በእርግዝናሽ ወቅት ልጅሽ ኃይልና ንጥረ ነገሮችን የሚያገኘው ካንቺ ነው። ስለዚህም በቂ የሆነ የበለፀጋ ምግብ ላንቺ እና ለልጅሽ መውሰድ ይኖርብሻል።

Fotolia_30371529_XS-36b4291600በተቻለ መጠን ቁርስ፣ ምሳ፣ እራት እና በመሃል ደግሞ የተወሰነ መክሰስ መውሰድ ይመረጣል። በዚህ አይነት በቀን ውስጥ ጊዜ እየጠበቅሽ ስትመገቢ ለልጅሽ የሚሆን ኃይልና ንጥረ ነገር በማይዛባ መልኩ ቀኑን ሙሉ ይደርሰዋል። በሚያቅለሸልሽሽ እና ጤንነት በማይሰማሽ ወቅት ትንሽ ትንሽ ምግብ በመክሰስ መልክ ቶሎ ቶሎ መብላት የተሻለ እንዲሰማሽ ይረዳል።

የምትመገቢውን የምግብ አይነቶች ማብዛትና መቀያየርም ላንቺና ለልጅሽ የሚያስፈልጋችሁን ንጥረ ነገሮች በብቃት እንድታገኙ ይረዳል። ቫይታሚኖችና ሚኒራሎችን ማግኘትሽ ለልጅሽ ወሳኝ ሚና አለው። በቫይታሚን ዲ፣ ኦሜጋ-3 ቅባቶች፣ ፎሊክ አሲድ እና በአይረን የበለዘጉ ምግቦች መመገብ ይኖርብሻል።

ምሳና እራት

ምሳና እራት ከሁሉም አይነት ምግቦች የተወጣጡ መሆን ይኖርባቸዋል። የሰሃንሽን 3/4ኛ በድንች/ፓስታ/ሩዝ እና አትክልቶች የቀረውን 1/4ኛ ደግሞ በስጋ፣ አሳ፣ እንቁላል መሙላት ጥሩ አመጋገብ ነው። ከምግብሽ ጋር ውኃ በደንብ ጠጪ።

ለቁርስሽና ለመክሰስ የምትወስጂው ምግብ ከስር ከተዘረዘሩት የምግብ ቡድኖች ከእያንዳንዱ ቢኖረው መልካም ነው፦
ዳቦ/እንጀራ፣ የተደባለቀ እህል አጥሚት ወይም ገንፎወተት፣ እርጎማርጋሪን፣ የገበታ ቂቤ፣ ቺዝ/አይብ፣ ሳርዲን/ቱና፣ ጉበት/ኩላሊት (ቅባቶች መብዛት የለባቸውም) አትክልት ወይም ፍራፍሬ

ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች

አይረን

የቀይ የደም ህዋሶች ዋንኛው አካል የሆነው ይህ ነጥረ ነገር በእርግዝና ጊዜ የእነዚህ ህዋሶች ቁጥር ስለሚጨምር በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች አንዱ ነው። በስጋ፣ ጉበት፣ ካልተበጠረ እህል ከሚሰራ ዳቦ፣ ባቄላ፣ ምስር እና አተር ውስጥ ይገኛል። ሰውነትሽ ይህን ንጥረ ነገር በጥሩ ሁኔታ ከአንጀትሽ ማጣራትና መውሰድ እንዲችል በቫይታሚን ሲ የበለዘጉ ምግቦች መውሰድ ይኖርብሻል (አትክልትና ፍራፍሬዎች)። በተጨማሪም የምትከታተልሽ ሃኪም የቀይ የደም ህዋስ ብዛትሽን በምርመራ አረጋግጣ እንደ አስፈላጊነቱ በክኒን መልክ የተዘጋጀ አይረን ልትሰጥሽ ትችላለች።

ፎሊክ አሲድ

ፎሊክ አሲድ የቫይታሚን ቢ አይነት ሲሆን ለልጅሽ ጤናማ አፈጣጠርና አስተዳደግ በተለይ በህብለ ሰረሰሩ ላይ ችግር እንዳይፈጠር አይነተኛ አስተዋፅዎ አለው። ፎሊክ አሲድ ቢቻል እርግዝና ሲታቀድ ቀደም ብሎ ጀምሮ ቢወሰድ ይመከራል። አረንጓዴ አትክልቶች፣ ፍራፍሬና ስራስሮችን መመገብ ጥሩ የፎሊክ አሲድ ምንጭ ነው። ፎሊክ አሲድ በክኒን መልክ ስለሚገኝ መውሰድ ያስፈልግሽ እንደሆን ሐኪምሽን አማክሪ።

