በእርግዝና ጊዜ ጤናማና የተመጣጠነ ምግብ ስትመገቢ እንዲሁም በትክክለኛው የክብደት መጠን ላይ ስትሆኚ፤ ልጅሽ የሚያስፈልጉትን ንጥረነገሮች እያገኝ እንደሆነ ያመላክትሻል። ልጅሽም በአስፈላጊው ፍጥነት እድገት ያሳያል። በእርግዝና ጊዜ ለሁለት ሰው መመገብ አስፈላጊ አይደለም።

Fotolia_42203195_XS-1eb8620924እርግጥ ነው ለልጅሽ እድገት የሚሆን ተጨማሪ ሃይል ያስፈልግሻል። ነገር ግን በእርግዝና ጊዜ የሚያስፈልገው በፊት ከምትመገቢው ተጨማሪ ከ100 እስከ 300 የሚሆን ካሎሪ ብቻ ነው።

ምን ይህል ኪሎ ብትጨምሪ ጥሩ እንደሚሆን ከሐኪምሽ ጋር ብትማከሪ ጥሩ ነው። ከእርግዝና በፊት ከነበረሽ አማካይ የክብደት መጠን በእርግዝና ጊዜ ከ11-16 የሚሆን ኪሎ መጨመር ይኖርብሻል። ከእርግዝና በፊት የነበረሽ ክብደት አነስተኛ ከሆነ ከ13 እስከ 18 ኪሎ ፤ እንዲሁም በፊት የነበረሽ ክብደት ከፍተኛ ከነበረ ከ7 እስከ 11 ኪሎ በእርግዝና ጊዜ መጨመር ይኖርብሻል። በተጨማሪም ሐኪምሽ በሚመክርሽ መሰረት ክብደትሽን መከታተል ይጠበቅብሻል። በአጠቃላይ ለመጀመሪያዎቹ ሶስት የእርግዝና ወራት ከ1 እስከ 2 ኪሎ ለተቀሩት ጊዜያት ደግሞ በየሳምንቱ ግማሽ ኪሎ መጨመር ጥሩ ነው። ያረገዝሽው መንታ ከሆነ ከ16 እስከ 20 ኪሎ መጨመር ያስፈልግሻል።

ክብደቴ እንዲጨምር የሚያደርገው ምንድን ነው?

ለክብደትሽ መጨመር የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የየራሳቸው ሚናን ይጫወታሉ፡፡

እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡፡

 • ህጻኑ 3.5ኪሎ
 • እንግዴ ልጅ 1 – 1.5 ኪሎ
 • ሽርት ውሃ 1 – 1.5 ኪሎ
 • ጡት 1 – 1.5 ኪሎ
 • ደም 2 ኪሎ
 • ማህጸን 1 – 2 ኪሎ
 • የስብ ክምችት 2 – 4 ኪሎ
 • አጠቃላይ 11 – 16 ኪሎ

በእርግዝና ጊዜ ክብደት መቀነስ ጥሩ ነው?

አንዳንዴ ሴቶች ከመጠን በላይ ወፍረት ካላቸው በእርግዝና ጊዜ ክብደት ቢቀንሱ ችግር የለውም ነገር ግን ከሐኪም ጋር መመካከር ያስፈልጋል። አብዛኛውን ጊዜ ግን ነፍሰጡር ሴቶች ክብደት ለመቀነስ ሙከራ እንዳያደርጉ እንመክራለን።

እንዴት ትክክለኛውን የክብደት መጠን መጨመር እችላለሁ?

ሐኪምሽ የበለጠ ክብደት መጨመር እንዳለብሽ መክሮሽ ከሆነ፤ የሚከተሉትን ማድረግ ትችያለሽ፡

 • በየቀኑ ከ 5 እስከ 6 ጊዜ እነስተኛ ምግብ መመገብ
 • ቀለል ያለ አነስተኛ ቁርስ በቦርሳሽ መያዝ፤ ለምሳሌ፡ ዘቢብ፣ እርጎ፣ አይብ፣ ብስኩት … የመሳሰሉ
 • የኦቾሎኒ ቅቤ በዳቦ ቀብቶ መብላት፤ አንድ የሻይ ማንኪያ ኦቾሎኒ ቅቤ 100 ካሎሪ ያስገኛል።
 • ቅባቱ የወጣለት ወተት ወይም የዱቄት ወተት በምግቦች ላይ መጠቀም
 • የዳቦ ቅቤ (ማርጋሪን) እና አይብ ከተለያዩ ምግብ አይነቶች ጋር መጠቀም

በእርግዝና ጊዜ ከመጠን በላይ ክብደት ከጨመርኩኝ ምን ማድረግ እችላለሁ?

