ሁን ልጅሽ መጫወት፣ መሮጥ፣ ያለማቋረጥ ማውራት ጀምሯል፡፡ አመጋገቡም ይህንን መሰረት አድርጎ መቀየር አለበት፡፡

በዚህ እድሜው ልጄን ምን ያህል መመገብ አለብኝ?

c7ልጆች ምንም እንኳን በፊት ከነበረው አሁን በእድሜም ፣ በክብደትም ሆን በእንቅስቃሴ ቢበልጡም የሚያስፈልጋቸው የካሎሪ መጠን ከክብደታቸው አንፃር ሲታይ ከበፊቱ ያንሳል፡፡ ይህም የሆነው እድገታቸው ከበፊቱ ዝግ ስለሚል ነው፡፡ አሁን የተመጣጠነ ምግብ መብላት መጀመር አለባቸው፡፡ ዳዴ የሚሉ ህፃናት በቀን ከ1000 እስከ 1400 ኪሎ ካሎሪ ምግብ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከተለመዱት ምግቦች በተጨማሪ ከ3-4 የሻይ ማንኪያ እንደ አሳ ዘይት የመሳሰሉ ተጨማሪ ምግቦች ያስፈልገዋል፡፡ በቀን መመገብ ያለበትን የካሎሪ መጠን ከተለያዩ ምግቦች ያገኛል፡፡ እነዚህን ምግቦች እንደሚከተለው በምድብ ከፋፍለን ማየት እንችላልን፡- የጥራጥሬ ምርቶች፣ አትክልት፣ ስጋ ወይም አተር ፣ ፍራፍሬ እና ወተት ናቸው፡፡ ስለዚህ በቀን ውስጥ የሚከተሉትን ምግቦች እንደሚመቾት እያቀናበሩ ሊመግቡት ይችላሉ፡፡ ቁም ነገሩ በተቻለ አቅም ከአራቱም ምድቦች ያሉ ምግቦች አመጣጥኖ ለልጅዎ መመገብ ነው፡፡ ለመረዳት ቀለል እንዲል በየእለቱ የሚያስፈልገውን መጠን ከእድሜያቸውና ከምግብ አይነቱ አኳያ በሰንጠረዥ አስቀምጠነዋል፡፡ በዚህ መሰረት ለልጅዎ ምግብ ሲያዘጋጁ – ቁርስ – ተቀቅሎ የተፈጨ ካሮት፤ ምሳ – ¼ እንጀራ በሽሮ ወጥ፣ 1 ሙዝ ፤ እራት – አንድ ዳቦ በደቃቁ ተከትፎ በተጠበሰ ስጋ ቢያበሉና ወተት ቢያጠጡት ሚበቃውን ያህል ምግብ አግኝቷል፡፡

343በሰንጠረዥ ሁለት እና ሶስት የተጠቀሱት ቁጥሮች በሰንጠረዥ አራት ውስጥ ያሉትን የምግብ አይነት መጠን ያመላክታል፡፡በዚህ መሰረት ለልጆ ምግብ ሲያዘጋጁ – ቁርስ – ተቀቅሎ የተፈጨ ካሮት፤ ምሳ – ¼ እንጀራ በሽሮ ወጥ፣ 1 ሙዝ ፤ እራት – አንድ ዳቦ በደቃቁ ተከትፎ በተጠበሰ ስጋ ቢያበሉና ወተት ቢያጠጡት ሚበቃውን ያህል ምግብ አግኝቷል፡፡

ልጄ እራሱን መመገብ የሚጀምረው መቼ ነው?


አንድ ልጅ በአማካይ ዘጠኝ ወር ሲሞላው በአውራ ጣቱና ሌባ ጣቱ እቃ መያዝ ይጀምራል፡፡ ጡጦውን በደንብ መያዝና እራሱን መመገብ ይችላል፡፡ ብዙ ህፃናት አንድ አመት ከሞላቸው በኋላ ምግባቸውን በራሳቸው መብላት ይችላሉ፡፡ እስከ አንድ አመት ከስድስት ወራቸው ድጋፍ የሚፈልጉም አሉ፡፡ ከሁለት አመታቸው በኋላ ግን ክዳን በሌላቸው ኩባያና ብርጭቆ በስርአት ይጠጣሉ፡፡ ነገር ግን ጡጦ የሚመርጡ ከሆነ አትከልክሏቸው፣ ምንም ጉዳት የለውምና፡፡ ምግባቸውን በደንብ እስከበሉ ድረስ በራሳቸው እጅ መመገባቸው የሚደገፍ ነገር ነው፡፡ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች የእጆቻቸው ክህሎት ከማዳበር በተጨማሪ በእናትና አባታቸው ላይ ያላቸውን አላስፈላጊ ጥገኛነት ይቀንሳል፡፡ የተለያዩ ነገሮችንም በራሳቸው እንዲሞክሩ ይረዳቸዋል፡፡

 

ምንጭ — አዲስ ጤና

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.