(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

✔ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

9485_1497909717100572_2245555502542936159_nየአካል ብቃት እቅስቃሴ ማድረግ ለጤናማ ሕይወት መሰረትና ለጥሩ እና ሰላማዊ እንቅልፍዎ ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡ ነገር ግን እንቅልፍ ከመተኛትዎ በፊት በ3 ሰዓታት ውስጥ የሚሰሩ ከሆነ የሰውነት ሙቀት መጠንዎ ስለሚጨምር እና በቶሎ ለመቀዝቀዝ ጊዜን ስለሚፈጅ ለመተኛት ይቸገራሉ፡፡ ስለዚህም አካል ብቃት እንቅስቃሴ በጠዋት ቢሰሩ ይመከራል፡፡

✔ ቴሌቪዢን ወይንም ኢንተርኔት መጠቀም

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከነዚህ ቁሳቁሶች የሚመጣ ከፍተኛ ብርሃን ሰውነታችን እንቅልፍ እንድንተኛ የሚረዳን ሆርሞን (ሜላቶኒን) እንዳይመነጭ ስለሚያደርግ እንቅልፍ ከመተኛትዎ ከአንድ ሰዓት በፊት ቴሌቪዢንዎን/ኮምፒተርዎን/ማጥፋት አይዘንጉ፡፡

✔ የሙቅ ሻወር መውሰድ /በሙቅ ውሃ ገላን መታጠብ

እንደ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ሁሉ የሙቅ ሻወር መውሰድ ጥሩ እንቅልፍ እንዲተኙ የሚረዳ ሲሆን ለእንቅልፍ ችግር የሚሆነው ግን ከመተኛትዎ እጅግ ቀርቦ ሲተገብሩት ነው፡፡ የሰውነት ሙቀት እጅግ ከጨመረ ለመተኛት ሰለሚቸገሩ ሰውነትዎ እስኪቀዘቅዝ ጊዜ ይስጡ፡፡

✔ ብዙ ፈሳሽ መውሰድ

ካፌን ያላቸውና አልኮል መጠጦችን መውሰድ ሰላማዊ ቅንቅልፍ እንዳይወስድን የሚዳርጉ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውንም ዓይነት ፈሳሽ ከአንድ ወይንም ሁለት ሰዓታት በፊት መውሰድ የውሃ ሽንት ለማስወገድ ከአንዴ በላይ እንዲነሱ ስለሚያደርግ አይመከርም፡፡ይህ ሲባል ግን እየጠማዎት ይተኙ ማለትም አይደለም፡፡ ምክንያቱም ውሃን ለመጠጣት መነሳትዎ አይቀርምና ስለዚህ ቀደም ብለው ተጥተው እና የውሃ ሽንት አስወግደው ሰላማዊ እንቅልፍ መተኛት ይችላሉ፡፡

✔ ሥራ መስራት

በተቻለ መጠን ሥራዎን በጊዜ ለማጠናቀቅ ይሞክሩ ምክንያቱም ሥራን ዘግይቶ/አምሽቶ መስራት አንጎልዎን የማነቃቃትና ላልተፈለገ ጭንቀትም ሊዳርግዎ ስለሚችል ነው፡፡

✔ ልብ አንጠልጣይ የሆኑ ልብ ወለድ መጻሕፍትን ማንበብ

አብዛኛውን ጊዜ አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ ልብ ወለዶችን ማንበብ እንቅልፍ ከመተኛት ሊያግዱን ይችላሉ ወይንም ከለመድነው ሰዓት እጅግ እንድንዘገይ ያደርጋሉ ይህም ሰውነታችን የሚገባውን የዕረፍት መጠን ስለሚሻ እንቅልፍ ሳንጨርስ መነሳት ለተቀረው ቀን የሚኖረንን ውጤታማነት በእጅጉ ይቀንሳል፡፡

✔ ከጥጋብ በላይ መመገብ እና ጨዋማ ምግቦችን መውሰድ

ከጥጋብ በላይ መመገብ እንዲጨነቁና እንቅልፍ በቶሎ እንዳይወስድዎ ስለሚያደርግ እራት ሲመገቡ በልኩ ቢሆን ይመከራል፡፡ጨው የበዛባቸው ምግቦችን በአራት ሰዓት መመገብ ሌሊት በውሃ ጥማት ስለሚቀሰቅስዎ እንዲመገቡ አይመከርም፡፡

✔ ከህይወት አጋርዎ/ከቤተሰብዎ ጋር መጋጨት

እንቅልፍ ለመተኛት ቢያስቡ አዕምሮዎን ነጻ አድርገው መሆን ይኖርብዎታል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከጥል ወይንም ከአስደንጋጭ አጋጣሚ በኋላ ወዲያውኑ ለመተኛት እጅግ እንደምንቸገር ነው፡፡ ስለዚህ የሚፈታ ችግርም ካለ በጊዜ ተነጋግሮ ችግሩን መፍታት ለሰላማዊ እንቅልፍ ወሳኝ ነው፡፡

እብክዎ ለወዳጅዎ ያካፍሉ!!

ጤና ይስጥልኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.