ ካሎት ኮመንት ያድርጉ። በተረፈ ‘share’ በማድረግ ለጓደኞችዎ ያካፍሉ።

pregnancy-images

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.