ቫይታሚን ዲ

Fotolia_9695460_XS-8c5906a103ቫይታሚን ዲ ሰውነታችን ካልሲየም የተባለውን ንጥረ ነገር እንዲሰበስብ እና ያንቺም ሆነ የልጅሽ አጥንቶች ጠንካራ እንዲሆኑ የሚያስፈልግ ዋንኛ ንጥረ ነገር ነው። በሰውነትሽ ውስጥ ፀሃይ ቀዳሽን በሚያገኝበት ወቅት ይሰራል፤ ሆኖም በተለይ በተለያዩ ምክንያቶች ፀሃይ በበቂ ሁኔታ ሊያገኝሽ ካልቻለ በተጨማሪ ቫይታሚን ዲ ከምግብ ለማግኘት አሳ፣ በቫይታሚን ዲ እንዲበለፅጉ የተደረጉ የወተት ተዋዕፅዎች፣ እንቁላል መውሰድ ትችያለሽ።

አዮዲን

ላንቺም ሆነ ለልጅሽ የታይሮድ እጢ ትክክለኛ ስራ አዮዲን በጣም አስፈላጊ ንጥረ ነገር ነው። ዋና ምንጩም በአዮዲን የበለፀገ የገበታ ጨው በመሆኑ ምግብ ለመስራት የምትጠቀሚው ጨው አዮዲን ያለው መሆኑን አረጋግጪ። ከዚህ ውጪ የምትመገቢውን የጨው መጠን መጨመር የለብሽም።

ካልሲየም

በእርግዝናሽ ወቅት ከወትሮው በላይ ካልሲየም ያስፈልግሻል። ከላይ እንደተጠቀሰው ካልሲየም ላንቺ አጥንት መጠንከር እንዲሁም ለልጅሽ አጥንት እና ጥርስ ማደግ ወሳኝ ንጥረ ነገር ነው። በቀንሽ ውስጥ ሁሌ ወተት (5 ኩባያ)፣ አይብ፣ እና የመሳሰሉ የወተት ተዋዕፅዋችን ብትመገቢ ላንቺና ለልጅሽ የሚያስፈልጋችሁን ካልሲየም ማግኘት ትችያለሽ። ቅባቱ የተቀነሰለት ወተት ተመራጭ ነው።

በእርግዝና ጊዜ ክብደት ለመቀነስ የሚሆን አመጋገብ (ዳይት ማድረግ) ላንቺም ሆነ ለልጅሽ አደጋዎች ሊኖሩት ስለሚችል በፍፁም አይመከርም። ለምሳሌ ከፍ ያለ ኪሎ በፍጥነት ብትቀንሺ በሰውነትሽ ጮማ ውስጥ ታስረው የነበሩ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ወደ ደም ዝውውር በቶሎ እና በብዛት እንዲገቡ ሊያደርግ ይችላል። በእርግዝና ወቅት ከሚገባው ኪሎ በላይ መጨመርም አይመከርም። ይህ ነው የሚባል መጨመር ያለብሽ ኪሎ የለም፤ ምክንያቱም እያንዳንዷ ሴት የምትጨምረው ኪሎ ይለያያል። ቢሆንም ዝቅተኛ ቅባት ያላቸውን ምርቶች በመጠቀም እንዲሁም ሁል ጊዜ የሰውነት እንቅስቃሴ በማድረግ ጥሩ ኪሎ ላይ ለመሆን መሞከር ይቻላል። በእርግዝና ወቅት በጣም ብዙ ኪሎ የሚጨምሩ እናቶች ከእርግዝና ጋር ለሚከሰት ስኳር በሽታ፣ ለደም ግፌት በሽታ እንዲሁም ከወሊድ በኋላ ለሚቀጥል የከፋ ውፍረት የተጋለጡ ናቸው።

በፋርማሲዎች የሚገኙ የምግብ ክኒኖች ሁሉ ጠቃሚ ናቸው ማለት አይደለም። እንዲሁም ለአንዲት እናት የታዘዘ ክኒን ላንቺ አያስፈልግሽ ይሆናል። ስለዚህም የሚከታተልሽን ሃኪም ሳታማክሪ ምንም አይነት ክኒን እንድትወስጂ አይመከርም።

Source- addishealth.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.