ከቅድስት አባተ
ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል

blogFava1
የሰው ልጅ ከሺ ዓመታት ጀምሮ ሲያለማቸው ከነበሩ ተክሎች ውስጥ የባቄላ እሸት (Fava Beans) አንዱ ነው፡፡ ለጥንታዊ ህዝቦች ዋነኛ የፕሮቲን ምንጭ የሆነው ይህ ተክል ከክርስቶስ ልደት በፊት 3000 ዓ.ዓ በቻይና እንደተገኘ ይነገርለታል፡፡ Pea የተሰኘው የተክሎች ቤተሰብ ውስጥ የሚመደበው ባቄላ እሸት በጥንታዊው ግሪክና ሮም ለምግብነት ይውል እንደነበር ታሪክ ይናገራል፡፡ በሀገራችን አዲሱ ዓመቱ ሲብት አብረው ከሚሽቱ ተክሎች አንዱ ሲሆን ለአመጋገብ ቀላል በመሆኑም ተወዳጅ ነው፡፡

እንደ ሁሉም ተክሎች የባቄላ እሸትም የሚሰጣቸው ጥቅሞች አሉት፡፡ በፕሮቲን የበለፀገው ባቄላ እሸት በቀላሉ በመዋሃድ በፋይበር የተሞላ አስገራሚ ሊባል በሚችል መጠን ዝቅተኛ ስብ ይዟል፡፡ ለሰው ልጅ በሚበጁ ንጥረ ነገሮችም የበለፀገ ነው፡፡
1ኛ. የልብን ጤንነት ይጠብቃል 

በቀላሉ በሚሟሟ ፋይበር የበለፀገ መሆኑ ለልብ ጤንነት ጠቃሚ ያደርገዋል፡፡ ይህ የፋይበር አይነት ለልብ ጠቀሜታውን የሚያበረክተው የደም፣ የስኳር መጠንን እና የኮሌስትሮል መጠንን ያረጋጋል፡፡ ጎጂ የሚባለውን Lipoprotein (LDL) ኮሌስትሮል ይቀንሳል፡፡

2ኛ. ክብደትን ለመቆጣጠር ያግዛል

ባቄላ እሸት በሩብ ኩባያ 10 ግራ ፕሮቲን ይይዛል፡፡ (European Journal of Clinical Nutrition) ላይ ለንባብ የበቃ አንድ ጥናት የካሎሪ መጠናቸውን ለመቆጣጠር የሚፈልጉ ሰዎ ባቄላ እሸትን እንዲመገቡ ይመክራል፡፡ ዕድሜያቸው ከ18-65 ዓመት በሆነ 89 እንስቶች ላይ የተካሄደው ይህ ጥናት ለ19 ሳምንታት ሴቶቹ በፕሮቲን የበለፀጉና በፋይበር የተሞሉ ምግቦችን እንዲወስዱ ተደርገው የሰውነት ክብደታቸውና የስብ መጠን ቀንሶ ተገኝቷል፡፡
3ኛ. በጠቃሚ ይዘቶች የበለፀገ ነው

 ከፍራፍሬዎችና ከአትክልቶች ጋር ካነፃፀርነው ባቄላ እሸት በተሻለ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ ቫይታሚን ቢ1፣ ቫይታሚን አይረን፣ ኮፐር፣ ፎስፈረስ፣ ፖታሲየምና ማግኒዚየም በከፍተኛ መጠን ይገኙበታል፡፡ ቫይታሚን ቢ1፣ ለማዕከላዊ የነርቭ ስርዓት (Central Nervous System) እና የኃይል ዑደት (energy metabolism) ጠቃሚ ነው፡፡
አይረን በደም ውስጥ የሚጓጓዘው የኦክስጅን መጠን በተገቢው ሁኔታ እንዲገኝ ያደርጋል፡፡ ኮፐር ከአይረን ጋር በመተባበር ቀይ የደም ሴሎች እንዲመረቱ የድርሻውን ይወጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የደም ስሮችን የበሽ መከላከል አቅም ከማሳደጉም በላይ የአጥንትን ጤንነትና አቋም ይጠብቃል፡፡ ፎስፈረስና ማግኒዚየም ለጠንካራ አጥነት ዋነኛ ግብአቶች ናቸው፡፡
4ኛ. የደስታ ስሜትን ይፈጥራል
አዎ ይህ ጣፋጭ እሸት ፊትዎ ላይ ፈገግታን ይጨምራል፡፡ L-dope (doparmine) የተሰኘውን አሚኖ አሲድ በከፍተኛ መጠን ይዟል፡፡ ይህ ንጥረ ነገር የድብርት ስሜትን በመቀነስ የደስታ ስሜትን ያሳድጋል፡፡
5ኛ. የመጥገብ ስሜትን ይፈጥራል
በአንድ ጊዜ የሚመገቡት የባቄላ እሸት ከ200 ያነሰ ካሎሪ ይሰጥዎታል፡፡ ክብደት ለመቀነስ የሚያስቡ ከሆነ የባቄላ እሸቱን መመገብ የመጥገብ ስሜትን በመፍጠር ብዙ እንዳይመገቡ ያደርጋል፡፡
6ኛ. ምርጥ የካልሲየም መገኛ ነው
ለአጥንትና ጥርስ ዕድገት እንዲሁም ለመጠገን የሚውለው ካልሲየም ከእነዚህ የተለመዱ ግልጋሎቶቹ በተጨማሪም ልብ ተግባሩን በአግባቡ እንዲወጣ የበኩሉን ይወጣል፡፡
7ኛ. የሆድ ድርቀትን ይከላከላል
የባቄላ እሸት ውስጥ የሚገኘው ፋይበር በምግብ ማሳለጫ ስርዓቱ ውስጥ ምግብ በቀላሉ እንዲንሸራሸር ያደርጋል፡፡
8ኛ. የበሽታ መከላከል አቅምን ያሳድጋል
በተክሉ ውስጥ የሚገኘውና ካንሰር አማጭ የሆኑትን ፍሪ ራዲካልስ የሚቀንሰው ቫይታሚን ሲ የበሽታ መከላከል አቅምን ያሳድጋል፡፡
9ኛ. የውሃ መጠንን ያረጋጋል
በፖታሲየም ውስጥ የሚገኘው electrolytes ሲያልበን ከሰውነት ውስጥ የሚወጡ ሲሆን እንደ ባቄላ እሸት ያሉ ምግቦች እንዲተካ ያደርጋሉ፡፡
10ኛ. የኦክስጅን እጥረትን ይቀርፋል

ደም ውስጥ በቂ ኦክስጅን እንዲኖር ዋነኛው ባለጉዳይ ሄሞግሎብን ሲሆን በባቄላ እሸት ውስጥ የሚገኘው አይረን ደግሞ ዋነኛ ግብአቱ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ባቄላ እሸት በአንዳንድ ሰዎች ላይ fivism የተሰኘ አለርጂክ ያስከትላል፡፡
– ተክሉ በComplex carbohydrates የበለፀገ በመሆኑ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የሆነ ህመም ይፈጥራል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.