ከሚያስፈልገው የክብደት መጠን በላይ ክብደት ከጨመርሽ ከሐኪምሽ ጋር መወያየት ይኖርብሻል። በራስሽ ተነሳሽነት ብቻ ክብደት ለመቀነስ ጥረት ማድረግ የራሱ መዘዞች ይኖሩታል።
የተመጣጠነ ምግብ እየተመገብሽ ከሆነ ልጅሽ የሚያስፈልጉትን ንጥረነገሮች እያገኘ እንደሆነ እርግጠኛ ሁኚ። የክብደት አጨማመርሽን ሊያዘገዩ የሚችሉ መንገዶችን እንደሚከተለው እንጠቁምሻለን፡

 • ፈጣን ምግብ አቅራቢዎች ጋር የምትመገቢ ከሆነ ማዮኔዝ የሌለበትን እና አትክልት የበዛበትን ተመገቢ ፤ በቅባት የሚጠበሱ ምግቦችን አትጠቀሚ ለምሳሌ፡ የተጠበሰ ድንች
 • በቀን ውስጥ ለአራት ጊዜ ወተት መጠጣት ያስፈልግሻል ነገር ግን ቅባቱ የወጣለትን ወይም የዱቄት ወተት በመጠቀም የምትወስጂውን የቅባት መጠን መቀነስ ትችያለሽ።
 • ጣፋጭ ምግቦችን እና መጠጦችን መቀነስ ይኖርብሻል። ለምሳሌ፡ ለስላሳ ፣ የታሸጉ ፍራፍሬ መጠጦች፣ ዱቄት ተበጥብጦ የሚሰሩ መጠጦች። ከነዚህ ይልቅ ውሃን ብትጠቀሚ ተጨማሪ አላስፈላጊ ካሎሪ እንዳትጨምሪ ይረዳሻል።
 • በምግብ ውስጥ የምትጠቀሚውን የጨው መጠን ቀንሺ።
 • ከፍተኛ ካሎሪ ያላቸውን እና ጣፋጭ ምግቦች ለምሳሌ፡ ብስኩቶች፣ ከረሜላዎች፣ ኬኮች፣ ማር.. የመሳሰሉትን ምግቦች በየቀኑ እትጠቀሚ። ይልቁንም ፍራፍሬ፣ ቅባቱ የወጣለት እርጎ፣ የአትክልት ኬኮችን በመብላት ለመተካት ጥረት አድርጊ።
 • የቅባት ምግቦችን መጥነሽ ተጠቀሚ። የቅባት ምግቦች የምግብ ዘይት፣ ማርጋሪን፣ የገበታ ቅቤ፣ ማዮኔዝ፣ አይብ፣ እና ክሬምን የመሳሰሉት ምግቦች ናቸው። ለእንደዚህ አይነት ምግቦች በተቻለ አቅም የቅባት መጠናቸው አነስተኛ የሆነውን አይነት መርጠሸ ተጠቀሚ።
 • ምግብ ስታዘጋጂ በዘይት ወይም በቅቤ የምትጠብሺ ከሆነ የምግቦቹን የካሎሪ መጠን ስለሚጨምር ክብደት እንድትጨምሪ ያደርግሻል። ስለዚህም ምግብን ማብሰል፣ መቀቀል ወይም መጋገር የተሻሉ አማራጮች ናቸው።

የሰውነት ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ይኖርብኛል?

ከሐኪምሽ ጋር በመመካከር የሚያስፈልግሽን የእንቅስቃሴ አይነት ማድረግ ትችያለሽ። በዚህም አላስፈላጊ የሆኑትን ካሎሪዎች እንድታቃጥይ ይረዳሻል። እርምጃ ማድረግ እና መዋኘት ለነፍሰጡር ሴቶች ጥሩ የሚመከሩ እንቅስቃሴዎች ናቸው። ነገር ግን እንቅስቃሴ ከመጀመርሽ በፊት ከሐኪምሽ ጋር መማከር ይኖርብሻል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.